Saturday, 16 June 2012 11:42

በዓሉ የማነው? የህፃናት ቀን ዛሬ ይከበራል

Written by  ሠላም ገረመው
Rate this item
(0 votes)

ባልና ሚስቱ አቶ ጀማል ሁሴን እና ወ/ሮ ዘይቱና ሐጂ፤  በወራቤ ከተማ የመሰናዶ ት/ቤት  መምህራን ሲሆኑ መምህርት ዘይቱ፤ የዞኑ መምህራን ማህበር ሊቀመንበርም ናቸው፡፡ ጥንዶቹ ወላጅ አልባ የሆነችውን የ8 አመት ህፃን ዛሊካን፤ ከባሌ አዳባ አካባቢ ያመጡዋት ሊያሳድጉዋትና የ11 ወር ህፃን ልጃቸውንም እንድትጠብቅላቸው ነበር፡፡ ህፃንዋ ግን በስራ ጫና ከመሰቃየትዋም ባሻገር አሳዳጊዎችዋ ለንፅህናዋም ሆነ ለጤንነትዋ መጠበቅ አለመጨነቃቸውን ጎረቤቶቻቸው ይመሰክራሉ፡፡
በቅርቡ ህፃንዋን “የድስት ጥራጊ በላሽ” በሚል የወነጀልዋት አሳዳጊዎቹዋ፤ሁለት እጇቹዋን በእሳት በማቃጠል እና ጀርባዋን በመግረፍ ከፍተኛ ስቃይ እንዳደረሱባት ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ በደረሰባት ድብደባ ሰውነትዋ የቆሳሰለው ህፃን ዛሊካን “ ለሁለት ሳምንት ህክምና ባለማግኘቱዋ ቁስልዋ መሽተት መጀመሩን ያወቁት የአካባቢው ነዋሪዎች” ጉዳዩን ለፖሊስ ያመለክታሉ፡፡ ከሰው እንዳትገናኝ አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎባት የነበረችውን ህፃን በማስወጣትም አንድ የፖሊስ አባል ቤት እንድትጠለል ተደርጎ  ምርመራውን ም/ኢንስፔክተር አብሳር የሱፍ እንዲያደርግ ተወስኖ ነበር፡፡
አቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር ተባብሮ ሲሰራ እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች” የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት በህግ ጥላ ስር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው የነበሩት ወ/ሮ ዘይቱና ሐጂን ያለምንም ዋስ እንዲለቀቁ አድርገዋል፡፡ ይሄም ሳያንስ ጉዳዩን የያዘው መርማሪ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲዛወር መደረጉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ህፃኗ የደረሰባትን ጉዳት በተመለከተ ለፖሊስና ለአቃቤ ህግ ቃልዋን እንደሰጠች የጠቆሙት ምንጮቻችን”ሆኖም ክሱ እንዲስተካከል ግፊት እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ህፃንዋ “አሳዳጊዎቼ አቃጥለውኝ ሳይሆን ከሠል ላይ ተደናቅፌ ወድቄ ነው” የሚል ቃል ህፃኗ እንድትሰጥ ለማግባባት አሳዳጊዎቹ ልብስ በመግዛትና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በማቅረብ ሲደልሉዋት እንደነበር  ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ስለጉዳዩ የተጠየቁት የዞኑ የሴቶች” ህፃናትና ወጣቶች ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ነጂባ ሱልጣን በወቅቱ እንዳልነበሩና ጉዳዩን ከአካባቢው ሰዎች እንደሰሙ ገልፀው”  ተጠርጣሪዋ በህግ ጥላ ስር መቆየቱዋን ይናገራሉ፡፡
አሳዳጊዎቿ በሰጡት ቃል ህፃኑዋ እንደማንኛውም ህፃን ስትጫወት ከሠል ላይ ወድቃ ነው የተቃጠለችው ማለታቸውን የጠቀሱት ሃላፊዋ፣ ህፃኗ ጀርባ ላይ ግን የግርፋት ጠባሳ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን በመጠቆምም የተጠርጣሪዋን መፈታት በተመለከተ ግን  በህግ የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ አስተያየት መስጠት ያስቸግራል ብለዋል፡፡
መጀመሪያ ጥቃቱ መፈፀሙ በህክምና መረጋገጥ እንዳለበት የተናገሩት የከተማው አቃቤ ህግ አቶ አሰፋ ጥላሁን በበኩላቸው፣ሌላው በሚሠራው ምርመራ ላይ ገብቼ አላንቦራጭቅም ብለዋል፡፡ መዝገቡ በእጃቸው እንደሌለና እንዳልመረመሩት የገለፁት አቃቤህጉ፤ ወሬውን ያቀበላችሁ መርማሪ ይንገራችሁ ብለዋል፡፡
የዞኑ የፍትህ መምሪያ ሃላፊ አቶ ቃሲም ባዶ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው፣“መልስ ለመስጠት እዚህ መምጣት አለባችሁ ፣ ማንነታችሁን አላውቅም” በማለት ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል፡
በተጠርጣሪዋ ላይ ምርመራውን ሲያካሂድ የነበረውና ወደ ሌላ ቦታ የተቀየረው ም/ኢንስፔክተር አብሳር የሱፍን አነጋግረናቸው በሰጡት ምላሽ “ለሚዲያ መረጃ ሳልሰጥ ሠጥተሃል ተብዬአለሁ፣ስለዚህ እራሴን መጠበቅ ስላለብኝ ምንም መናገር አልችልም ብሏል፡፡
በአሁኑ ሰአት ተጐጂዋ ህፃን ያለችበት እንደማይታወቅ የገለፁ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ህፃንዋ ፍትህ እንድታገኝ ለሚመለከተው አካል አሳውቁልን ሲሉ ዝግጅት ክፍሉን ተማፅነዋል፡፡  የ11 አመትዋን እንዳይሽን ደግሞ ከጐንደር ወደ ደንግላ ያመጣቻት የእናቷ አክስት ነበረች፡፡ አንድ ልጅ ብቻ ያላት የእናቷ አክስት ለለቅሶ ጐንደር ሄዳ በነበረበት ጊዜ ነው እንዳይሽን አስተምራታለሁ፣ለልጄም እህት ትሆናታለች በሚል ከወላጆችዋ ቤት የወሰደቻት፡፡ ህፃኗ ከመጣች አንድ አመት ከስምንት ወር ቢሆናትም እስካሁን ት/ቤት አልገባችም፡፡ የ14 ዓመትዋ የአሳዳጊዋ ልጅ ት/ቤት ውላ ስትመለስ ከእኩዮቿ ጋር ትጫወታለች፡፡ እንይሽ ግን ከትምህርቱም ከጨዋታውም ተበድላለች፡፡ የቤቱን ስራ የምትሰራው እቺው ህፃን ስትሆን የቤቱን የጣውላ ወለል ሰም ቀብታ በጉልበቷ እንድታሽ ታደርጋታለች - አሳዳጊዋ፡፡ የህፃንዋ መከራ በጉልበት ስራ ብቻ ቢወሰንላት በማን ዕድልዋ ነበር፡፡
ባለፈው ሳምንት የአሳዳጊዋን ልጅ የተረፈ የምሳ እቃ ምግብ ጠርገሽ በላሽ በሚል የተወነጀለችው እንይሽ፣ የተወሰነባት ቅጣት ለሦስት ቀን በርበሬ መታጠን ነው - በእናቷ አክስት፡፡ ይሄ ደግሞ ህፃኑዋ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ ራስዋን ጥላ ትወድቃለች፡፡ ጉዳዩን የተመለከተችው የግቢው ተከራይ ምናየሁ ባንቺ፣ለፖሊስ በመጠቆምዋ የእንይሽ አሳዳጊ በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ከሁሉም የሚያስገርመው ግን ይሄን በደል በ11 ዓመትዋ ህፃን ላይ የፈፀመችው አሳዳጊ የወረዳው የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ መሆኑዋ ነው፡፡ “ህፃኗን የቀጣሁዋት ከጥፋትዋ እንድትማር ብዬ እንጂ ልጐዳት አስቤ አይደለም” ስትል ተጠርጣሪዋ ለፖሊስ ቃሏን እንደሰጠች የገለፀችው ተከራይዋ ምናየሁ፣አሳዳጊዋ ህፃኗን በየቀኑ ትገርፋት እንደነበር ገልፃለች፡፡ “እንኩዋን ህፃን አዋቂ የማይችለውን በርበሬ ማጠን ከግድያ የሚለይ አይደለም” ብላለች ተከራይዋ፡፡ አሁን ህፃን እንዳይሽን ወላጅ እናቷ እንደወሰደቻትና ህክምና እየተከታተለች  እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፡፡
የ13 አመቷን ህፃን ኤልሻዳይ ለአሳዳጊ የሰጠቻት እናት የጐረቤቴን ምክር ሰምታ መሆኑን ትናገራለች - ሁለት ልጆች የወለደችለት ባሏ ስለሞተና ለብቻዋ ማሳደግ ባለመቻሏ፡፡
የጐረቤቷ እናት የሆኑት ባልቴት በመልካም ባህርያቸው የሚታወቁ ስለሆነ በልጅዋ አንድም ክፉ ነገር ያደርጋሉ ብላ ፈፅሞ ገምታ አታውቅም፡፡ የሰው ፊት ከምታይ ከልጅ ልጆቼ ጋር ላሳድጋት ብለው ነበር የወሰዷት - ህፃን ኤልሻዳይን፡፡ ባልቴትዋ ግን ህፃኗን ትምህርት ቤት ሳይልኩ የልጆቻቸውን ልጆች ከማሳዘላቸው በተጨማሪ የቤት ውስጥ ስራዎችንም ያሰሩዋት ነበር፡፡
በየወሩ ልጇን የምታየው እናት  ልጇ ልብሷ ንፁህ በመሆኑ ይሄንን አልገመተችም፡፡ በየወሩም ባልቴትዋቷ አንድ መቶ ሃምሳ ብር ስለሚሰጧት አመስግና ትቀበላለች እንጂ አትጠይቅም፡፡ አንድ ቀን ግን ኤልሻዳይ እጇን ቢላ ይቆርጣትና በጨርቅ ጠቅልላ እናቷ ጋ ትሄዳለች፡፡ እናት ደንግጣ ምን እንደሆነች ትጠይቃታለች “ስራ ስሠራ ቢላ ቆረጠኝ” ስትል ትመልሳለች- ህፃኑዋ፡፡ የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም ትላለች - እናት፡፡ ከዚህም በላይ ክው እንድትል ያደረጋት ግን የልጅዋ ያልተጠበቀ ንግግር ነበር፡፡ “እሳቸው ጋር የወሰድሽኝ ስራ እንድሠራ አይደል፣ ላንቺስ ይከፍሉሽ የለም” በማለት ታፋጥጣታለች - እናቷን፡፡ በዚህ ሰበብ ከአሳዳጊዋ ባልቴት ጋር ተጣልታ ልጇን ራስዋ  እያሳደገች ትገኛለች፡፡ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ ደረጀ ፈቅ ይበሉ፣ ልጆችን ለአሳዳጊ መስጠትን በተመለከተ ህጉ ምን እንደሚል ሲናገሩ “ጉዲፈቻ በሁለት አይነት መንገድ ነው የሚከናወነው፣ በአገር ውስጥ የሚከናወንና ከአገር ውጪ የሚደረግ ነው፡፡
ይህም አቅም የሌላቸው በተሻለ መንገድ እንዲያድግ ወይም ወላጅ የሌለው ልጅ ቋሚ ወላጅ እንዲያገኝ የሚያስችል ሲሆን አሳዳጊዎች ልጆችን እንደ እራሳቸው ልጅ በማየት የመማር፣ የማደግ እንዲሁም ለሌሎች ህፃናት የተሰጡ መብቶች ሁሉ በእኩል ደረጃ ይጠብቁለታል ማለት ነው፡፡
በጉዲፈቻና በተፈጥሮ ልጅ መካከል ምንም ልዩነት አይፈጠርም፡፡ የጉዲፈቻ ልጆች በልዩነት አይያዙም” ስለዚህ ለችግርም ሆነ ለጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ ናቸው ተብሎ አይታሰብም፡፡ ለእነዚህ ችግሮች ይጋለጣሉ ተብሎ የሚገመቱት በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ ናቸው፡፡ ህገወጥ የህፃናት ዝውውር በተለይ ከደቡብ አካባቢ ያመጡና የሽመናና የተለያዩ የጉልበት ስራዎች ያሠሯቸዋል፡፡ ጉዲፈቻ ሲሰጥ ዝም ብሎ አይሰጥም፣ አቅም አለው ተብሎ ፍ/ቤቱ አጣርቶ እንጂ ዝም ብሎ አይደለም፡፡ በጉዲፈቻ የተወሰዱ ህፃናት ሌሎችም ህፃናት ያለው የህግ መብት ስላለው አሳዳጊው በሚደርስበት ችግር ይጠየቃሉ፡፡ ለምሳሌ ህፃናትን ልዩ ጥቅም ለማግኘት - የቡና ቤት ሴት ለማድረግ” የሰው ቤት ሠራተኛ አድርገው የሚያመጧቸው አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ህገወጥና በህጉ መሠረት የሚጠየቁ ናቸው ብለዋል፡፡   በአገር ውስጥ ከተለያዩ ክልሎች ወደ ሌላ ክልሎች የሚያዘዋውሩ አሉ፡፡ ከአገር ውጪ ያሉትን በተመለከተ ሪፖርት ስለሚቀርብ የዚህን ያህል ችግር ይገጥማል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በህግ መሠረት ፍርድ ቤት ቀርበው አሳዳጊውም (ሰጪ) ወላጅም ስምምነት ካልፈፀሙ ህገወጥ ተብሎ ነው የሚወሰደው” ብለዋል፡፡
=============================================================

Read 17996 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 13:16