Sunday, 10 March 2019 00:00

(PMTCT) ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)


         Feb /2019/ ተደርጎ በነበረው 27ኛው/ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ESOG አመታዊ ጉባኤ ከቀረቡት ሳይንሳዊ ወረቀቶች አንዱ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚገ ጥሙ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በተለይም በአንድ መስተዳድር ትኩረት ተደርጎ የተሰራ ጥናት ቀርቦአል፡፡ ጥናቱን ያቀረቡት ብርሀኑ እልፉ ፈለቀ /ሲሆኑ የተለያዩ እውነታዎ ችንም ከተለያዩ ጥናቶች በመውሰድ በወረቀ ታቸው ላይ አካተዋለ፡፡ በጥናቱ ላይ የተሳተፉት እናቶች ከአማራ ክልል ሲሆኑ ቁጥራቸውም /2615/ ነው፡፡ እድሜ ያቸውም በአማካይ እስከ 24 የሚደርስ ነበር። የብርሀኑ እልፉ ጥናት የሚከተለውን እውነታ ያሳያል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ 370‚000 ህጻናት በኤችአይቪ ቫይረስ በአዲስ መልክ ተይዘዋል፡፡
42‚000-60‚000 የሚሆኑ እርጉዝ ሴቶች በኤችአይቪ ቫይረስ መሞታቸውን የUNAIDS መረጃ ያሳያል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 68/ከመቶ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚሰራውን ስራ አጠቃቀም በሚመለከት የእናቶች ሁኔታ ሲታይ፡
ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ እራሳቸውን ለማወቅ የተመረመሩ ሴቶች ቫይረሱ በደማቸው የተገኘው 2.03/ከመቶ በሚሆኑት ላይ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡
18.7/ከመቶ የሚሆኑት እርጉዝ እናቶች ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስች ለውን አገልግሎት አግኝተዋል፡፡
ይህ ጥናት በተደረገበት የአማራ መስተዳድር ያለው ሁኔታ ሲታይ 10.3/ ከመቶ የሚሆኑት እርጉዝ እናቶች የምክር አገልግሎቱንም ምርመራውንም አድርገው በቀጣይ ሊፈጽሙት የሚገባቸውን ከሕክምና ባለሙያዎቹ ምክር አግኝተዋል፡፡
የአቶ ብርሀኑ ጥናት የተለያዩ መረጃዎችን ያካተተ እንደመሆኑ ከተለያዩ ጥናቶች ያገኙዋቸው በተከታይነት የተመዘገቡት ጠቃሚ መረጃዎችም ቀርበውበታል፡፡
ኤችአይቪ የመኖሪያ እድሜን በሰባት አመት ሊቀንስ ይችላል፡፡
ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ ለማድረግ የሚሰጠው አገልግሎት በየአመቱ በ5.1 ከመቶ እየጨመረ ይገኛል፡፡ አገልግሎቱ ግን ከ11 ከመቶ በታች መሆኑ ተጠቁ ሞአል፡፡
አንድ ጥናትን እማኝ አድርገው እንደጠቆሙትም በየአንዳንዱ የስራ ቀን የእግዝና ክትትል ከሚያደርጉት ውስጥ 326 እናቶች ለእርግዝና ክትትል እራሳቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ኤችአይቪን በሚመለከት ግን ምርመራ አያደርጉም፡፡
በአማራ ክልል ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለውን አገልግሎት ተጠቃሚ የማይሆኑ ቤተሰቦች ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ሲፈተሸ የሚከተሉት እውነታዎች ይታያሉ፡፡
የወሲብ ጉዋደኛን(ባልን) የጤና ሁኔታ በትክክል አለመረዳት፤
የእርግዝና ክትትሉን በትክክለኛው ጊዜ አለመጀመር፤
የጤና ተቋማቱ ውስጥ ለውስጥ ሕሙማንን የሚቀባበሉበት አሰራር referral ያለመኖር፤
ከጤና ባለሙያዎች ጋር ጥሩ ቅርርብ ያለመኖር፤
ሕክምናውን ለማገኘት የሚቆዩበት ጊዜ(የተራዘመ) …ወዘተ የመሳሰሉት ምክንያቶች ተጠቃሾች ናቸው።
ኤችአይቪ ቫይረስ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለውን አገልግሎት በመጠቀም ረገድ በከተሞች ውስጥ 68.1/ከመቶ ሲሆን በገጠር ያሉ እናቶች አጠቃቀም ግን በ33/ በመቶ ከፍ ይላል። የዚህ ምክንያቱ በከተሞች ውስጥ ያሉ እናቶች ብዙውን ጊዜ የጤና ተቋሙ በአካባቢያ ቸው የሚገኝ በመሆኑ ልጆቻቸውን ለማትረፍ ሲሉ ሊጠቀሙ የሚገባውን አገልግሎት አድሎና መገለልን በመፍራት ስለማያደርጉት ነው። ኤችአይቪን በሚመለከት የሚያደርጉት ምርመራም ከአካባቢያቸው እርቀው መሆኑ ሌላው ተከታታይነት ላለው አገልግሎት ችግር የሚፈጥር መሆኑ እሙን ነው።
አቶ ብርሀኑ በመደምደሚያው የጠቀሱት፡-
ሁሉም የህክምና ተቋም የውስጥ referral የአሰራር ዘዴ በመቀየስ ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላለፍ የሚያስችለውን አሰራር ማጠንከር ይገባዋል፡፡
ኤችአይቪ ከእናት ወደልጅ እንዳይተላላፍ የሚሰራው ስራ ፕሮግራም በእቅዱ ፤በአፈጻ ጸሙና በመመዘኛው ላይ ህብረተሰቡን ያሳተፈ እና ሙሉ እውቅና ያገኘ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ከብርሀኑ እልፉ ፈለቀ ጥናት ወጣ ብለን ኤችአይቪን በሚመለከት በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ኤችአይቪ በኢትዮጵያ ያለውን ስርጭት ለመግታት የኢትዮጵያ መነግስት ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ብሄራዊ እቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ እቅድም የኤችአይቪን ስርጭት በመግታቱ ረገድ አለም አቀፉን አቅጣጫ እና ምርጥ ተግባራትን የሚያ ካትት ሲሆን እቅዱም ለአምስት አመት ማለትም እንደውጭው አቆጣጠር ከ(2015 -2020) ድረስ ተግባር ላይ የሚውል ነው፡፡ ኤችአይቪን በሚመለከት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውቀት ምን ይመስላል ? ዝናባሌና ባህርይን በሚመለከትስ ምን እውነታ አለ? የሚለውን ለማወቅ የሚያስችል ጥናት ነው በ2016/ DHS ይፋ የሆነው፡፡
እንደውጭው አቆጣጠር በ2016/ በኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ማእከላዊ እስታትስቲክስ አማካኘነት በተሰራው የስነ ህዝብና የጤና ቅኝት ማለትም የ DHS (Demographic health survey) ዳሰሳ እንደሚያሳየው ኤችአይቪን በሚመለከት የተለያዩ እውቀት ፤ግንዛቤና ባህርይ በኢትዮጵያ መኖሩን ያሳያል። ወደ ዝርዝሩ ከመግባት በፊት ጠቅለል ብሎ ለንባብ የተቀመጠው መረጃ እንደሚከተለው ይነበባል፡፡
በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ እርጉዝ እናቶች 69/ከመቶ የሚደርስ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ያስረዳል ይላል የDHS/ ጥናት፡፡
ስለ ኤችአይቪ መተላለፍና መከላከል ያለው እውቀትን በሚመለከት እድሜያቸው ከ15-49/ የሚሆናቸው ሴቶች እና ወደ 38/ ከመቶ የሚሆኑ እድሜያቸውም ከ15-49 የሚሆናቸው ወንዶች ኤችአይቪ እንዴት እንደሚተላለፍና ስለመከላከያውም ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡
ኤችአይቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዴት እንደሚተላለፍ 57/ከመቶ ሴቶችና 55 ከመቶ ወንዶች በእርግዝና፤ በወሊድ እና በጡት ማጥባት ወቅት መሆኑን ያውቃሉ።
አድሎና መገለልን በሚመለከት 48/በመቶ የሚሆኑ ሴቶች እና 35 ከመቶ የሚሆኑ ወንዶች የኤችአይቪ ቫይረስ ያለባቸው ልጆች ቫይረሱ ከሌለባቸው ልጆች ጋር አብረው በትምህርት ገበታ መቀመጥ የለባቸውም ሲሉ የቀረበላቸውን ጥያቄ መልሰዋል፡፡ በሌላም በኩል 55 ከመቶ ሴቶች እና 47 ከመቶ የሚሆኑ ወንዶች የኤችአይቪ ቫይረስ ካለባቸው ነጋዴዎች ላይ አትክልትና ፍራ ፍሬን የመሳሰ ሉትን ሸቀጦች እንደማይገዙ ተናግረዋል፡፡
የወሲብ ጉዋደኛን በሚመለከት ከ1/ከመቶ በታች የሆኑ ሴቶችና ወደ 3/ከመቶ የሚሆኑ ወንዶች ከአንድ በላይ ከሆኑ የወሲብ ጉዋደኞች ጋር ላለፈው አንድ አመት ያህል እንደሚገናኙ ተናግ ረዋል፡፡
ኤችአይቪን በሚመለከት የጤና ምርመራ ለማድረግ 69/ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና 84/ከመቶ የሚሆኑ ወንዶች የት ሄደው ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡ 40 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና 43/ከመቶ የሚሆኑት ወንዶች ደግሞ ተመርምረው እንደማያውቁና እራሳቸውንም እንደማያውቁ መልስ ሰጥተዋል፡፡ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ማለትም ቅኝት ከመደረጉ በፊት 20/ከመቶ የሚሆኑ ሴቶች እና 19/ከመቶ የሚሆኑ ወንዶች ተመርምረው እራሳቸውን ማወቃ ቸውን አስረድተዋል።
Know Your Status--ኤችአይቪ ቫይረስን በሚመለከት አስቀድሞ (እራስን ማወቅ ተገቢ ነው።) የሰላሳኛው የአለም ኤይድስ ቀን መሪ ቃል።

Read 7646 times