ታጋቹ ለባለቤቱ ባስተላለፈው መልዕክትም፤ ባለቤቱዋ በደህና ሁኔታ ላይ እንዳለ እንድታውቅና የሚያስፈልጉትን ህክምናዎች በሙሉ እንደሚያገኝ እንድታውቅ እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡
የአልቃይዳው መሪ አይመን አልዛዋሪ፤ ባለፈው ታህሳስ ወር ለዋረን ዋይንስተን መታገት አልቃይዳ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ በመግለፅ፤ አሜሪካ የታሊባን እስረኞችን እንድትለቅ፣ በፓኪስታን በአፍጋኒስታን፣ የመን፣ ሶማሊያ እና ጋዛ የምታደርገውን የአየር ድብደባም እንድታቆም ጠይቆ ነበር፡፡
የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄይ ካርኔ በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ፤ ዋረን በአስቸኳይ እንዲለቀቅ ጠይቆ “ከአልቃይዳ ጋር መደራደር አንችልም፤ አንደራደርምም” ብለዋል፡፡