Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 30 June 2012 11:08

ፍርሀት ይገድላል

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

እንዲያውም ከሰዎች ይልቅ እንስሳት ናቸው በብዛት በድንጋጤና በፍርሃት የሚሞቱት፡፡ በተለይ ወፍን በመሳሰሉ እንስሳት ላይ አደጋው የከፋ ነው፡፡  ወጥመድ ውስጥ ከሚገቡ ወፎች መካከል 50 በመቶ ያህሉ በድንጋጤ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ፤ በቅርብ አመታት እንስሳትን ከማደን ይልቅ መጠበቅ እያመዘነ በመምጣቱ በድንጋጤ የመሞታቸው አጋጣሚ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ሰውየው ቤቱ ተቀምጦ ፀጥ ባለ ምሸት ወደ አልጋው ስር እንዳጋጣሚ ሲማትር ሁለት የሚያበሩ አይኖች ከጨለማው ስርቻ ሲያፈጥጡበት ያያል፡፡ ክው ይላል፡፡ የልቡ የምት ፍጥነት ይጨምርበታል፡፡

እነዛ አይኖች በተጠንቀቅ የሚመለከቱት እሱን መሆኑ ብቻ ሳይሆን የእነዛ አብረቅራቂ አይኖች ባለቤት … በጣም አስፈሪ እንስሳ ይመስላል፡፡ አይኖቹ የእባብ ናቸው? ምናልባትም የመርዘኛ እባብ፡፡ ሰውየው በተቀመጠበት ሆኖ ወደሚያፈጥበት እንስሳ ባፈጠጠ ቁጥር፤ “ምናልባት” የምትል ቃልትጠፋለች፡፡

የማመዛዘኛ ብቃቱን እያጣ፣ “እንዲህ ቢያደርገኝስ” የሚለው ፍርሀቱ እያየለ ሄደ፡፡ … በስተመጨረሻ የልቡ ምት ከአእምሮው የማዘዝ አቅም በላይ ሆኖ ቆመ፡፡

… አልጋው ስር ሆኖ ሲያደባ የታየው “እንስሳ” ግን፤ የራሱ ጫማ ነው፡፡ ግን ጫማ እንደሆነ ማንም ሊያስረዳው አይችልም - ሰውየው በፍርሀት ከሞተ በኋላ፡፡ የእንስሳው አይኖች፤ ማሰሪያ ያልገባባቸው ጫማ ቀዳዶች ነበሩ፡፡

በቅርቡ “የዙ ቢክዊቷ” (Zoo biquity) እትም ላይ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፤ ከፍርሃትና ከድንጋጤ ጋር የተያያዘ ነው፡፡  “The Science of being scared to Death” በሚል ርዕስ የቀረበው ፅሁፍ፤ ፍርሀት የአእምሮን የማመዛዘን ብቃት ከማሳጣት አልፎ ሞትን ሊያስከትል እንደሚችል ያትታል፡፡

ፍርሀት እና የሰውነት አሰራር

የሰውነት ጡንቻዎች በነርቭ መዋቅር ትዕዛዝ ስር ተጣምረው እንዲሰሩ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ በድንጋጤ ወቅት የሚመነጩ ሆርሞኖች፤ “ካታክሎሚንስ” ተብለው የሚጠሩ ሲሆን፣ ዋነኛ ስራቸውም ጡንቻዎች በፍጥነት፣ በቅልጥፍናና በብቃት እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ከአደጋ እንድናመልጥ ማገዝ ነው፡፡

ድንጋጤው ከመጠን ያለፈ ሲሆን ግን፣ ሆርሞኖቹ ከመጠን በላይ እየመነጩ ይሰራጫሉ፡፡

የልብን የምት ከመጠን በላይ ይጨምራል፡፡ ልብ ማለት የደም ቧንቧዎች ኔትዎርክ ነው፣ በጡንቻዎች ማእቀፍ የተሳሰሩት የልባችን የደም ቧንቧዎች ሲጨናነቁ የልባችን ጡንቻዎች የተወሰኑትም የደም ስሮች በስራ ይጨናነቃሉ፤ ይመረዛሉ፡፡ ልብን እስከ ማቆምም ይደርሳል፡፡

በዚህ አይነቱ መጨናነቅ የልብ ደም ስሮች የሚፈነዱበት አጋጣሚም ይከሰታል፡፡ ልክ ከሌላው ፍርሃትና ድንጋጤ፤ የሚመነጩ ሆርሞኖች ልብን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሰውነትን ጡንቻ ከሚገባው በላይ እንዲሰራ በማድረግ ከጥቅም ውጭ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ፍርሀት በሰው እና እንስሳት አለም

በድንገተኛ ፍርሀትና ድንጋጤ የሚከሰት የሞት አደጋ፣ በሳይንቲስቶች “ታኮስቡቦ” ተብሎ ይጠራል፡፡ በሰዎች ላይ እንዲህ አይነቱ አደጋ የሚበረክተው መቼ መቼ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ሰዎች ይደነግጣሉ፣ የገንዘብ ችግር ሲደርስባቸው በፍርሃት ይርዳሉ፡፡ ህዝባዊ አመፅ እና ብጥብጥ ሲኖርም እንዲሁ፡፡ አንዳንዴ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ፤ በውጥረት ሲከታተሉ የነበሩ ቲፎዞዎችም ለአደጋው የሚጋለጡበት ጊዜ አለ፡፡

የጨዋታው የመጨረሻ ሰዓት ሲቃረብ፣ በፍፁም ቅጣት ምት ስጋት ሲነግስ ልቦች ይንጠለጠላሉ፡፡ የሚያስፈሩ (ሆረር) ፊልሞች ሲያዩ፤ የልባቸው የምት መጠን እየጨመረ የሞቱም አሉ፡፡ … በሰዎች ላይ የሚከሰተው የፍርሀት አይነት እና መጠን፤ በእንስሳት ላይም ተመሳሳይ ነው - ውጤቱም ጭምር፡፡  በፍርሃትና በድንጋጤ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡

ስለ እንስሳት እና በፍርሃት ስለሚገጥማቸው ሞት የቬትረነር ባለሞያዎች አስቀድመው ያውቃሉ፡፡ በተለይ ድንገት ወጥመድ ውስጥ የገቡ እንስሳት ሲሞቱ በተደጋጋሚ ተስተውሏል፡፡ “Capture Myopathy” ይሉታል ይህንኑ የፍርሀት ሞት፡፡

እንዲያውም ከሰዎች ይልቅ እንስሳት ናቸው በብዛት በድንጋጤና በፍርሃት የሚሞቱት፡፡

በተለይ ወፍን በመሳሰሉ እንስሳት ላይ አደጋው የከፋ ነው፡፡  ወጥመድ ውስጥ ከሚገቡ ወፎች መካከል 50 በመቶ ያህሉ በድንጋጤ ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ፤ በቅርብ አመታት እንስሳትን ከማደን ይልቅ መጠበቅ እያመዘነ በመምጣቱ በድንጋጤ የመሞታቸው አጋጣሚ እየቀነሰ መጥቷል፡፡

ግዙፍ እንስሳት ግን፣ ከትንንሾቹ የተሻለ የመቋቋም አቅም አላቸው፡፡ የድንጋጤ ሞት በእንስሳት ላይ በጣም የተለመደ ከመሆኑ የተነሳ፤ በወጥመድ ተይዘው ወደ እንስሳት መጠበቂያ (zoo) የሚመጡ እንስሳትን ከፍርሀት አደጋ ለመጠበቅ የሚወሰዱ እርምጃዎች አሉ፡፡ … ሰው ፊት ከመቅረባቸው በፊት ሰፊ ስፍራ ላይ ብቻቸውን ሆነው እንዲረጋጉ፣ ምንም አይነት ድምፅ እንዳይሰሙ ይደረጋሉ፡፡

በአንድ የእንስሳት ማጐሪያ አቅራቢያ ይሰማ የነበረ የኦፔራ ሙዚቃ “Okapi” የተባለውን ቀጭኔ መሰል እንስሳ በድንጋጤ እንደገደለው ተመዝግቧል፡፡

የተለያዩ አይነት እንስሳዎችን አንድ ላይ ማስቀመጡም ፍርሀትን ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ …

ከኬፕ የመጣውን ጐሽ፤ ከሜዳ አህዮች ጋር እንዲቀላቀል ሲደረግ አያሌ ሜዳ አህያዎች በድንጋጤ ሞተው ተገኝተዋል፡፡

በሰው ልጆችም ዘንድ ነገሩ ተመሳሳይ ነው፡፡

ይህንን መመሳሰል መጀመሪያ በማጣመር ጥናቷን ይፋ ያደረገችው ባቦራ ኔተልሰን ሆሮዊትዝ ናት፡፡ በእንስሳትም በሰውም ላይ ቀዶ ጥገና የምታከናውን ሰርጅን ነች፡፡

ሰዎች እንደ እንስሳት በከፍተኛ ድምፆች ደንግጠው ይሞታሉ፡፡

በድንገተኛ ወጥመድ ውስጥ በመግባት ብቻ፣ ጤነኛ ሰዎች በድንገት ይሞታሉ፡፡ በስራ እና በትምህርት ቦታ ነቀፌታ ሲደርስባቸው፣ የሚወዷቸውን ሲያጡ፣ ሊያመልጡ የማይችሉት ተስፋ አስቆራጭ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ … ድንጋጤ ያጋጥማቸዋል፡፡

ድንጋጤ ደግሞ የአእምሮን ብቻ ሳይሆን የአካል ሞትንም ያስከስታል የሚሉን የ“ዙቢ ኪውቲ” እትም አዘጋጆች ባርባራ ጌትልሰን ሆሮዊትዝ እና ካተሪን ባወርስ ናቸው፡፡

 

 

Read 4922 times Last modified on Saturday, 30 June 2012 13:07