Tuesday, 01 October 2019 10:20

ESOG ለእናቶች ጤንነት የሙያ ብቃትን ለማረጋገጥ ይሰራል

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

 ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ የESOGና የCIRHT ትብብር ፕሮጀክት አስተባባሪ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደገለጹት ሁለቱ መስሪያ ቤቶች በትብብር ከሚሰሩባቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ወደ ማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ትምህርት የሚገቡ ጠቅላላ ሐኪሞች ጥራትና ብቃት ባለው መንገድ ደረጃውን ያሟላ ትምህርት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በተመሳሳይ መንገድ እንዲሰጥ ለማድረግ ድጋፍ መስጠት ነው፡፡ የESOGና የCIRHT ትብብር ፕሮጀክት በአጠ ቃላይ በስምንት ዘርፎች ላይ ይሰራል::
የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ትምህርት ስርአተ ትምህርት (Curriculum) ደረጃውን በጠበቀ መንገድ ማዘጋጀት፤
የፈተና አዘገጃጀት እና አሰጣጥ ላይ ማሻሻያዎች ማድረግ፤
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪም በሕክምና ስነምግባር፤
ቀጣይነት ያለው የሙያ ማጎልበቻ CME ትምህርት አሰጣጥ ላይ ይሰራል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ከሚባሉት ፕሮጀክቶች የሚጠቀሱት ሲሆኑ ይበልጥ ሐኪሞቹ ከየትኛውም ዩኒቨርሲቲ ቢሆን ደረጃውን የጠበቀ ትምህርትን በእኩል ቀስመው የተመጣጠነ እና ወጥ የሆነ ደረጃ እንዲኖራቸውና ህብረተሰቡንም በተመሳሳይ በተሙዋላ መልኩ እንዲያገለግሉ ለማድረግ ሁለተኛው ዙር ፈተና በአሁኑ ወቅት ተሰጥቶአል፡፡ የዚህ ተግባር ውጤትም በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያዎችን እውቀትና ብቃት ከፍ ለማድረግ እንደሚረዳ የታመነበት ነው፡፡  
በኢትዮጵያ ከጠቅላላ ሐኪምነት ወደ ማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስትነት ለመዞር ለሚፈ ልጉ ባለሙያዎች ከአሁን ቀደም ትምህርቱ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጥ የነበረ ሲሆን ነገር ግን የትምህርት አሰጣጡም ሆነ የፈተናው አቀራረብ ወጥነት የሌለው እና ተመሳሳይ ያልሆነ ነበር ማለት ይቻላል:: ስለዚህም በዚህ ፕሮጀክት መጀመሪያ የተሰራው የትምህርት ስርአቱ ማለትም Curriculum ነው፡፡ የተለያዩ የትምህርት ስርአት ለነበራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ፕሮጀክቱ እንደጀመረ ማለትም እ.ኤ.አ በ2016/ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ተመልክተውት ፤አምነውበት አንድ አይነት የትምህርት ስርአት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎቹ ተሰ ራጭቶአል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ 12/የሚሆኑ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ሲሆን ይህንን ህጋዊ ሰነድ ተጠቅመውበታል ወይንስ? የሚለውን ለመፈተሸ የራሱ የሆነ የፍ ተሻ መስመር ወይንም ምዘና ያለው ሲሆን በመሰራት ላይ ያለው ምዘናም ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡ ምዘናውን ከሚያካሂደው አካል ውጪ ደግሞ ያንን የትምህርት ስርአት መሰረት በማ ድረግ ፈተናና ምዘናውን የሚሰራው ኮሚቴ በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የነበረውን በተለያየ መንገድ ማስተማርና በየራሳቸው መንገድ ፈተና መስጠትን ለውጦ ወደ አንድ አይነት አሰራር መለወጥ ቀዳሚው ትኩረቱ ስለሆነ በዩኒቨርሲቲዎቹ ላሉት መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና በቅድሚያ ተሰጥቶአል፡፡ ይህም የተደረገው ከአሜሪካ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ኮሌጅ በመጡ  ባለሙያዎች አማካኝነት ነው፡፡ ከዚያም በመቀጠል የፈተና ፕላን (Blue print) ስልጠና ለሁ ሉም የሙያ ትምህርቱ ለሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች አስተማሪዎች ተሰጥቶአል፡፡ የዚህ የ(Blue print) ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ባለሙያዎች ተናግረውት ከነበረው ለትውስታ የሚከተለውን ታነቡ ዘንድ ጋበዝን፡፡
‹‹…ለማህጸን ሕክምና ልዩ ትምህርት የሚወስዱ የአራተኛ አመት ተማሪዎች ፈተና ይዘጋጅ ሲባል ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ጥያቄዎች ይውጡ ይባላል፡፡ በዚህ ጊዜ ለአስተ ማሪዎች ይከፋፈላል፡፡ አንድ አስተማሪ 20 ጥያቄ እንዲያወጣ ሌላው ደግሞ 30 ጥያቄ እንዲያወጣ…ወዘተ ሲከፋፈል አስተማሪዎቹ የመሰላቸውን ለራሳቸው በሚመቻ ቸው መንገድ ጥያቄ አውጥተው ያስረክባሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ተማሪዎቹ በትምህርት ያላገኙ ዋቸው ጥያቄዎች ሁሉ ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከየርእሶቹ ይህንን አይነት ወይንም ይህንን ያህል ጥያቄ ይውጣ የሚል ምንም አይነት መመሪያ አልነ በረውም:: ስለዚህ ብሉ ፕሪንት የሚለው አሰራር ግን ከየትኛው አርእስት ጥያቄ ይውጣ? ከየርእሱ ምን ምን ያህል ጥያ ቄዎች ይውጡ? የሚለውንና በቀጣይ ማለትም ለወደፊት ለሚኖሩት አሰራሮ ችም ማሻ ሻያ ቢያስፈልግ የሚያገለግል ቋሚ የተማሪዎች ምዘና ሰነድ እንዲ ዘጋጅ የሚያ ደርግ ነው፡፡››  
ዶ/ር ወንድሙ ጉዱ በቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲ ካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር  
ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ እንዳብራሩት የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ትምህርት ባለሙያዎች ትም ህርቱን የሚወስዱት ለአራት አመት ሲሆን በትምህርት ላይ እያሉ የመመዘኛ ፈተና እንዲፈ ተኑ ይደረጋል፡፡ በዚህም መሰረት የመጀመሪያው ፈተና ባለፈው አመት የተሰጠ ሲሆን ይህ የሁለተኛው ዙር ፈተና ደግሞ ዘንድሮ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 4 እና 5/2019 ተሰጥቶአል፡፡ ከአሁን ቀደም በነበረው አሰራር  በማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ የሙያ ትምህርት በመማር ላይ ያሉት የህክምና ባለሙያዎች አራቱን አመት የትምህርት ጊዜ ካጠናቀቁ በሁዋላ በአራተኛው አመት ላይ የሚሰጣቸውን መመዘኛ ሲያልፉ ለሙያው ብቁ ናቸው ተብሎ ይመረቁ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከዚያ በተ ጨማሪ certification examination  ማለትም ከሁሉም ትም ህርት ቤቶች የሚመረቁትን ምሩቃን ወጥ የሆነ ፈተና ፈትኖ እውቅና ወይንም የሙያ ፈቃድ መስጠት እንዲያስችል የተዘረጋ አሰራር ነው፡፡ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በጥቁር አን በሳ፤ በአዋሳ፤ በጅማ፤ በመቀሌ… ወዘተ በ12 ቱም ዩኒቨርሲቲዎች ያሉት ባለሙያዎች ልዩ ትምህ ርቱን በሚገባ ተከታትለዋል? ተመሳሳይ እውቀት አላቸው? እናቶችን ወጥ በሆነ እና በተመሳሳ ደረጃ ሕክምና በበመስጠት ማገልገል ይችላሉ? የሚለውን ለመመዘን እኩል እውቀት ፤እኩል ክህሎት አላቸው ወይ የሚለውን ለመመዘን የሚያስችል ነው፡፡
በእርግጥ የሙያ ተማሪዎቹ በየትምህርት ቤታቸው የሚመዘኑበትን ፈተና በማለፋቸው ወደስራ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሀገሪቱ ለምትፈልገው ደረጃ መብቃት አለመብቃቱን ለማረጋገጥ የሚረዳው ይህ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የታመነበት እና የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር የሚሰ ጠው የcertification examination መመዘኛ ነው፡፡
አንድ ሐኪም በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ ወደ ማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ትምህርት ሲገባ የተነደፈውን የትምህርት ስርአት Curriculum በተመሳሳይ መልኩ አግኝቶ ምዘናውም ደረጃውን በጠበቀና በስርአት በሚመራ መልኩ በተመሳሳይ ከተካሄደ ወደስራው አለም ሲገቡ በተመሳሳይ ሁኔታ ውጤታማ የሆነ ስራ ይሰራሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ በሌላው አለም በአሜሪካና በአውሮፓ የተለመደና ቀደም ብሎ የተጀመረ አሰራር ሲሆን በኢትዮጵያም የተጀመረው የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ማህበር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ድጋፍ በሚያደርጉ አካላት ትብብር ነው፡፡
የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወደልዩ ሙያ ትምህርት የሚገቡ ባለሙያዎችን ወይንም ጠቅላላ ሐኪሞችን ባሉበት የስራ ቦታ ሆነው የሚፈትንበት የኢንተርኔት አሰራር ዘዴ አለ፡፡ የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበርም ያንን ተጠቅሞ ሁሉም የማህጸንና ጽንስ ሕክምና የልዩ ሙያ ተማሪዎች ባሉባቸው የስራ ቦታዎች በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ሆነው አንድ ወጥ የሆነ ፈተና በተመሳሳይ ቀንና በተመሳሳይ ሰአት እንዲፈተኑ አድርጎአል፡፡ በዘንድሮው የፈተና አሰጣጥ አንደኛና ሁለተኛ አመት ተማሪዎች አንድ ላይ፤ ሶስተኛና አራተኛ አመት ተማሪዎች ደግሞ አንድ ላይ ነገር ግን አንድ አይነት ወጥ የሆነ ፈተና እንዲወስዱ ተደርጎአል፡፡ ከእያንዳንዱ አመት የተማሪዎች ደረጃ የሚጠበቅ ውጤት ያለ ሲሆን ተፈታኞቹ በኮምፒውተር ፈተናውን ሰርተው እንደጨረሱ ወዲያውኑ ውጤታቸውን ከኮምፒውተሩ ያገኛሉ፡፡ ይህ የፈተና አሰጣጥም በየአመቱ የሚሰጥ በመሆኑ በየአመቱ የሚኖራቸውን መሻሻል ለማየትም ይረዳል፡፡ ባለሙያዎቹ ግድፈት ያሳዩት የትኛው ፕሮግራም ላይ ነው?ጥንካሬስ የታየው በየትኛው ዘርፍ ነው? የሚለ ውን በማየት ማሻሻያ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ፈተናውም ከአሁን ቀደም በፈተና አወጣጥ ፕላን (Blue print) ስልጠና ላይ የተሳተፉ አስተማሪዎች ያወጡት ነው፡፡
የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር እየሰራ ያለው የዩኒቨርሲቲዎችን አቅም ከማሻ ሻል አንስቶ የትምህርት አሰጣጡ ወጥ እንዲሆን እንዲሁም ፈተናው በአገር ደረጃ በተመሳሳይ መንገድ እንዲሰጥ እና በየትምህርት ቤቱ ወጣ ገባ የሆነ አሰራር እንዳይኖር ለማድረግ ነው፡፡ በአጠቃላይም እኩል የሆነ ደረጃቸውን የጠበቁ ሐኪሞችን ለማፍራት ጥረት እየተደረገ ነው:: ይህ አካሄድ በመላ አገሪቱ ላሉ እናቶች ደረጃውን የጠበቀ ሕክምና ለመስጠት ያስችላል፡፡  

Read 7717 times