Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Sunday, 06 May 2012 15:08

የተሰጠንን አስተያየት ተቀብለናል፤ እናመሰግናለን

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ዘወትር አርብ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ 12 እንዲሁም ቅዳሜ ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ የሚተላለፈውን የ”ጣዕም ልኬት” የተሰኘ ፕሮግራማችንን አስመልክቶ ቃል ኪዳን ይበልጣል የተባሉ አድማጭ በዚህ ጋዜጣ ላይ የሰጡትን አስተያየትተመልክተነዋል፡፡ ይህ ፕሮግራማችን ላለፉት አራት አመታት በሸገር ሬዲዮ ጣቢያ ሲተላለፍ ከቆየ በኋላ በቅርቡ በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ሬዲዮ ጣቢያ መተላለፍ ጀምሯል፡፡ በዚህ ሁሉ የሥራ ጊዜያችን የፕሮግራማችንን ጠንካራ ጐንም ሆነ ደካማ ጐናችንን አንስቶ እንዲህ በይፋ ለማመስገንም ሆነ ለመወቀስ የቻለ ወገን አልነበረም፡፡ የምንሠራበትን ጣቢያም ጨምሮ ማለታችን ነው፡፡ በእርግጥ ከተለያዩ አድማጮች በስልክ፣ በደብዳቤና በኢሜይል የተለያዩ አስተያየቶች ይደርሱናል፡፡ በዚህም ሲበዛ ደስተኞች ነን፡፡

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከዚህ በዘለለ መልኩ ስለእኛም ሆነ ስለሌሎች ፕሮግራሞች የተሰጡትን አስተያየቶች ተቀብሎ ለማስተናገድ መቻሉ የሚያስመሰግነው ሲሆን የአስተያየቱ አቅራቢንም ቃልኪዳንይበልጣልን እጅግ አድርገን ማመስገናችንን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡በፕሮግራማችን ላይ ሊስተካከሉ ይገባቸዋል ተብለው የተጠቀሱትንም ጉዳዮች የተቀበልንና ማስተካከያዎችንም ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን በዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን፤ እናመሰግናለን፡፡ሠርፀ ፍሬስብአት

 

 

 

Read 2255 times Last modified on Sunday, 06 May 2012 15:11