Print this page
Saturday, 13 April 2019 13:23

ስለወር አበባ መቋረጥ (Menopause) መታ ወቅ ያለባቸው ነገሮች

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(4 votes)

 በተለያዩ መረጃዎች እንደተመዘገበው ከሆነ የወር አበባ የሚቋረጠው ሴቶች በእድሜያቸው ከ45-55 አመት ሲደርሱ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ሴቶች እድሜያቸው ከ30-40 በሚደርስበት ጊዜም የወር አበባ ሊቋረጥ እንደሚችል ባለሙያዎች ይመሰክራሉ፡፡
Menopause እንዴት ይገለጻል?
አንዲት ሴት በተከታታይ ለ12/ወራት ማለትም ለአንድ አመት የወር አበባዋን ማየት ካቆመች የወር አበባ መቋረጥ Menopause ከሚባለው ደረጃ ደርሳለች ማለት ነው፡፡ ይህ የሚሆነውም የሴትዋ የስነተዋልዶ አካል የወር አበባ እንዲመረት የሚያስችለውን ተፈጥሮአዊ አቅም ሲያጣ ነው፡፡
የወር አበባ መቋረጥ ሂደት በድንገት የሚከሰት አይደለም::  ቀስ በቀስ የሚከሰት ተፈጥሮ አዊ ጉዳይ ነው:: ይህ ከወር አበባ መቋረጥ በፊት ያለው ጊዜ ለሴቶች ለየት ያለ ሁኔ ታን የሚመለከቱበት ጊዜ ነው፡፡
በአማካይ እድሜያቸው 51/አመት የደረሱ ሴቶች menopause የሚገጥማቸው ሲሆን ነገር ግን አንዳንዶች በፍጥነት በ30/አመት አንዳንዶች ደግሞ ዘግይተው በ60/አመታቸው ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማወቅ የሚያስችል የጥናት ውጤት ባይመዘገበም ቀደም ብሎ የሚመጣባቸው አንዳንድ ምክንያቶች ግነ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የወር አበባ መምጣት የጀመረበትን ጊዜ እንደምክንያት ለመውሰድ የሚሞከር ቢሆንም ነገር ግን የመምጫው ጊዜ የመቋረጫውን ጊዜ እንደማያመላክት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
የወር አበባ መቋረጥ menopause ምልክቶች ውስጥ የብልት መድማት፤ ሰውነትን ሙቀት መሰማት፤ ላብ ማላብ፤ የባህርይ መለዋወጥ፤ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
የወር አበባ መቋረጥን ተከትሎ የሚመጣ የጤና ችግር ይኖራል፡፡ ለምሳሌም የአጥንት መሳሳትና የልብ በሽታ የሚገለጹ ናቸው፡፡ የወር አበባን ተከትለው ለሚመጡ ሕመሞች በህክምናው እርዳታ ሊደረግ የሚችል ሲሆን ሴቶቹ የሚኖራቸውን የተዛባ ስሜት እና ምቾት የማጣት ሁኔታ ሊያስታግስ የሚችል ነው፡፡
የወር አበባ ሊቋረጥ ሲያስብ አስቀድሞ ባለው ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች በሁሉም ሴቶች ላይ አንድ አይነት አይደሉም፡፡ አንዳንድ ሴቶች ጥቂት ወይንም ምንም ምልክት ላያዩ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በአካላቸው ወይንም በስነልቡናቸው ላይ ጫና ሊያሳድር የሚችል የጤና መዛባት ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ምልክቶቹም በቋሚነት እንደህመም ላይታዩ እና መጣ ሄድ ሊሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ ይህም ቢሆን በሁሉም ሴቶች ላይ የሚታ አለመሆኑን ልብ ማለት ይባል፡፡ አንዳንዶች በተደጋጋሚ ችግሮቹን ሊያስተውሉ ይችላሉ፡፡ የወር አበባ መቋረጥ ሂደቱን የሚጀምረው አስቀድመው ባሉ አመታት ሲሆን ሴትየዋ የወር አበባዋ መቋረጡን የምታረጋግጠው ለአንድ አመት ያህል ማየት ካቆመች ነው፡፡
ወቅቱን ያልጠበቀ የደም መፍሰስ፤
ሴቶች የወር አበባቸው ሲቆም ከብልታቸው የተዛባ የደም መፍሰስ ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ በሚመጣባቸው ወቅት ውስን የሆነ የደም መፍሰስ ሊገጥማቸው የሚችል ሲሆን አንዳንዶች ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ መጠኑ በርከት ያለ የደም መፍሰስ ሊያኖራቸው ይችላል፡፡ የወር አበባ ጊዜውን ሳይ ጠብቅ በአጭር ጊዜ እየተመለሰ ሊታይ አለዚያም በጣም በተራራቀ ሱኔታ ሊመጣ ይችላል::  ስለዚህ የወር አበባ በቅርቡ የሚቋረጥ ከሆነ ቀድሞ እንደነበረው በትክክል በተ ወሰነ ጊዜ የማየቱ ሁኔታ እንደሴቶቹ ተፈጥሮአዊ ሁኔታ ይለያያል፡፡ ይህ የወር አበባ መዛባት እስከመቋረጫው ወቅት ለተወሰኑ ወራት ሊቀጥል ይችላል፡፡ ለተወሰኑ አመታት የወር አበባ መምጫው ወቅትም በተለመደው ወይንም መሆን እንደሚገባው በተወሰነ ጊዜ ሳይሆን እንደፈለገው አጠር ወይንም ረዘም ባለ ጊዜ ሊሆን ይችላል፡፡ በእርግጥ የወር አበባ መምጫው ወቅት ሲዛባ ሴትየዋ ወደ menopause የወር አበባ መቋረጫው ወቅት እየተዳረሰች ነው ወይንስ በሌላ ምክንያት የሚለውን ለማወቅ የጤና ባለሙያን ማማከር ተገቢ ነው፡፡
የወር አበባ በመደበኛው ወቅት መምጣቱን ሲያቋርጥ ልጅ የመውለድ ሁኔታንም ሊያዛባው እንደሚችል መገመት ይገባል፡፡ በእርግጥ አንዳንዶች ወደ menopause እየደረሱ ባሉበት እና የወር አበባም ትክክለኛውን ጊዜ ሳይጠበቅ በመሀከል ወደትክክለኛው መቋረጥ ከመድረሳቸው በፊት እርግዝና ሊከሰት የሚችልበት አጋጣሚ ይስተዋላል፡፡
ሙቀትና - ላብ፤
ብዙውን ጊዜ ሴቶች የሚሰማቸው ሙቀት ወይንም ወበቅ ስሜት በመላ ሰውነታቸው ሲሆን ለእይታ የሚበቃው ግን በእራስና በደረት አካባቢ ነው፡፡ ይህ የሚከሰተው በድንገት በማንኛውም ሰአት ሲሆን ሙቀቱ ከተሰማ በሁዋላ ላብ ይከተለዋል፡፡ ስሜቱ የሚቆየ ውም ከ30/ሴኮንድ እስከተወሰነ ደቂቃ ሊሆን ይችላል፡፡ menopause እድሜ ላይ በደረሱ ሴቶች ላይ የሚታየው ድንገተኛ ሙቀትና ላብ ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም ነገር ግን ኢስትሮጂን የተባለው ንጥረ ነገር መጠኑ በመቀነሱ የሚፈጠር የሆርሞን ችግር ያስከተለው እንደሚሆን አይካድም፡፡   
ወበቅ እና ላብ በአንዳንድ ሴቶች ማለትም እስከ 40% በሚሆኑት በትክክል የወር አበባቸውን እያዩ ባሉበት በ40/ዎቹ አመታቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ወቅት ወደ መቋረጡ ሂደት እየተጠጉ መሆኑን ሊያመላክት ይችላል፡፡
ወደ 80% የሚሆኑ ሴቶች ለአምስት አመት ያህል ወበቅና ላብ ሲሰማቸው ቆይቶ ከዚያ በሁዋላ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
አንዳንዶች ማለትም ወደ 10% የሚሆኑ ሴቶች ወበቅና ላብ ሲሰማቸው ለአስር አመት ያህል ሊቆዩና ከዚያ በሁዋላ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የወር አበባ በመቋረጡ ምክንያት የሚከሰተው ወበቅና ላብ በዚህ ጊዜ ጀምሮ በዚህ ጊዜ ያበቃል የሚባል ሳይሆን እንደሴቶቹ ተፈጥሮአዊ ሁኔታ የሚለያይ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ ይህ ሙቀትና ላብ በተለይም በመኝታ ጊዜ መጠኑንና ምልልሱን ከቀኑ ይበልጥ ሰፋ ሊያደርገው እንደሚችል አንዳንዶች ይመሰክራሉ፡፡
ላብ በሌሊት ወይንም በመኝታ ወቅት፤
የወር አበባ መቋረጥ የገጠማቸው ሴቶች በመኝታ ወቅት አየር እንደልብ የሚዘዋወርበት ክፍል መተኛት እንዲሁም አለባበስን ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል::  መኝታ የሚጋሩዋ ቸውን ሰዎች ላለመረበሽ ወይንም ላለማስቸገር አስቀድሞ ያሉበትን ሁኔታ ማስረዳት እና በመኝታው ወቅት መፍትሔ የሚሉትን ሁኔታ ማመቻቸትም ጥሩ ነው፡፡ የወር አበባዋ የተቋረጠባት ሴት የሚከሰትባት ወበቅና ላብ እንቅልፍ ሊከለክላት እና መኝታ ላይ በመገላበጥ ሌሊቱን መጨረስ ሊገጥማት ይችላል፡፡ በዚህም የተነሳ የቀን ውሎዋንም የተጫጫነው ሊያደርገው ይችላል፡፡ ስለዚህ መኝታን በተገቢው መንገድ ማድረግ ይጠበቃል፡፡
በብልት ላይ የሚታዩ ስሜቶች፤
በወር አበባ መቋረጥ ወቅት የኢስትሮጂን መጠን ስለሚቀንስ የብልት የውስጥ ክፍል መሳሳት እና መድረቅ እንዲሁም የመሳብ አቅሙን የመቀንስ እና የማሳከክ ወይንም ወሲብ በሚፈጽሙበት ወቅት ሕመም ሊኖረው ይችላል፡፡ ስለዚህ ህመሙ ተባብሶ ወደ infection ወይንም መመረዝ እንዳያመራ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡


Read 10585 times