Monday, 03 February 2020 12:05

ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ በ14 ሚሊዮን ዶላር የማስፋፊያ ሥራ አከናወነ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

   የማልታ ጊነስ በፕላስቲክ ጠርሙስ ቀረበ
                                 
           ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ፋብሪካው 14 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ በሰዓት 32ሺ የማልታ ጊነስ መጠጦችን የሚያመርት የፋብሪካ ማስፋፊያ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ፡፡ ኩባንያው ማልታ ጊነስ የተባለውን ከአልኮል ነፃ መጠጥ በአዲስ አይነትና አስተሻሸግ ለገበያ ማቅረቡንም ገልጿል፡፡
ኩባንያው ከትናንት በስቲያ በራዲሰን ብሉ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፋብሪካው ዋና ዳይሬክተር ስቴፊን ኔርንስተይን እንደተናገሩት፤ የደንበኞችን ፍላጎት ለማሟላት ታስቦ ደንበኞች ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ እንደ ልብ ለመጠቀም በሚያስችላቸውና ለአያያዝ በሚያመቻቸው መንገድ ማልታ ጊነስን በፕላስቲክ ጠርሙሶች አሽገው ለገበያ አቅርበዋል፡፡
የዲያጆ ኮርፖሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ዘርይሁን በበኩላቸው፤ ኩባንያው በፕላስቲክ አጠቃቀም ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሌሎች በዘርፉ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር በመሆን የደቡብ አፍሪካውያን፣ ፔትኮ ኩባንያ በመቅጠር ፕላስቲኮች ተመልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዝና ከፕላስቲክ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ስለሚመጣው ጉዳትና መልካም አጋጣሚዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችንም ለመስጠት አብሮ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡  


Read 1821 times