Saturday, 21 March 2020 13:00

“ሁላችንም ተረባርበን ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ማዋል አለብን”

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(7 votes)

     ሙዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ላም በረት መናኸሪያ፣ በጎ ፈቃደኞችን በማሰማራት ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ወደ መናኸሪያው የሚገቡና ከመናኸሪያው የሚወጡ መንገደኞችን እጅ የማስታጠብ ሥራ መጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን፤ በዚህም በመላው ዓለም የተሰራጨውንና በቅርቡም ወደ አገራችን የገባውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዳሰበ ጠቁሟል፡፡
ይሁን እንጂ ቀኑን ሙሉ የሚወጡና የሚገቡ መንገደኞችን እጅ በማስታጠብ የሚሰሩት ውስን በጎ ፈቃደኞች እንደሆኑና ውስን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንዳላቸው የገለፁት የሙዳይ መስራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ፤ በጎ ፈቃደኞች ወደ መናኸሪያው መጥተው እጅ በማስታጠብ፣ ሳሙናና ሌሎችን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በመለገስ እንዲረዷቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አሁን ለተጋረጠብን ችግር ሁላችንም ተረባርበን ምላሽ መስጠት ስላለብን በጉልበት፣ በእውቀት፣ በገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ በመረባረብ፣ ቫይረሱን በቁጥጥር ስር ማዋል አለብን ብለዋል - ሥራ አስኪያጇ፡፡

Read 2330 times