Saturday, 24 August 2019 14:21

ወሲባዊ ግንኙነት ከፈጸሙ በሁዋላ መድማት ትክክል ነውን?

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(33 votes)


          Jennifer Huizen የተባሉ ምሁር እንደሚያስረዱት አንዲት ሴትና አንድ ወንድ የግብረስጋ ግንኙነት ከፈጸሙ በሁዋላ በሴቶች ብልት ላይ የመድማት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚከሰተው የደም መፍሰስ ባልተጠበቀ ወይንም ጥንቃቄ በጎደለው መንገድ በሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ምክንያት እርግዝና እንዳይፈጠር ለማድረግ ሰውት በሚያደርገው መኮማተር መፍታታት ምክንያት የሚከሰት መድማት ሲሆን ይህ ሁኔታ በሳይንሳዊ ቃሉ postcoital ይባላል:: በሚኖረው የግንኙነት ወቅት በሚፈጠረው የሰውነት መኮማተር እና መፍታታት ምክንያት ሊከሰት ይችላል:: በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ የደም መከሰት ለምን ይሆናል ለሚለው ጥያቄ የተለያዩ መልሶች ይኖራሉ:: በመጀመሪያ ደረጃ ከ0.7-9/% በሚሆን ግምት ከግብረስጋ ግንኙነት በሁዋላ መድማት ሊኖር ይችላል ተብሎ የሚገመተው ሴትዋ የወር አበባ የምታይበት ጊዜ ላይ ልትሆን ትችላለች የሚለው ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ምክንያት ይሆናሉ የተባሉት ሚከተሉት ናቸው፤፤
ከወሲብ በሁዋላ የሚኖረው መድማት ምክንያቶች፤
የወር አበባ የመምጫው ወቅት ከሆነ በግንኙነት ጊዜ ደም ሊፈስ ይችላል፡፡
የሚፈሰው ደም የወር አበባን መምጫ ተንተርሶ ከሆነ ግን እንደ postcoital አይቆጠርም፡፡
ማንኛዋም የግብረስጋ ግንኙነት የምትፈጽም ሴት postcoital ሊሆን ይችላል ተብሎ በሚገመተው መንገድ የደም መፍሰስ ሊኖራት ይችላል፡፡
የደም መፍሰሱ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?
ጉዳት፤
በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት በሰውነት ላይ የመቆረጥ ወይንም የመፈጋፈግ ሁኔታ ካለ ስስ የሆነው የሴት ብልት በመጠኑም ቢሆን ሊከፈትና የመድማት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡
ህጻናት በሚወለዱበት ጊዜ የሚፈጠሩ የብልት መወጠር ወይንም መሰንጠቅ ሊኖር ስለሚችል በዚያም ምክንያት በቀላሉ በወሲብ ግንኙነት ጊዜ መድማት ሊኖር ይችላል፡፡
ምናልባትም የወሲብ ግንኙነቱ ለሴትዋ የመጀመሪያ ጊዜ ማለትም በአማርኛው ድንግልናው ስለሚወጠርና ስለሚቀደድ የመድማት ሁኔታ ሊኖርና ይህም ከአንድ እስከ ሁለት ቀን ድረስ ሊቆይ የሚችል ነው፡፡
የሴት ብልት መድረቅ፤
የሴት ብልት መድረቅ ከግብረስጋ ግንኙነት በሁዋላ መድማትን ከሚያስከትሉ ችግሮች መካከል ነው:: ምክንያቱም ቆዳው ደረቅ ከሆነ በግንኙነት ጊዜ በሚኖረው ጫና በቀላሉ መሰነጣጠቅና መድማት ስለሚጀምር ነው፡፡
የሴት ብልት መድረቅ ምክንያቶች፤
ከወር አበባ ማረጥ ጋር በተያያዘ ልስላሴን የሚፈጥር ፈሳሽ አለመኖር፤ የብልት ውስጥ ክፍል ሰውነት መሳሳት እና የመሳሳብ ችግር መፈጠር፤
የማህጸን መጎዳት ወይንም ከነጭርሱ በተለያየ ምክንያት መወገድ በሰውነት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለውን ኢስትሮጂን የተባለውን ንጥረ ነገር እንዳይፈጠር ስለሚያደርግ፤
ልጅ መውለድ እና ጡት ማጥባት፤ በእርግዝና ጊዜ ሴትየዋ ያላት የኢስትሮጂን መጠን መጠኑ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ልክ ህጻኑ እንደተወለደ መጠኑ በድንገት ዝቅ ሊል ይችላል፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ ኢስትሮጂን የጡት ወተትን በማምረት ተግባርም ስለሚገባ ነው፡፡  
በአንዳንድ ሕክምናዎች ምክንያት የሚሰጡ መድሀኒቶች ከኢስትሮጂን ጋር ላይጣጣሙ ወይንም ሰውነትን ሊያደርቁ ይችላሉ፡፡ የሴት ብልት ድርቀት ሊከሰት ከሚችልባቸው ምክንያቶችም ኢስትሮጂንን የሚረብሹ መድሀኒቶች ሲወሰድ ወይንም እንደጉንፋን፤ ሳል፤ ለመሳሰሉት ሕመሞች በሚሰጡ መድሀኒቶች ሳቢያ ሊሆን ይችላል፡፡  
አንዳንድ ኬሚካሎች የሰውነት ፈሳሽን በማይታወቅ መንገድ ሊያደርቁ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ልብስ ማጠቢያ ላውንደሪ ቤቶች የሚጠቀሙባቸው መድሀኒቶች፤ መጥፎም ባይሆን ግን የራሳቸው ጠረን ያላቸው ቅባቶች ለሴት ልጅ ብልት መድረቅ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
በጣም ኃይል ባለው ወይንም በቧንቧ ተገፍቶ በሚወረወር ውሀ የሴት ልጅ ብልት ሲታጠብ ሊጎዳ ወይንም ድርቀት ሊከተል ይችላል፡፡
ለወሲብ በመንፈስ ዝግጁ ሳይሆኑ ግንኙነት መፈጸም ሌላው ችግር ነው፡፡ አንዲት ሴት እራስዋን ለግንኙነት ዝግጁ ስታደርግ ብልት በተፈጥሮው ማለስለሻ ፈሳሽ ይለቃል፡፡ ይህም ድርቀትን ስለሚከላከል በግንኙነት ጊዜ ሊፈጠር የሚችለውን መፈጋፈግ ካለጉዳት እንዲያልቅ ይረዳል፡፡ ሴትየዋ ምንም ፍላጎት ወይንም ስሜት ከሌላት ግን ሰውነትዋ ስለሚደርቅ በቀላሉ የመድማት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡  
Jennifer Huizen እንደሚሉት ማንኛውም አይነት ኢንፌክሽን የሴት ልጅ ብልትን እንዲቆስል እና ተጎጂ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል፡፡ እነዚህ ኢንፌክሽንን ሊያመጡ የሚችሉ ችግሮች ብዙ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል በወሲብ ምክንያት የሚተላለፉ ሕመሞች ማለትም እንደ ጨብጥ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ለሴቶች ብልት መደረቅ ምክንያት የሚሆኑ የተለያዩ ነገሮች በባለሙያዋ ተጠቅሶአል፡፡
አንዳንድ ሴቶች በተፈጥሮ የሰውነት ወይንም የውስጥ አካላቸው የተለየ ቅርጽ ይዞ ይስተዋላል:: ይህም የሚያደርጉትን ግንኙነት ስቃይ የተሞላበት ሊያደርገው ከመቻሉም በላይ የመሰንጠቅ ወይም የመላላጥ ነገር ሊያስከትል ስለሚችል መድማት ሊኖራቸው ይችላል፡፡
አንዳንድ ሕመሞች ማለትም ትክክል ያልሆነ የደም መፍሰስ ወይንም መቆም  ያሏቸው ሴቶች የመድማት ሁኔታውን ሊያባብሱት ይችላሉ፡፡ በተለይም የደም ማቅጠኛ መድሀ ኒት በመውሰድ ላይ ያሉ ሴቶች በግንኙነት ጊዜ መድማት ይኖራቸዋል፡፡
በስነተዋልዶ አካል ላይ የሚታይ የካንሰር ሕመም የብልት የውስጥ ክፍልን እንዲሁም የሆርሞን መጠንን ከተፈጥሮ ውጭ ሊያደርገው መጠኑንም ሆነ ብቃቱን ሊለውጠው ይችላል፡፡ በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚከሰት መድማት በተለይም Postcoital bleeding የሚባለው የማህጸን በር ወይንም የማህጸን ካንሰር መኖሩን አመላካች ሊሆን ይችላል፡፡  
ባጠቃላይም Jennifer Huizen እንደሚመክሩት በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ የሚከሰተውን መድማት ለመከላከል፤
ሰውነት እንዳይደርቅ መከላከል፡፡ ይህም ውሀን በመጠጣት ወይም በግንኙነት ወቅት የሚወሰዱ ማለስለሻዎችን መጠቀም ጥሩ ነው፡፡
ስሜት በሌለው ሁኔታ ወይንም ፍላጎት ሳይኖር በድንገት ወሲብ መፈጸምን ማስወገድ፡፡
አንዳንድ ሽቶዎች ወይንም ዶደራንቶችን በብልት ላይ አለመጠቀም፡፡
በግንኙነት ጊዜ ኮንዶምን መጠቀም፡፡
የህክምና እርዳታን ከሕምና ባለሙያዎች ማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡ 

Read 28737 times