Monday, 07 October 2019 15:26

የኤልያስ መልካ ስንብት

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(6 votes)

የዕውቁ የሙዚቃ ጠቢብ ኤልያስ መልካ የቀብር ሥነሥርዓት ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤ/ክርስቲያን ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ተፈጸመ፡፡ በብሔራዊ ቲያትር በተዘጋጀው የሽኝት ፕሮግራም ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ከንቲባ ታከለ ኡማን ጨምሮ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሣና ሌሎችም የመንግስት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ታላቅ የሙዚቃ ባለሙያ የሽኝት ፕሮግራም ላይ እንደተገለጸው፤ ኤልያስ ዕድሜውን ሙሉ ለሙዚቃ ኖሮ ሺዎችን ያፈራና በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ አሻራውን ያኖረ ድንቅ የጥበብ ሰው ነበር፡፡
በ42 ዓመት ዕድሜው በስኳር ህመም ሳቢያ የኩላሊት ድክመት ገጥሞት፣ ህክምናውን በአግባቡ መከታተል ሲገባው፣ ሥራውን በማስቀደም፣ለራሱ ምንም ጊዜ ሳይሰጥና ህመሙን ሳይከታተል በመቅረቱ፣ ለህልፈት መብቃቱ በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ ተጠቁሟል፡፡
የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በታዋቂው የሙዚቃ ባለሙያ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል፡፡ ፈጣሪ ነፍሱን በመንግስተ ሰማያት ያኑርለት፡፡


Read 6116 times