Saturday, 07 December 2019 11:59

ህብረተሰብ ለውጥ ማምጣት ይችላል

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

    December 1-2019 አለም አቀፍ ኤችአይቪ ቀን
አለምአቀፉ ኤችአይቪ ቀን በተለያዩ ተቋማት እና የአለም የጤና ድርጅት መሪ ቃል ይወጣለታል:: ለእትሙ አርእስት ያደረግነው ጥሩ ትርጉም ያለው ሲሆን የአለም የጤና ድርጅትም “Rock the Ribbon”, ብሎ የአመቱን የኤድስ ቀን መሪ ቃል አድርጎአል:: ይህም ሰዎች በደረታቸው ላይ ቀዩን ሪባን እንዲያደርጉ እና ለሁሉም ሰው በግልጸ እንዲያሳዩ ነው፡፡ በአጠቃላይም በየአመቱ የሚሰየሙት መሪ ቃሎች ህብረተሰቡ እራሱ መፍትሔውን የማምጣት ዋነኛ አካል እንዲሆን የሚጋብዙ ናቸው፡፡
በ2019 የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው በ2018-መጨረሻ 37.9 ሚሊዮን ሰዎች በአለም አቀፍ ደረጃ የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ህብረተሰብ ለውጥ ማምጣት ይችላል የሚለው መሪ ቃል አሰያየምም ህብረተሰቡ ንቃተ ህሊናውን እንዲያዳብርና በሁሉም አቅጣጫ በመከላከሉ ረገድ ተመሳሳይ ድርጊት እንዲፈጽም ለማስቻል መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡በዚህም ረገድ ከህብረተሰቡ ጋር አቻ የሆኑ ቡድኖች፤የተለያዩ ተቋማት ፤በህብረተሰቡ ዘንድ ከስር መሰረት ጀምሮ መገናኘት የሚችሉ እና ተሰሚነት ያላቸው እንደ እድር…ማህበር…በመሳሰሉት የሚሳተፉ ሰዎች፤የጤና ባለሙያዎች፤ የጤና ተቋማት፤ የእምነት አካላት…ወዘተ በተመሳሳይ መንገድ ህብረተሰቡ ከኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት እራሱን እና ወገኑን እንዲከላከል ማድረግ እንዲችሉ ታስቦ የተሰየመ መሪ ቃል ነው፡፡
ኤችአይቪ ኤይድስ በአለም አቀፍ ደረጃ አንዱና ዋናው የህብረተሰብ ጤና ጉዳይ ነው፡፡ በ2017 የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው እጅግ አስፈሪ የሆነ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ይነበባል፡፡
በግምት ከ28.9 እስከ 41.5 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ተያያዥ በሆኑ ሕመሞች ሞተዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ36.7 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ገኛል፡፡
በአለማችን በአማካይ 25 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከ1981-2007 ድረስ በኤችአይቨ ኢንፌክሽን ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በ2007-ፀረኤችአይቪ መድሀኒት በአለም አቀፍ ደረጃ ተግባር ላይ ከዋለ በሁዋላ እንኩዋን ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡
በየአመቱ ቀኑን በሚመለከት መሪ ቃሎች የሚወጡ ሲሆን የአለም ኤችአይቪ ቀን መሪ ቃል በ2018-ተመርምረህ እራስህን እወቅ የሚል እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ይላል ሶሻል ፖስትስ፡፡
ብሔራዊ የኤችአይቪ ቀን ምርመራ በማድረግ እራስን የማወቂያ ቀን በየአመቱ እንዲተገገበር በ2018 ተጀምሮአል፡፡ይህ እለት በየአመቱ  June 27- ቀን እንዲውል ተደርጎአል፡፡
June 27- በ2018 የዋለው እሮብ አለት ነበር፡፡
June 27- በ2019 ሐሙስ እለት ይውላል፡፡
June 27- በ2020 ቅዳሜ እንደሚውል worldnationalday.com ይገልጻል፡፡
UNAIDS ባለፈው አመት ባወጣው ሪፖርት በተለይም ሰዎች የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ይኑር አይኑር ለማወቅ ጥረት አለማድረጋቸው እና ቸልተኝነት ትልቁ ችግር ነው፡፡ እራስን ለኤችአይቪ ምርመራ አዘጋጅቶ ቫይረሱ በደም ውስጥ መኖር አለመኖሩን አስቀድሞ ማወቅ በአለም ላይ የሚታቀዱ የልማት ግቦች እንዲሳኩ አጋዥ እንደሚሆን እና በቫይረሱ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በመከላከል ሌሎችንም የቤተሰብ አባላት መከላከል እንደሚቻል UNAIDS ያስረዳል፡፡ ዛሬም አሳሳቢው አድሎ እና መገለል ሰዎች እራሳቸውን ለማወቅ ጥረት እንዳያደርጉ እንደሚያደርግ UNAIDS ያምናል፡፡ ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን እውቀት የማጎልበትና እራሳቸው እንዲያውቁ የማድረግ ጥረት የሳሳ መሆኑን እና ሰዎች ስለ ጤንነታቸው ምርመራ የሚያደርጉት ሲታመሙ ወይንም በአንድ ምክንያት የጤና ምርመራ ውጤታቸው ሲፈለግ መሆኑ በአለም እየታየ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቫይረሱ መኖሩ በታወቀበት ጊዜ ማለትም ከ30/ አመታት በፊት የነበረ ልምድ ነው፡፡ ይህ ልምድ ቫይረሱን በሚመለከት ለሚሰሩ ስራዎች ውጤት እንዳይኖር ማድረግ እና ለሕክምናውም ይሁን ለመከላከሉ ተግባር እውክታን መፍጠሩ አልቀረም፡፡ በወደፊቱ አሰራር በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ብዙ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ለእራስ ከመመርመር ጀምሮ ሕብረተሰብ ቤተሰብን እንዲሁም ህብረተሰቡን ለፕሮግራሙ ዝግጁ ማድረግ እና የኤችአይቪ ቫይረስ በደም ውስጥ መኖር አለመኖሩን አስቀድሞ ማወቅ እንዲሁም ለህክም ናው እና ለምክር አገልግሎቱ ዝግጁ መሆን የሁሉም ኃላፊነት ነው ብሎአል UNAIDS.
አለም አቀፍ የኤችአይቪ ኤድስ ቀን ሲባል ለመሆኑ ምን ማለት ነው ሲል የሚጠይቀው አቨርት የተሰኘው ድረገጽ ነው፡፡ ኤችአይቪ ኤይድስ በአለም ህመም ሆኖ ከተመዘገበበት ወቅት ጀምሮ ብዙዎችን የጎዳ በመሆኑ በየአመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ መፍትሔ መፈለግ እና ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸውን ሰዎች ከጎናቸው በመቆም መርዳት እንደሚገባ የሚያስታውስ ቀን ተደርጎ መታሰብ ከጀመረ እነሆ ሰላሳ አንድ አመቱን አስቆጠረ፡፡
በየአመቱ በዲሴምበር የመጀመሪያው ቀን አለም አቀፉ ህብረተሰብ በተመሳሳይ ቀን ስለ ኤችአይቪ ኤይድስ ሁኔታዎችን የሚያስብበት ቀን ነው፡፡ በቫይረሱ ምክንያት ያጣውን ወገኑን የሚያስታውስበት ፤በቫይረሱ ሁኔታ ላይ ያለው ግንዛቤ አንዲጨምር እና ስርጭቱን ለመግ ታት፤ ስለ ኤችአይቪ ቫይረስ ተገቢው ግንዛቤ እንዲኖር እንዲሁም ስርጭቱን በሚመለከት ምን ማድረግ እንደሚገባ የሚወያይበት ቀን ነው፡፡ አለም አቀፉ የኤችአይቪ ኤይድስ ቀን በዚህ ሁኔታ በየአመቱ እንዲታሰብ የተደረገው እ.ኤ.አ በ1988- ሲሆን በዚያን ጊዜ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች እድሜ በአጭሩ የሚቀጠፍበት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሁኔታዎች ተለውጠው ፀረኤ ችአይቪ (ART)መድሀኒት በስራ ላይ በመዋሉ የሰዎች እድሜ በቫይረሱ ምክንያት በአጭሩ መቀጠፉ ቀርቶ መኖር የሚችሉትን ያህል እንዲኖሩ አስችሎአል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት እንዳወጣው መረጃ እስከ 2016/መጨረሻ ድረስ በአለም ላይ ከ70/ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኤችአይቪ ኤይድስ ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ 35/ ሚሊዮን የሚሆኑት በኤችአይቪ ኤይድስና ተያያዥ ምክንያቶች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት ወደ /36.7/ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ይህም በአለም ላይ አስከፊው ገጽታ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የተሰራው Demographic Health Survey (DHS)  እንደሚያሳየው በቅኝቱ ከተካተቱት ወደ 56% የሚሆኑ ሴቶች እና 55 % የሚሆኑ ወንዶች ስለ ኤችአይቪ ምንም አይነት ምርመራ አድርገው እንደማያውቁ የሚያሳይ ሲሆን ምናልባትም መላው ህዝብ ተመርምሮ እራሱን ቢያውቅ ቫይረሱ በደማቸው አለ የሚባ ሉት ሰዎች ቁጥር ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ይሆናል፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳ ዩት ምርመራ አድርገው ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው መኖሩን ካወቁት ውስጥ 72% የሚ ሆኑት ለጤንነታቸው ማድረግ የሚገባ ቸውን በባለሙያዎች የምክር እገዛ እና ሕክምና የቀጠሉ ሲሆን ወደ 28% የሚሆኑት ግን ቫይረሱ በደማቸው መኖሩ ከተነገራቸው በሁዋላም ችላ ያሉ መሆናቸው ታውቆአል፡፡ እ.ኤ.አ በ2020/ በዓአለም አቀፍ ደረጃ ኤችአይቪ ኤይድስ ስርጭቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል የአለም ሀገራት በተስማሙት መሰረት ኢትዮጵያም የእራስዋን የድርጊት መርሀ ግብር ቀርጻ በእንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች፡፡
በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭት እንዲገታ የተቻለውን ያህል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሚያሳየው መረጃ እንደጠቆመው በሀገሪቱ በመደረግ ላይ ያለው እንቅስቃሴ በአለም አቀፍ ደረጃ ስርጭቱን ቢያንስ እስከ 2020-ድረስ 73% ያህል መቀነስ የሚለውን መስፈርት ለማሟላት የሚያስችል አሰራር መኖሩን ያሳያል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙትም ART በመውሰድ በኩል ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ሰዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ተመርምረው እራሳቸውን ያወቁ በሁሉም መስተዳድሮች፤ ጾታን፤ እድሜን፤ ሳይለይ የሚጠቀሙበት መንገድ ተመቻችቶ ሰዎች ጥሩ አገልግሎት በማግኘት ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያስረዳል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ሰዎች ተመርምረው እራሳቸውን እንዲያውቁ ለማስቻል ተጨማሪ ስራዎችን በመስራት ላይ ያለ ሲሆን በዚህም አሰራር ኢትዮጵያ ከጥቂት የአፍሪካ አገራት ጋር እ.ኤ.አበ2020 የታለመውን ግብ ለማሳካት የምትችል ሀገር ያሰኛታል እንደ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እማኝነት፡፡   

Read 12145 times