Saturday, 09 February 2019 12:25

ጥራት…ሚዛናዊነት እና ክብር በስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር 27ኛ አመታዊ ጉባኤ


     የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እንደውጭው አቆጣጠር February/5-6/2019 ማለትም ጥር 28-29/2011 በአዲስ አበባ ተካሂዶአል፡፡ ይህ አመታዊ ጉባኤ የማህበሩ አባላት፤ ከጠቅላላ ሐኪምነት ወደሙያው ለመግባት ልዩ ትምህርት በመውሰድ ላይ ያሉ ሐኪሞች፤ እንዲሁም እንግዶች ባጠቃላይም እስከ ሶስት መቶ የሚደርሱ ተሳታፊዎች የተገኙበት ነው፡፡ (PROMOTING QUALITY, EQUITY, & DIGNITY in Reproductive Healthcare) በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው አመታዊ ጉባኤ መክፈቻ ስነስርአት ላይም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲ ያዊት ኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ሌሎች ተጋባዥ እን ግዶች የተገኙ ሲሆን ዶ/ር ሊያ የመክፈቻ ንግግር አድርገው ነበር፡፡
ዶ/ር ሊያ እንደተናገሩት የኢትዮያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ተመስርቶ በስነተዋልዶ ጤና ላይ ትኩረት ማድረግ ከጀመረበት እንደውጭው አቆጣጠር ከ1992/ዓ/ም ጀምሮ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እጅ ለእጅ ተያይዞ ማለት በሚያስችል ሁኔታ ጠቃሚ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ እሙን ነው፡፡ ማህበሩ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በትብብር ከሰራቸው ስራዎች መካከል፤
•የእናቶችን ደህንነት መጠበቅ፤
•እናቶች ከወሊድ በሁዋላ መድማት እንዳይገጥማቸው መከላከል፤
•የወሲብ ጥቃት ለደረሳባቸው አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፤
•አስቸኳይ እና የተሟላ የማህጸን እና የጨቅላዎች የህክምና አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል የባለሙያዎችን ብቃት ለማሻሻል የተሰሩ ስራዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡  
ዶ/ር ሊያ በማከል እንደገለጹትም በዘንድሮው አመታዊ ጉባኤ በመሪ ቃልነት የተቀመጠው (PROMOTING QUALITY, EQUITY, & DIGNITY in Reproductive Health care) ወቅታዊና ትክክለኛ  የትኩረት አቅጣጫ ሲሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአምስት አመቱ የጤና አገል ግሎት በመመሪያነት ቋሚ የግቡ አቅጣጫ አድርጎ የያዘው ወይንም እየተገበረው ያለ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የአሁኑ የአለም አቀፍ የጤና ድርጅት ዳይሬክተር በ71/ኛው የአለም የጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ እንደ ተናገሩት በአለም አቀፉ የጤና አጠባበቅ ስርአት ከጥራት ፤እኩልነት እና ክብርን ከመጠበቅና ከማስቀደም በላይ ምንም አይነት አለም አቀፍ የስነተዋልዶ ጤና መብት አይኖርም ብለዋል።
በእርግጥ አሉ ዶ/ር ሊያ…በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የእናቶችን ጤንነት በማሻሻሉ ረገድ ከግምት ውስጥ ሊገቡ የሚችሉ ድርጊቶች መፈጸማቸው እሙን ነው። እንው ጭው አቆጣጠር ከ1990/ዓ/ም ጀምሮ ባለው መረጃ መሰረት የእናቶችን ሞት በ72/% እንዲቀንስ የሚያስችሉ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በማዋለድ ተግባር ላይ የሚሰማራ የሰለጠነ የሰው ኃይል ቁጥር ጨምሮአል፡፡ የጤና አገልግሎት ተቋማት ቁጥርም ከፍ ብሎአል፡፡ ቢሆንም ግን አሁንም እናቶች ልጅ በመውለድ ላይ እንዳሉ ሕይወታቸው ያልፋል፡፡ በመሆኑም አሁንም ትኩረትን በማጠናከር እናቶች የሚድኑበት መንገድ አጥብቆ ሊፈተሸ ይገባል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ ብዙ ቢሰራም አሁንም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ እናቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎቱን ማግኘት አልቻሉም ማለት ይቻላል፡፡ እንደዚህ ላሉት ቤተሰቦች ያሉበት ሁኔታ የሚለካው እንደሚከተለው ነው፡፡
…ድል አግኝቶ በመደሰት ፈንታ…በተፈጠረው ሁኔታ እንባ ይታይባቸዋል፡፡
….የሚያስቃቸውን ሳይሆን……የሚያገኙት ማጣትን ማዘንን ይሆናል፡፡
…. የወለዱትን ማቀፍ ሳይሆን …..መቅበር ነው፡፡
የእናቶች ወይንም የጨቅላዎች ሞት ለቤተሰብ ከምንም በላይ አሳዛኝ እና አሰቃቂ ነው፡፡ እናት በእርግዝና ወቅት ወይንም ስትወልድ ብትሞት በቤተሰቡ እና ባቅራቢያ በሉ ዘመድ አዝማዶች ላይ የሚወድቀው ሀዘን ጨለማው ከልክ በላይ እና አስከፊ ነው፡፡
እርግዝና ባልታቀደ ሁኔታ ከተከሰተ ውጤቱ የሚያበቃው ብዙ ጊዜ አሳዛኝ ሆኖ ነው፡፡ ደህንነቱ ያልተጠባ ጽንስ ማቋረጥ፤ በተፈጥሮው ችግር ያለበት ህጻን ፤እንዲሁም ያልታቀደ እርግዝና የአረገዘቸው እናት ሞት ከውጤቶቹ መካከል አስከፊዎቹ ናቸው። ስለሆነም በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ያለውን የጤና አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ በሚዛናዊነትና ለሁሉም ክብርን በሚሰጥ መልኩ እንዲሆን ማስተዋወቅ፤ማስፋፋት፤መፈጸም ለጤና ተቋማቱ እና ባለሙያዎቹ እንደ አንድ ግዴታ፤ ወይንም የእት ተእለት ተግባር ማድረግና እና ኃላፊነት ሊወሰድት የሚገባ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አሉ ዶ/ር ሊያ…ለእናቶችና ለጨቅላዎቻቸው የመኖር ወይንም ለመኖር የሚያስችል ጉዳይን የምንመለከትበት ስለሆነ ለእናቶች እና ጨቅላዎቻቸው ሕይወት መቀጠል ወሳኝ እና ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡
Quality… ጥራት…ሲባል የእናቶችን እና ጨቅላዎችን ሕመም፤ የአካል ጉድለት፤ እና ሞትን ለመከላከል የሚያስችል ስራን በሁሉም ስፍራ ውጤታማ የሆነ ሊመዘን የሚችል እና የተሸሻለ የጤና አገልግትን መስጠትን ያመላክታል፡፡
Equity …ሚዛናዊነት…ሲባል ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት ተገልጋዩ እንደመደበኛው የሰብአዊ መብት ባልተዛነፈ መንገድ ማግኘት መቻል አለበት ማለት ነው፡፡ እናቶችን እና ጨቅላዎቻቸውን በምንም መንገድ ማለትም ደሃ ወይንም ሀብታም  ሳይባል በዘር ወይንም በሃይማኖት ሳይለዩ ማግኘት ያለባቸውን በተሙዋላ ሁኔታ ማግኘት እንዲችሉ ሲሆን በተለይም በተለያየ መንገድ ተጎጂ የሆኑ ሰዎች አገልግሎቱን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሊያገኙ የሚችሉበ ትን ስርአት ማመቻቸት ከጤና ተቋማቱ እና ባለሙያዎቹ ይጠበቃል፡፡
Dignity …ክብር መስጠት ማለት ተገልጋዮች በየትኛውም አቅጣጫ እና ሁኔታ ላይ ቢገኙ የሚደረግላቸው የህክምና አገልግሎት ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ መሆን አለበት፡፡ እናቶች በሚወልዱበት ጊዜ ሊያገኙ የሚገባቸው ክብርና ፍቅር የተለየ ስሜትን የሚያሳድርባቸው እና ጭንቀታቸውን የሚቀንስላቸው ሲሆን ይህ ደግሞ በብዙ ጥናቶች እንደተጠቆመው የምጥ ሁኔታን በማቃለልና የተለያዩ ጉዳቶችን በመቀነስ ረገድ ጥቅም አለው ብለዋል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፡፡ የጤና ባለሙያዎች ቀረቤታና ድጋፍ እንዲሁም እናት በምጥ ተይዛ ወደ ሕክምና ተቋሙ ስትመጣ የሚደረግላት የእንኩዋን ደህና መጣሽ አቀባበል ሁኔታ ገና ከጅምሩ ደስታን የሚሰጥ ስለሆነ ወላድዋን ያጽናናታል፡፡ ምጥዋንም ያቀልላታል፡፡    
በርእስነት የተቀመጠው ጥራት… ሚዛናዊነት…ክብርን በስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት (ማስከበር…ማስፋፋት…ማሳወቅ…)በሚል መሪ ቃል የ27/ኛ አመቱ ጉባኤውን ያካሄደው የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ESOG ከጉባኤው ቀደም ብሎ ባሉት ሁለት ቀናት ለጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች የሙያ ስልጠና አካሂዶአል፡፡
ሐኪሞች በአመት ሙያቸውን በተመለከተ የተለያዩ ስልጠናዎችን መውሰዳቸው ያላቸውን እውቀት ለማጎልበት እንዲሁም በየጊዜው በምርምር ከሚደረስባቸው አዳዲስ የህክምና አገልግ ሎት ዘዴዎች እና ከሚፈጠሩ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች ጋር ትውውቅ እንዲኖራ ቸውና ተገልጋዩን በብቃት እንዲያገለግሉ የሚያስችላቸው መሆኑ የታመነበት በመሆኑ የኢትዮ ጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበርም በየአመቱ ከጉባኤው ቀደም ብሎ ስልጠናውን ሲያ ካሂድ የተወሰኑ አመታትን አስቆጥሮአል፡፡
በዘንድሮው (27ኛ) የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ጉባኤ የተለያዩ የምርምር ስራዎች ቀርበዋል፡፡ በእነዚህ ወረቀቶች እንደተጠቆመው በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ሊነሱ የሚገባቸው ነጥቦች ለባለሙያው ልምድ ልውውጥ የሚያግዙ ከመሆኑም በላይ ጉዳዩን ማወቅ የሚገባቸው እናቶች እና መላው ሕብረተሰብ ግንዛቤ ሊያገኙበት የሚችሉት ነው፡፡

Read 1912 times