Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 May 2012 10:00

“እህቷ ከፎቅ ስትወድቅ አይታለች”

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ወደ አረብ አገር ተመዝግበው የሚሄዱት ቁጥራቸው ከእጥፍ በላይ አድጓል

አሰሪዋ ሊደፍራት ሲል ወደኋላ ስትሸሽ ከ4ኛ ፎቅ ላይ የወደቀችው ማህሌት የቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል “ባለቤቴን ስታይ ትስቂያለሽ፣ ያልተገባ አለባበስ ትለብሻለሽ” በሚል ፀጉሬን ይዛ ደረጃ ለደረጃ ትጐትተኝ ነበር ብላለች - ጭንቅላቱዋ  ቁስል ብቻ እንደሆነ በመግለፅ፡፡ ሁለት እጆቿን ፍሪጅ ውስጥ የምትከትባትም በቅዝቃዜው ለመቅጣት ሲሆን የሜሮን እጆች ድርቅ ያሉትም በዚሁ የተነሳ እንደሆነ ተናግራለች፡፡በ3ዓመት 200ሺ ኢትዮáያውያን ወደ አረብ አገራት ሄደዋል አሰሪዋ ሊደፍራት ሲል ወደኋላ ስትሸሽ ከ4ኛ ፎቅ ላይ የወደቀችው ማህሌት የቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል “ባለቤቴን ስታይ ትስቂያለሽ፣ ያልተገባ አለባበስ ትለብሻለሽ” በሚል ፀጉሬን ይዛ ደረጃ ለደረጃ ትጐትተኝ ነበር ብላለች - ጭንቅላቱዋ  ቁስል ብቻ እንደሆነ በመግለፅ፡፡

ሁለት እጆቿን ፍሪጅ ውስጥ የምትከትባትም በቅዝቃዜው ለመቅጣት ሲሆን የሜሮን እጆች ድርቅ ያሉትም በዚሁ የተነሳ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ የሁለት ልጆች እናት የነበረችው ወ/ሮ አለም ደቻሳ፤ ወደ ቤሩት የሄደችበት ምክንያት ከአብዛኞቹ ሴቶች የተለየ ነው፡፡ ከባለቤቷ ከአቶ ለሜሳ ኤታ ጋር ለ14 ዓመት በትዳር ኖራለች፡፡ ባለቤቷ” ሲዲሴ ኡርጋ ከተባለች ሴት ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመሩን ስትሰማ ነው ትዳራቸው መናጋት የጀመረው፡፡ በባልና ሚስቱ መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ሁሌም ያስታርቅ እንደነበር የሚናገረው ታናሽ ወንድሟ ለታ ደቻሳ፤ትዳራቸው ህጋዊ እንዲሆንም እወተውታቸው ነበር ብሏል፡፡ ሆኖም ህጋዊ ከመሆኑ በፊት ፈረሰ፡፡ አለም ወደ ቤሩት ለመጉዋዝ የቆረጠችው” የባለቤቷ አዲስ ፍቅረኛ ማርገዙዋን ስትሰማ እንደሆነ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ከወንድሟ አስር ሺህ ብር ተበድራ ለመሄድ ስትነሳ “አትሂጂ ትንሽ ነገር ክፈቺና እዚሁ ስሪ ብያት ነበር - ግን አሻፈረኝ አለች” ይላል - ለታ ደቻሳ፡፡ መሄዷ ካልቀረም በህጋዊ መንገድ እንድትሄድ ነግሬያት ነበር የሚለው ታናሽ ወንድሟ “ሆኖም 7ሺ ብር ከፍላ በደላላ መሄዱዋን መረጠች ብሎዋል፡፡ በሄደች በሳምንቷ ስልክ ደውላ ቤሩት መግባቷን እንደነገረችው የገለፀው ለታ “የቀድሞ ባለቤቷ ልጆቹን ለእናቷ እንዲሰጥላት ማሳሰቡዋንም ያስታውሳል፡፡ ከባድ መኪና ላይ የሚሰራው  ለታ ደቻሳ ግን በአካባቢው ስላልነበረ እህቱ ያዘዘችውን ሳይፈፅም እንደቀረ ተናግሮዋል፡፡  ቤሩት በሄደች በሁለተኛው ወር ስልክ ደውላ የአካባቢውን ሰዎች ስትጠይቅ ለሜሳ፤አዲሱዋን ሚስቱን ቤቷ ውስጥ እንዳስገባና ልጆቿም ጥሩ ይዞታ ላይ እንዳልሆኑ በመስማቷ ብስጭት ውስጥ መግባቷን ምንጮች ይናገራሉ፡፡ አለም ያልተለመደ ባህርይ ማሳየት ጀምራ እንደነበርም ከአሰሪዎቹዋ አካባቢ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል፡፡ አሠሪዎቿ ጥሩ እንደሆኑ ነግራኝ ነበር የሚለው ወንድሟ፣ቤሩት ከገባች በሁዋላ ሁለቴ ብቻ መደወሉዋን ያስታውሳል፡፡ የቀድሞ ባለቤቷ ሚስት” መውለዷን ስትሰማ በጣም በመረበሹዋ  አሠሪዎቿ ተደናግጠው ትኬት ቆርጠውላት ነበር - ወደ ሀገሯ እንድትመለስ፡፡ ዓለም ግን ፈቃደኛ አልነበረችም፡፡ ከቤት አምልጣ ለመጥፋት ስትሞክር አሠሪዎቿ አግኝተዋት፤ ኤምባሲ ወይም አገሯ እንድትሄድ ቢያግባቡዋትም ሁለቱንም አልፈልግም እንዳለች ምንጮች ያወሳሉ፡፡ ከአሰሪዎቿ ጋር ስትታገል የሚያሳይ ምስልም በኢንተርኔት ተሰራጭቷል፡፡ ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ የተገኘው መረጃ “ ዓለም አገሯ መምጣት እንደማትፈልግ እየጮኸች ትናገር እንደነበር ይጠቁማል፡፡ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አሰሪዎቹዋ ህክምና እንድታገኝ ሆስፒታል አስገብተዋት እንደነበረ የሚናገሩት  ምንጮች” ባለቤቷን ማየት ስለማትፈልግ ወደ አገር ቤት እንዳትወስዱኝ ትል እንደነበረ ገልፀዋል፡፡ ዓለም ሆስፒታል  በገባች በሦስተኛው ቀን በአንሶላ ቅዳጅ ታንቃ ህይወቷ እንዳለፈ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ህይወቷ ካለፈ ሁለት ወር ቢሆናትም እስካሁን  አስከሬኗ ወደ አገሯ እንዳልመጣ ቤተሰቦችዋ ይናገራሉ፡፡ በካሳ ጉዳይ ግን በቀድሞው ባለቤቷና በቤተሰቦቹዋ መካከል ውዝግብ ተፈጥሩዋል፡፡ ከአዲሱዋ ሚስቱ የወለደው የአምስት ወር ልጅ እንዳለው የገለፀው ለሜሳ፤ ከአለም ጋር ፊርማ ባይኖረውም ልጆች እንዳሉት ይናገራል - “ይሄ ደግሞ ከፊርማ በላይ ነው” በማለት፡፡ የዓለም ቤተሰቦች አዲሱዋን ሚስቱን በ80 ተፈራርሞ እንዳገባት በመጥቀስ” ካሳው አይገባውም በሚል ሲከራከሩ እሱ ደግሞ አለምም ሚስቴ ስለሆነች ካሳው ይገባኛል” ልጆቿን እያሳደግሁ ነው ብሎዋል፡፡ የአለም ታናሽ ወንድም ግን ካሳው ሙሉ በሙሉ ለልጆቹዋ መዋል አለበት ባይ ነው “ለልጆቿ ስትንከራተት ነው የሞተችው” ት/ቤት ይግቡ እያለች” ስለዚህ መስዋዕት የሆነችበት ካሳ ለልጆቿ መማሪያ መዋል አለበት” የሚለው ወንድሟ፤ ካልሆነ መንግስት በፈለገው መንገድ ለልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን በስማቸው እንዲያደርግላቸው ጠይቋል፡ከባሌ ሮቤ ወደ አዲስ አበባ የመጣችው የ32 ዓመትዋ መስከረም (ስሟ የተቀየረ)” ትምህርቷን ከ9ኛ ክፍል አቋርጣ ነበር የጐረቤቷ ልጅ ወደ ሄደችበት ዱባይ ያመራቸው - በ2000 ዓ.ም፡፡ ለሁለት አመት ከሰራች በሁዋላ ወደ ትውልድ ቀዬዋ በመመለስ “ሁለት በሬዎችና ሦስት ላሞች  እንደገዛች ቤተሰቦቹዋ ይናገራሉ፡፡ ሆኖም ባሌ ውስጥ ለመቆየት ስላልፈለገች ወደ አዲስ አበባ ተመለሰችና አክስቱዋ ጋ ተቀምጣ የፀጉር አሰራር ሙያ መማር ጀመረች፡፡ ብዙም አልዘለቀችበትም  “ትምህርቱ ወጪ ብቻ ነው” በማለት ወደ ቤሩት ሊባኖስ ለመሄድ ትነሳለች፡፡ በደላላ በሱዳን በኩል እንደሄደች የምትናገረው መስከረም “ የሊባኖስ የስድስት ወር ቆይታዋ በመከራ የተሞላ እንደነበር ገልፃለች፡፡ አሠሪዋ “ስራ እያለ እንዴት ትተኛለሽ” በሚል በብልቃጥ የሚሸተት ነገር ትሰጣት እንደነበር ትናገራለች - ማነቃቂያ ነው እያለች፡፡ ሆኖም ስራዋን ከጨረሰች በሁዋላም መድሃኒቱ ቆሞ ያስቀራት እንደነበር ተናግራለች፡፡ ምግብ የሚሰጠኝ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነው  የምትለው መስከረም “ምግብ አለመብላቱዋ ከምታሸተው መድሃኒት ጋር ተዳምሮ አቅም አሳጥቶዋት እንደነበር ገልፃለች፡፡ የምታሸተው መድሃኒት አደገኛና  ክልክል እንደሆነ የነገሩዋት የአሰሪዋ እናት ጉዋደኛ እንደነበሩ የጠቆመችው መስከረም “አንዳንድ የአረብ ወንዶች ለሱስ እንደሚጠቀሙበት” እንቅልፍ እንደሚነሳቸውና ጉዳቱም ከፍተኛ እንደሆነ ነግረውኛል ብላለች፡፡  ከዚያ በኋላ ግን ጊዜ አላጠፋችም - ከምትሠራበት ቤት ጠፍታ በመውጣት ወደ አገሯ እንደተመለሰች ትናገራለች፡፡ ሆኖም ቤተሰቦቿ አዲስ አበባ እንዳለች አያውቁም፡፡ የእስዋን እጅ የሚጠብቁ ችግረኞች በመሆናቸው መርካቶ አካባቢ የልብስ ዝምዘማ ስራ እየሰራች ገንዘብ ትልክላቸዋለች፡፡ እዛው አረብ አገር ያለች እንዲመስላቸውም ቀለበት መንገድ ላይ ወይም ትልቅ ሆቴል  ሄዳ ፎቶ በመነሳት ለቤተሰቦችዋ እንደምትልክ ተናግራለች፡፡  በአንድ የማገገሚያ ጣቢያ ውስጥ ከህመሟ ለማገገም እየጣረች እንደሆነ የገለፀችው መስከረም “አሰሪዋ ታሸትታት የነበረውን መድሃኒት ስለማታገኝ ያዞራታል፡፡ በስራዋ ላይ ሆናም ልትወድቅ ትችላለች፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ስራው ያስጠላኛል - ብላለች መስከረም፡፡ ለወላጆቹዋ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው የ29 አመቷ ሜሮን አበራ” ወደ ሶሪያ ለመሄድ ስትነሳ  ከቤተሰቦችዋ ሃሳቡዋን የደገፈላት ማንም አልነበረም፡፡ ሜሮን ነጥብ ባይመጣላትም 12ተኛ ክፍልን አጠናቃለች፡፡ ዓምና ወደ ሶሪያ የተጓዘችው በህጋዊ ኤጀንሲ አማካኝነት ሲሆን የኤጀንሲው ባለቤት ከቤተሰብዋ ጋር ቅርበት ያለው ስለሆነ ብዙም አላሳሰባትም ነበር፡፡ ባለቤቱ እንደውም የተከበረ የንጉሳውያን ቤት ውስጥ እንደምትቀጠር ቃል ገብቶላታል - ሶሪያ ስትገባ የገጠማት ፍፁም የተለየ ቢሆንም፡፡ ስራ በጀመረች በወሩ አሠሪዋ ፓስፖርቷን እንደወሰደችባት የምትናገረው ሜሮን” ለጊዜው ምክንያቱ ባይገባትም በሁዋላ ግን ጠፍታ እንዳትሄድ ለማድረግ እንደሆነ አውቃለች፡፡ ሜሮን እንደምትለው” ሴትየዋ ያላደረገቻት ነገር የለም፡፡ “ባለቤቴን ስታይ ትስቂያለሽ፣ ያልተገባ አለባበስ ትለብሻለሽ” በሚል ፀጉሬን ይዛ ደረጃ ለደረጃ ትጐትተኝ ነበር ብላለች - ጭንቅላቱዋ  ቁስል ብቻ እንደሆነ በመግለፅ፡፡ ሁለት እጆቿን ፍሪጅ ውስጥ የምትከትባትም በቅዝቃዜው ለመቅጣት ሲሆን የሜሮን እጆች ድርቅ ያሉትም በዚሁ የተነሳ እንደሆነ ተናግራለች፡፡ አንዲት ኢትዮጵያዊት አብዳ ራቁቷን ስትሄድ ያየችው አሠሪዋ “የአገርሽ ልጅ ወንድ ፈልጋ ራቁቷን ትሄዳለች” ትላትና ሜሮን ልጅቷን ለማየታ ትወጣለች፡፡ እግረመንገድዋን የአገሯ ልጅ ከሆነችው ጐረቤቷ ኢትዮጵያዊት ጋር ተመካክራ ትመለሳለች፡፡ ማታ አሠሪዎቿ ሲተኙ ጠብቃ” መስኮት ላይ ገመድ በማሰር” በገመዱ ተንጠላጥላ ጐረቤቷ ቤት ገብታ አደረች፤ ጠዋት እጇን ለፖሊስ ሰጠች፡፡ ሜሮን በህገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ መግባት በሚል ክስ ተመስርቶባት   ፍርድ ቤት ቀርባለች፡፡ ስትያዝ በፒጃማ ብቻ ስለነበረች “የለሊት ሴተኛ አዳሪ” በሚል ጠርጥረዋት እንደነበር ገልፃ” ሆኖም በተመሳሳይ ዘርፍ ይሠራሉ ተብለው ስማቸው ከተመዘገቡ ኢትዮጵያዊያን ዝርዝር ውስጥ ባለመካተትዋ” ዳግመኛ ወደዚያ አገር እንዳትገባ ተደርጋ እንደተባረረች ተናግራለች፡፡ ሜሮን አሁን ከህመሟ እያገገመች መሆኑን ገልፃለች፡፡ ታላቅና ታናሽ እህትማማቾች አበባና ማህሌት ወደ ሶሪያ የሄዱት የዛሬ ሁለት ዓመት ነበር- በ2002 ዓ.ም፡፡ አበባ እህት ቤት” ስትቀጠር ማህሌት ደግሞ ወንድም ቤት ነው የተቀጠረችው፡፡ ቤቱም ትይዩ ስለነበር ፍርሃት አላደረባቸውም፡፡ የ28 ዓመትዋ አበባ የምትሰራበት ቤት በምቾት የሚያንፈላሰስ ባይሆንም ለክፉ የሚሰጥ አይደለም፡፡ የ26 ዓመትዋ ማህሌት ግን አስቸጋሪ አባወራ ነበር የገጠማት፡፡ በተደጋጋሚ አስገድዶ ለመድፈር ሙከራ ማድረጉን ማህሌት ለአበባ ገልፃላት ነበር፡፡ ማህሌት ለስራ ባጎነበሰች ቁጥር አሰሪዋ ወደ መቀመጫዋ  ይጠጋት እንደነበርና እንደሚደባብሳት አበባ ትናገራለች፡፡ የቱንም ያህል ብትሰጋና ራስዋን ለመከላከል ብትሞክርም አልቀረላትም፡፡ ባኞ ቤት እያፀዳች ሳለ በመቀመጫዋ በኩል በአሠሪዋ ተደፈረች፡፡ ታምማ ተኛች፡፡ እህቷ የደረሰባትን ስቃይ የሰማችው አበባ” ለጊዜው ከመብገን በቀር ምንም ማድረግ ባትችልም እህቷን ይዛ ለመጥፋት ቀን እየጠበቀች ነበር፡፡ የማህሌት አሠሪ ግን አሁንም ከአስነዋሪ ድርጊቱ አልታቀበም፡፡ አንድ ቀን የለመደውን ሊፈፅም  ወደ ማህሌት ሲጠጋ” እስዋ ወደ ሁዋላዋ ስትሸሽ” ሲጠጋ ስትሸሽ” ሳታውቅ ከአራተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ወድቃ” መሬት የቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ትገባለች፡፡ እንዳጋጣሚ እቃ በማጠብ ላይ የነበረችው አበባ” በመስኮት ውልብ የሚል ነገር ማየቷን ትናገራለች፡፡ እህቴ ትሆናለች ብላ ግን አልጠበቀችም፡፡ የእህቷን አደጋ የነገረቻት አሰሪዋ ነበረች፡፡ ማህሌት ወዲያው ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም አልተረፈችም፡፡ አበባ የእህቷን አስከሬን ይዛ ወደ አገሯ መጣች፡፡   አሁን የሱዋም አይምሮዋ ትክክል አይደለም፡፡ ቀን ቀን ትፈዛለች፡፡ ለሊት ለሊት ትቀዣለች፡፡ በተደጋጋሚ ቢላ ይዛ ራስዋን ለማጥፋት ስትሞክር ቤተሰብ ደርሶ አድኖዋታል፡፡ ለዚህ ዘገባ ስናነጋግራት” አብዛኛውን ቤተሰቦቿ እያገዝዋት ነው የመለሰችልን፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ወደ 200ሺ የሚጠጉ ኢትዮáያውያን በህጋዊ መንገድ ወደ አረብ አገራት እንደደተጉዋዙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

 

 

 

 

Read 20512 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 11:21