Wednesday, 06 May 2020 00:00

ለማጆችን በቆፍጣና ስልጡኖች እንተካ!

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 ቆየት ያለ “ሰኔ ሰላሳ” የተሰኘ ድንቅ የአማርኛ ፊልም ላይ እንዲህ የሚል ምልልስ አስታውሳለሁ.....
ጠያቂ… ድምፅህን እማውቀው ይመስለኛል?
ተጠያቂ…. አዎ የሬዲዮ ፕሮግራም አለኝ፤ ጋዜጠኛ ነኝ፡፡
ጠያቂ….. አዎ አዎ አዎ ሬዲዮ ላይ ሰምቼሀለው….. አሃ በዝነኛ ሰው ነዋ የምሸኘው?
አሃሃሃሃ  እንዴት  ነው  ሙያውን ትወደዋለህ?
ተጠያቂ….. አዎ በጣም፡፡
ጠያቂ… ጥሩ ሙያ ነው ለማንበብ ቅርብ ያደርጋል….. ታዲያ አንተ የትኛው ጋዜጠኛ ነህ? ህዝብ ላይ የሚለምዱት ወይስ እውነተኛዎቹ?
ተጠያቂ…  አይ…. ይ….ብሎ እንደ መሳቀቅ አለ፡፡
ጠያቂ….. አይዞህ አይዞህ ጫንቃ ሰፊ ህዝብ ነው፤ ሁሉም ነው እሚለምድበት፤ ከሰባኪ እስከ ፖለቲከኛው ይሞክሩብናል፤ ይሞከርበታል ይሄ ህዝብ፤ እህህ………እያለ ይቀጥላል ፊልሙ።
***
እውነት ነው ሕዝቡ ጫንቃው ሰፊ ነው፤ ስንቱ እየመጣ ፖለቲከኛ ነኝ ሲል፣ ሳንመርጠው ወክዬሃለሁ ሲል፣ የጎረነነና የሰለለ ድምፁን ይዞ ዜመኛ ነኝ ሲል ....እንጨት እንጨት የሚል ግጥም ፅፎ ባለቅኔ ነኝ ሲል፣ ከፖለቲከኛ ያልተናነሰ ስብከት እየሰበከ ወንጌላዊ ነኝ ሲል፣ ሰው የመሆንን ጉዳይ ዘሎ ስለ ብሔር እየሸነሸነ እያስተማረ መምህር ነኝ ሲል፣ በቁም ያሉት አልበቃ ብለውት የሉሲን ብሔር እፈልጋለሁ እያለ እየተጋጋጠ ዶክተር ነኝ ሲል፣ ሰርክ በኩራት የጀሶ እንጀራ ለህብረተሰቡ እየሸጠ ታማኝ ነጋዴ ሲል.....እረ ስንቱ ይጠቀሳል:: እነዚህን ሁሉ ነኝ ባዮች፣ ሕዝቡ በሰፊው ጫንቃው ተሸክሞ ነው የሚኖረው።
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ማንም የሚለምድበት መለማመጃ ሜዳ ነው፤ ህብረተሰቡ።
..... መፍትሄ
 1ኛ. ለማጆች ቴሌቪዥን ፊት ቀርበው የሚናገሩትን ከማሰብ የሚሉትንና ሊሉ የፈለጉትን ሃሳብ ቢያንስ አጥንተው፣ ውሸትም ቢሆን ቢያንስ ልጆቻችን እንዳይበላሹ ስርዐትና ሞራልን የሚጠብቅ ነገር ቢናገሩ መልካም ነው።
2ኛ. ትላንትም ዛሬም ነገም በህዝቡ ላይ የሚለማመዱ ይሉኝታ ቢስ አይነደረቆች በዝተዋልና መፍትሄው ህዝቡ በቃኝ ማለት ሲችል ነው ፣ ህዝቡ ጫንቃውን አጥብቦ አሸንራቶ መጣል ሲችል ነው።
3ኛ. ምንም እንኳ አንዱና ዋነኛው በህዝብ ላይ ተለማማጅ አካል እራሱ መንግስት ቢሆንም...ቢያንስ የማይመጥኑ ፕሮግራሞችን...ነጋዴዎችን....ነቢያቶችንና ጸሃፍት ፈሪሳውያንን በለመደውና በታጠቀው መቀስ ይቁረጥልን።
ለማጆችን በቆፍጣና ስልጡኖች እንተካ!
(ከመልእክተ ሥንታየሁ ሰሌዳ)

Read 6609 times