Saturday, 07 March 2020 12:21

ጥራቱን የጠበቀ ሕክምና…በተመሳሳይ… ለእናቶች

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

   በኢትዮጵዮጵያ ከጽንስ ጋር በተያያዘ የሚደርስ የእናቶች ሞት ምን ያህል ነው የሚለውን በሚመለከት ጥናት ያደረጉት እነ አየለ ገለቶ (PhD candidate) የተለያዩ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ነጥቦች ለንባብ ብለዋል፡፡
ከጽንስ ጋር በተያያዘ የሚደርሱ የጤና እክሎች በአለም አቀፍ ደረጃ ለሴቶች አስፈሪ ነገሮች ሲሆኑ በዚህም በእርግዝና ላይ ካሉ ሴቶች ወደ 15% ያህል ተጎጂዎች ናቸው፡፡ (WHO 2012)
በትክክለኛው መንገድ ሕክምና ካላገኙ ከጽንስ ጋር ተያያዥ የሆኑ የጤና ችግሮች በእርግዝናና ልጅ በመውለድ ጊዜ መጨረሻው የእናት ሞት ሊሆን ይችላል፡፡ (Say 2014).
ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የእናቶች ሞት ከፍተኛውና ትኩረትን የሚሻ የህዝብ የጤና ችግር ሲሆን የእናቶች ሞት መጠን ከሌሎች የአለም ክፍሎች ይልቅ ከፍተኛውን ደረጃ ይዞ ይገኛል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው የእናቶች ሞት መጠን 99 % የሚሆነው ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ሲሆን ከዚህም ውስጥ 66% ከሰሃራ በታች ባሉት የአፍሪካ ሀገራት መሆኑ ተመዝግቦአል:: (WHO 2015)
በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ተመዝግቦ ያለው የእናቶች ሞት መጠን ከ (100.000) በሕይወት ከሚወለዱ (412) ሲሆን ዛሬም የእናቶች ሞት መጠን ከፍተኛ ከሚባልባቸው ሀገራት የምትጠቀስ ናት፡፡ (EDHS 2016)
በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ ጥናቶች ለተጠቆሙት የእናቶች ሞት ከፍተኛው ደረጃ በጽንስ ምክንያት ከሚፈጠር ችግር ጋር እንደሚገናኝ ጥናት አቅራቢዎቹ ይስማማሉ፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን የእናቶች ሞት ከመቀነስና የጤና ችግሩን ከመከላከል አንጻር ለመሆኑ ምን ያህል ሴቶች በእርግዝናቸው ወቅት ድንገተና ለሚከሰት ችግር ወደሆስፒታል ይገባሉ ወይንም ወደሆስፒታል ከገቡ በሁዋላ ምን ያህሉ ችግሩ ይከሰትባቸዋል ከሚለውና ከሆስፒታሉስ ሳይወጡ የሚደርሰው የሞት መጠን ምን ያህል ነው? የሚለው በአጠቃላይ ወደሆስፒታል ከመጡ እናቶች ለይቶ በጥናት የታየው በተለያዩ ሀገራት ሲሆን በኢትዮጵያም የእነ አየለ ገለቶ (PhD candidate) ጥናት መረጃውን ለንባብ ብሎአል፡፡
እርጉዝ የሆኑ ሴቶች እና ጨቅላ ሕጻናት በሚደርስባቸው የጤና ችግር ምክንያት ምን ያህሉ አገልግሎት ለማግኘት ችለዋል የሚለውን በሚመለከት የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲ ትዩት በ2016 እ.ኤ.አ የዳሰሳ ጥናት አድርጎ ነበር:: በጥናቱም አፋጣኝ ወይንም አስቸኳይ የጽንስና የጨቅላዎች ጤና ክብካቤን እና ሌሎች የእናቶችና የጨቅላዎችን ጤና ችግሮችን በሚመለከት ከተለያዩ መረጃዎች የህዝብ እና የግል የጤና ተቋማትን ለመመልከት ችሎአል፡፡ በዚህ ጥናት ደግሞ ወደ 293 በሚሆኑ ሆስፒታሎች ዳሰሳ ተደርጎአል፡፡ ምን ያህል ሴቶች ለወሊድ ቀረቡ፤ምን ያህል ሴቶች በቀጥታ ከጽንስ ጋር በተያያዘ የጤና ችግር ገጠማቸው የሚለውን ለመለየት በምህጻረ ቃሉ DOCFR  የተሰኘው አሰራር የሚገልጸውን ለማየት ተችሎአል:: ይህ አሰራር ምን ያህል ሴቶች ከጽንስ ጋር በተያያዘ በደረሰባቸው የጤና ችግር ወደሆስፒታል እንደመጡ ወይንም ሆስፒታል ከገቡም በሁዋላ ቢሆን ምን ያህሉ ተመሳሳይ የጤና ችግር ገጠማቸው? በዚህ ምክንያት ከሆስፒታል ሳይወጡ ምን ያህሉ እንደሞቱ የሚያሳይ መረጃ አሰራር ነው፡፡ ከዚህም በመነሳት፤
ሆስፒታሉ ደረጃው ምንድን ነው?
የሆስፒታሉ አመራር ምን አይነት ነው?
ሆስፒታሉ የት ነው ያለው?
ሆስፒታሉ ምን ያህል የተሟላ ነው?
ባለሙያዎቹስ ምን ያህል ናቸው? የሚለውንም ለይቶ የሚያሳይ አሰራር ነው፡፡
እናቶች በእርግዝና ወቅት ከልጅ መውለድ ጋርም ሆነ ተያያዥ በሆነ ምክንያት የተለያዩ በአፋጣኝ እርምት የሚገባቸው የጤና እክሎች ሲገጥማቸው የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት እንደቦታው ወይንም የህክምና ተቋሙ የተለያየ መሆኑ እሙን ነው፡፡
ይህንን መሰረት በማድረግ በተለያዩ ሀገራት የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩት ውጤት ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ሲሆን በዚህ የጥናት ወረቀት የተመዘገበው እንደሚከተለው ነው፡፡
15% የሚሆን ከእርግዝና ወይንም ልጅን ከመውለድ ጋር በተያያዘ የጤና ችግር መድረሱ የሚያሳይ መረጃ ይታያል፡፡ (የአለም የጤና ድርጅት እ.ኤ.አ 2012)
እናቶች ሕይወታቸውን ከሚያጡባቸው ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ የደም ግፊት ሲሆን በዚህ የሚሞቱ እናቶች ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ የተራዘመ ምጥ፤ ከወሊድ በሁዋላ ደም መፍሰስ፤ ከወሊድ በሁዋላ የሚከሰት ኃይለኛ መመረዝ (Infection) ለእናቶች ሞት ምንያቶች መሆናቸውን በኬንያ፤በኤርትራ፤እና በብራዚል የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
በጥቅሉ ሲታይ እርጉዝ ሴቶች አስቀድሞውኑ ወይንም ሆስፒታል ከገቡ በሁዋላ የሚደርስባ ቸውን የጤና ችግር በአፋጣኝ የህክምና አገልግሎት በመስጠት እርዳታ የማድረግ አሰራር መኖር ይገባዋል ተብሎ በተቀመጠለት መመሪያ መሰረት እየተከናወነ መሆኑ ምናልባትም ለእናቶች ጤና አገልግሎት የተሻለ አሰራር መዘርጋቱን ወይንም በምእተ አመቱ የልማት ግብ ምክንያት መንግስት ከፍተኛ ትግል ማድረጉን የሚያሳይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ መስተ ዳድሮች ያለውን ልዩነት ጥናቱ እንደሚከተለው ያስነብባል፡፡
በጋምቤላ እናቶች ከእርግዝና ጋር በተያያዘ በህክምና ላይ እያሉ የመሞታቸው ሁኔታ ከፍተኛ ማለትም 3.82 ከመቶ ሲሆን ይህም ከአዲስ አበባ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
በአፋር፤ ሐራሪ፤ እና ሶማሊያ ላይ ከሌሎች ከፍተኛ የሚባል ደረጃ ላይ የሚገኝ መረጃ ተመዝግ ቦአል፡፡
በጋምቤላ፤ አፋርና ሶማሊ መስተዳድሮች ችግሩ ሰፋ ያለ የመሆኑ ምስጢር ለእናቶች ጤና ያለው የህክምና አገልግሎት ውስን መሆኑ እና በአኑዋኑዋራቸውም ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ መሆና ቸው ነው የሚያሰኝ እውነታ አለው፡፡ በሃራሪ በኩል ያለው ምክንያት ደግሞ ጥራቱ ዝቅተኛ የሆነ የጤና አጠባበቅ ሊሆን ይችላል የሚል እምነት አለ፡፡
በብሔራዊ ደረጃ እርጉዝ ሴቶች ለሚገጥማቸው ድንገተኛ ሕመም አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት ምላሽ ባለማግኘታቸው እናቶች ከሆስፒታል ሳይወጡ የሚሞቱበት ምክንያት የማህጸን መፈን ዳት፤ ከወሊድ በሁዋላ የመድማት፤ እና የደም ግፊት ቀዳሚውን የሚይዝ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በብሔራዊ ደረጃ እናቶች ጥራቱን የጠበቀና ብቃትባላቸው ባለሙያዎች የታገዘ የእናቶች ጤና አገልግሎት ሊሰጥ እንደሚገባ መንግስትን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ሊያውቁ ይገባል፡፡
ለእናቶች ሞት በምክንያትነት የሚጠቀሱት የደም ግፊት፤ ኢንፌክሽን፤ የማህጸን መተርተር፤ ከወ ሊድ በሁዋላ የደም መፍሰስ አደገኛ የሆኑ እና ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙ በመሆኑ የሚመለ ከተው ሁሉ ልብ ሊለው የሚገባ ነው፡፡
የእናቶች የጤና አገልግሎት በየመስተዳድሩ የሚሰጥበት ደረጃ ከፍና ዝቅ ሳይል ጥራቱን በጠበቀ እና በሰለጠነ ባለሙያ በተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
በአንዳንድ መስተዳድሮች ባሉ ሆስፒታሎች ያለው የእርጉዝ ሴቶች የጤና ክትትል ደካማ ስለሆነ ምልከታን ይሻል፡፡
የእናቶች ህክምና አገልግሎትን ጥራት በማሻሻል ደረጃ ትኩረት ሊደረግ ይገባል፡፡
በብህራዊ ደረጃ ለየሆስፒታሎቹ ያለው የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ስርጭት በእኩል ወይንም አገልግሎት ከሚሰጡት ሕብረተሰብ ቁጥር ጋር የተመጣጠነ መሆን ይገባዋል፡፡
የእናቶችን ሞት በመቀነሱ ረገድ የሚሰጠው የህክምና አገልግሎት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል እና እንዴት ይሻሻል የሚለውን እና የህብረተሰቡን አኑዋኑዋር ጭምር ቤት ለቤት በሚያሰኝ ሁኔታ መፈተሸ፤ ማጥናት፤ ለተሻሻለና ጥራቱን ለጠበቀ የእናቶች የህክምና አገልግሎት መደረግ የሚገ ባውን ለመጠቆም የሚያስችል አገር አቀፍ ጥናት ማድረግ እንደሚገባ የእነ አየለ ገለቶ (PhD candidate) ጥናት ይጠቁማል፡፡


Read 12199 times