Saturday, 02 February 2019 15:09

ከ10/እርግዝናዎች አንዱና ከዚያ በላይ…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


     ባለፈው እትም እንዳስነበብናችሁ በኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ የሚቻልባቸው መንገዶች በህግ ተሸሽለው የተቀመጡ ሲሆን በዚህም የሚጠቀሙ የመኖራቸውን ያህል የማይጠቀሙም መኖራቸው የማይካድ መሆኑን GUTTMACHER Institute /January /2017/ ጥናቶች የሚጠቁሙ መሆኑን አስነብቦአል፡፡  ለዚህ እትም ለንባብ የምንላቸው ነገሮች፤
•በኢትዮጵያ ያለው የጽንስ ማቋረጥ ሁኔታ ምን ይመስላል?
• የጽንስ ማቋረጥ ድርጊት መቼ የት …ወዘተ ምን ይመስላል?
•ያልተፈለገ እርግዝና እና የታቀደ እርግዝና በኢትዮጵያ ምን ይመስላል?
•ሕጋዊ ጽንስ ማቋረጥ ተግባር እና ጽንስ ከተቋረጠ በሁዋላ ያለው አገልግሎት በኢትዮጵያ ምን ይመስላል?
•ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ምን ያስከትላል? የሚሉትንና ተያያዥ ነገሮች ነው፡፡
ጽንስ ማቋረጥ በኢትዮጵያ፡-  
በ2005/እንደውጭው አቆጣጠር የተመዘገበ መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ጽንስን ማቋረጥ ዛሬ ህጋዊ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ጽንስን ማቋረጥ የሚቻልበት ሕግ ቀድሞ ከነበረበት ማለትም እናትየው በሕይወት ወይንም በአካል ችግር ሲገጥማት ብቻ ይፈቅድ ከነበረበት ተሸሽሎአል፡፡ የተሻሻለው ሕግ ሴትየዋ በማንኛውም ሰው ተገዳ በመደፈርዋ ወይንም ያረገዘችው ዘመድ ከሆነ ሰው ከሆነ እንዲሁም ያረገዘችው ሰው እድሜዋ ህጻን ከሆነ ወይንም ያረገዘችው ሴት በአካልም ይሁን በአእምሮ ችግር ካለባት፤ የተረገዘው ልጅ ጤናማ ሆኖ የሚቀጥል ካልሆነ…ወዘተ ቀድሞ ከነበረው ህግ ተጨማሪ በሆኑ አሳማኝ ምክንያቶች በባለጉዳይዋ እና በሕክምና ባለሙያው ውሳኔ ደህንነቱ በተጠበቀ እና ህጋዊ በሆነ መንገድ ጽንሱ መቋረጥ ይችላል፡፡  
በኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስን ማቋረጥን በተመለከተ ተግባራዊ እንቅስቃሴውን በሕክምና ተቋማት መተግበር የሚቻልበትን መንገድ የሚያሳየው መመሪያ እንደውጭው አቆጣጠር በ2006/ዓ/ም በሕክምና ተቋማት ተግባራዊ እንዲሆን መመሪያ የወጣለት ሲሆን ይህም በአለም የጤና ድርጅት እውቅና ያለው ነው፡፡
በ2014 እንደውጭው አቆጣጠር በተገኘው መረጃ ወደ 620‚300 የሚሆን ጽንስ ማቋረጥ በኢትዮጵያ ተካሂዶአል፡፡ ይህም በአመት ሲሰላ ከ1‚000ሴቶች 28/የሚሆን ጽንስ ማቋረጥ እድሜያቸው ከ15-49/አመት በሆኑ የተፈጸመ ሲሆን በ2008/ዓ/ም ከነበረው ከ1‚000 ሴቶች 22/ጽንስ ማቋረጥ ድርጊቱ የጨመረ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሌሎች የምስራቅ አፍሪካ አገራት ማለትም ከ1‚000/ሴቶች 34/የጽንስ ማቋረጥ በየአመቱ ከሚተገበርባቸው በኢትዮጵያ የሚፈጸመው ጽንስ ማቋረጥ ያነሰ መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
የጽንስ ማቋረጥ ድርጊት መቼ ፤የት፤እንዴት …?
ጽንስን የማቋረጥ ድርጊት ከገጠር ይልቅ በከተሞች አየል ይላል፡፡ ይህም ቁጥሩ ሲሰላ በአመት ከ1‚000/ሴቶች 92/ጽንስ ማቋረጥ በአዲስ አበባ ሲኖር በተጨማሪም በድሬደዋና ሐረር ከ1‚000/ ሴቶች 78/ጽንስ ማቋረጥ  ተመዝግቦአል፡፡ ጽንስን የማቋረጥ ድርጊት በከተሞች የመብዛቱ ነገር ከሌሎች የኑሮ ሁኔታ እና ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረጉ ኑሮን ለማሸነፍ ሲባል በሚደረግ ፍል ሰት ጭምር ሲሆን ለወሲብ ግንኙነት በተለያዩ መንገዶች ማለትም በፍቃደኝነትም ይሁን በግ ዳጅ እንዲሁም ወሲብን ለመፈጸም ነጻ ከመሆን ጋር ተያይዞ የሚፈጠር ሲሆን እርግዝናው ሲከ ሰትም ጽንስ ማቋረጡን በሕጋዊ መንገድ ማድረግ አለዚያም በግላቸው ከሙያ ውጭ የሚፈ ጽሙ በመኖራቸው ድርጊቱን ለመመስጠር ይመቻል በሚል ስሜት መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
በ2014 የተመዘገበ መረጃ እንደሚያሳየው ከ10/እርግዝናዎች አንዱና ከዚያ በላይ የሚሆነው  በጽንስ ማቋረጥ እንደሚ ወገድ ነው፡፡  መረጃው እንደሚጠቁመው በ2014/ዓም፤
ያልተፈለገ እርግዝና በጽንስ ማቋረጥ የተወገደ 13%
ያልተፈለገ እርግዝና ጽንሱ በመሞቱ ወይንም ካለጊዜው በመወለዱ አለዚያም ጽንሱ የተቋረጠ 25%
በእቅድ የተረገዘ እርግዝናው ሕይወት ያጣ ወይንም የተወለደ 62%ሲሆኑ በጊዜው የተመዘገበው እርግዝና 4.3 ሚሊዮን መሆኑን የ GUTTMACHER Institute /January /2017/ መረጃ ያሳያል፡፡  
ጽንስን ለማቋረጥና ጽንስ ከተቋረጠ በሁዋላ የሚደረግ የህክምና እርዳታ፡-
በ2014/እንደውጭው አቆጣጠር እንደተገለጸው ወደ (326.200)ማለትም 53% የሚሆኑ ሴቶች ደህንነቱ የተጠበቀና በሕጋዊ መንገድ ጽንስ እንዲቋረጥ ያደረጉ ሲሆን በሕክምና ተቋም ገብ ተው የተገለገሉ እና ይህም ከ2008/ጋር ሲተያይ ከፍ ያለ ቁጥር እንደነበር ጥናቱ ያስረዳል፡፡ በ2008/ በጤና ተቀዋም ገብተው የተገለገሉት 27%ብቻ ነበሩ፡፡ በ2014/ሶስት አራተኛ የሚደርሱ የጤና ተቋማት ማለትም የመንግስት የጤና ተቋማት፤ የግል ወይንም መንግስታዊ ያልሆኑ የህክምና ተቋማት፤ እና ሆስፒሎች ባጠቃላይ በህጋዊ መንገድ ጽንስ ማስወረድ የሚችሉት በተሟላ የሕክምና መሳሪያና ባለሙያ የታገዘ አገልግሎትን ሰጥተዋል ማለት ይቻላል እንደ ጉትማቸር የጥናት ሰነድ፡፡ ከጥናት ሰነዱ መረዳት እንደሚቻለው አብዛኛው ጽንስ ማቋረጥ (66%)የተሰራው በግል ወይንም መንግስታዊ ባልሆኑ የህክምና ተቋማት ሲሆን ከጽንስ ማቋረጥ በሁዋላ ለሚደርሱ የጤና ችግሮች የህክምና አገልግሎት (72%) የተሰጠው ደግሞ በመንግስት ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ነው፡፡
ባጠቃላይም በ2008 -2014 ባለው ጊዜ ደህንነቱ የተጠበቀ ጽንስ የማቋረጥ የህክምና ስራ ቁጥሩ ከዜሮ ወደ 1/3ኛ እድገት ማሳየቱን ድርጊቶች ያመላክታሉ። አገልግሎቱን በመስጠቱም ረገድ በባለሙያዎች የሚደረግ ድጋፍም ይሁን ሕክምናውን በመስጠቱ ረገድ በ2008/(48%)የነበረ ሲሆን በ2014 ደግሞ ወደ 83% ከፍ ማለቱ ታይቶአል፡፡
ደህንነቱ ያልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ውጤት ፡-
ብዙ ሴቶች ደህንነቱ ባልተጠበቀ መንገድ ከጤና ተቋም ውጭ ወይንም በጤና ተቋም በሚያከ ናውኑት ውርጃ የተነሳ በሚደርስባቸው የጤና ችግር ለህክምና እርዳታ ወደ ጤና ተቋም የሚ መጡት በ2008/ዓ/ም እና በ2014/መካከል ያለው ቁጥር ከ52.600/ ወደ /103.600/በእጥፍ አድጎአል፡፡ በ2014/ዓ/ም ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ከጽንስ ማቋረጥ በሁዋላ በተለያዩ የስነተዋልዶ ጤና ችግር የሚሰቃዩት እና ሆስፒታል አልጋ እንዲይዙ የሚደረጉት በ2008/ 23% ነበሩ፡፡  
በኢትዮያ የጤና ባለሙያዎች እንደሚገምቱት /40%/ የሚሆኑት ከጤና ተቋም ውጭ ጽንስ ማቋረጥን ያሚያደርጉ ለከፋ የጤና ችግር የሚጋለጡ ሲሆን ወደ /74%/ የሚሆኑት ከፍ ያለ ሕክምና እንዲደረግላቸው ሁኔታዎች ያስገድዳሉ፡፡ በእርግጥ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ከጤና ተቋም ውጭ ጽንስ ማቋረጥን የሚያካሂዱ በአጋጣሚ የጤና ችግር ላይገጥማቸው ቢችልም ነገር ግን አደገኛነቱን መካድ አይቻልም፡፡ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሆነው ጽንስን ስለማቋረጥ የተደነገገው ሕግ ከወጣ በሁዋላ ሴቶች የሚጠቀሙበትን ዘዴ በማሳየት ረገድ ልዩነቱ እንደ ሚከተለው ተመዝግቦአል፡፡
በ2008/በሕክምና ተቋም ጽንስን ያቋረጡ 27%ሲሆኑ በ2014/53%/ናቸው፡፡
በ2008/ከሕክምና ተቋም ውጭ ጽንስን ያቋረጡ 73%ሲሆኑ በ2014/47% ናቸው፡፡
በጥቅሉም አሁን ያለው ሁኔታ ጽንስን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ማቋረጥ በመለመድ ላይ መሆኑን ነው፡፡
ምንጭ፡- GUTTMACHER Institute /January /2017/

Read 2010 times