Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 May 2012 08:54

የፈረንሳይ አዲሷ ቀዳማዊ እመቤት!

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ፈረንሳይ ባካሄደችው ምርጫ ፕሬዚዳንት ሳርኮዚ ተሸንፈው ሶሻሊስቱ ፍራንሷ ሆላንዴ አዲሱ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን አውጀዋል፡፡ የኤሊዜ ቤተመንግስትም አዲስ ቀዳማዊ እመቤት ተቀብሏል - ቫለሪ ትሬርዌራርን፡፡ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ለ”ፓሪስ ማች” ጋዜጣ የፖለቲካ አምድ ዘጋቢ የነበረችው ቫለሪ፤ ለአለም ፖለቲካ አዲስ አይደለችም፡፡ ከፍራንሷ ሆላንዴ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይፋ ካደረጉ በኋላ የፖለቲካ አምድ ዘጋቢነቷን ትታ “የጥቅም ግጭቶችን ማስወገድ ስለሚቻልባቸው ጥበቦች” ፀሀፊ ሆናለች፡፡

ከሁለት ጋብቻዎች ፍቺ በኋላ ከሆላንዴ ጋር አብረው በመኖር አራት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ሆላንዴ፤ ፕሬዚዳንት መሆናቸውን ተከትሎ የቀድሞው ነፃነቷ ላይ  ገደብ መኖሩ እንደሚያሰጋት የተናገረችው ቫለሪ፤ ሰዎች የእርሷን ድርጊት ከፕሬዚዳንቱ ጋር ሊያያዙ የሚችሉባቸው አጋጣሚዎች ሊኖሩ መቻላቸው አሳስቧታል፡፡ ይህን ስጋትም ስትገልፅ፤ “በእርግጥ ተጨንቄያለሁ፤ የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት አጋር መሆን ቀላል ነገር አይደለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ እያንዳንዱ ነገር በፍጥነት መገናኛ ብዙሀን ዘንድ ይደርሳል፡፡ ትንሽ ስህተት ትልቅ ውድቀት ሊያስከትል ይችላል” በማለት ይገልፃሉ፡፡

የ46 አመቷ ቫላሪ ዩኒቨርሲቲ ከገባች በኋላ የ”ፓሪስ ማች” የሶሻሊስት ፓርቲ የፖለቲካ ዘጋቢ በመሆን፣ በ1989 ስራ በጀመረችበት ወቅት ነው ከሆላንዴ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘችው፡፡ ሆላንዴ ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ከጀርባ ሆና ድጋፍ ማድረጓን ብዙዎች ይተቹት የነበረ ቢሆንም ከአይነፋርነት የመነጨ ነው ይላሉ ቫለሪ፡፡ በአሁኑ ወቅት ከጋዜጠኝነት ወጥታ የፖለቲካው ጨዋታ ዋነኛ ገፀባህርይ መሆኗን አስመልክቶ በሰጠችው አስተያየት፤ “እኔ ጥሩ ታዛቢ ነኝ፤ ነገሮች እንዴት እንደሚሆኑ መታዘብን እመርጣለሁ” ብላለች፡፡

ቆፍጠን ያለ ባህርይ እንዳላት የሚነገርላት ቫለሪ፤ በአንድ ወቅት የስራ ባልደረባዋ ሴቶች ላይ በሰነዘረው አስተያየት ጥፊ ያቀመሰችው ሲሆን “ሴቶች ለማጌጥ ብቻ የተፈጠሩ እና ቡችሎች” አይደሉም በማለት ተናግራለች፡፡ ከሳርኮዚ ፓርቲ በኩል የተሰጣትን ቅፅል ስም ተከትሎም ሳርኮዚ ይቅርታ እንዲጠይቁ አድርገዋቸዋል፡፡ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅትም “ቫለሪ የፍራንሷ ሆላንዴ አማላይ ንብረት” በሚል የወጣውን ጽሑፍ በተመለከተ “በቀጣሪዬ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ያለ እኔ እውቅና ፎቶዬን መፅሄቱ ላይ በማየቴም ተገርሜያለሁ” ያለችው ቫለሪ፤ “ብራቮ ፓሪስ ማች በአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ላወጣው  ቀስቃሽ ጽሑፍ” ስትል አጣጥላዋለች፡፡

የፈረንሳይ ቀዳማዊ እመቤቶች ብዙ ሚና እንደሌላቸው የሚጠቁሙ መረጃዎች፤ የፊቶቹ በአብዛኛው በበጎ አድራጎት አካባቢ ይሳተፉ ነበር ይላሉ፡፡ ሚሊዬነሯ ሞዴል እና የቀድሞዋ ቀዳማዊ እመቤት (የሳርኮዚ ባለቤት) ካርላ ብሩኒ፤ በኤራዚ ቤተመንግስት ሳለች የዘፈን አልበም አሳትማለች፡፡ አወዛጋቢ መግለጫዎችን የሠጠችውም ቤተመንግስቱን እንደረገጠች ነው፡፡

“ከአንድ ሠው ጋር ጋብቻ ሠለቸኝ” ያለችው ካርላ፤ ከሳርኮዚ ጋር ያላት ግንኙነት ግን አሪፍ እንደነበር ገልፃለች፡፡ አነጋገሩዋ ለአገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን ማላገጫ እና የስላቅ ምንጭ ሆኖ የነበረ ቢሆንም፡፡

የሆላንዴ ባለቤት ከቀድሞዎቹ የተለየ ሚና እንደሚጫወቱ ያሰቡ ይመስላሉ የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች፤ አሸናፊነታቸውን ያወጁ እለት ባደረጉት ንግግር ቫለሪ እንዲያጅቧቸው ያደረጉትም ለዚህ አላማ ነው ብለዋል፡፡ ሳርኮዚ ከባለቤታቸው ጋር ጋብቻቸውን የፈፀሙት ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ሲሆን ሆላንዴም ተመሳሳይ እርምጃ ይወሰዱ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ “ለሶስት አስር አመታት አብረን ኖረናል፡፡

ምክንያቱም ጋብቻን እንደ ቡርዧ ተቋም ስለምናየው ብለው ጉዳዩ እኔ እና ቫላሪን የሚመለከት ቢሆንም አናደርገውም፤ የመጋባት ግዴታም የለብንም፤ ከወሰንን ግን ሲሆን ታዩታላችሁ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

 

 

Read 3369 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 11:35