Saturday, 20 June 2020 11:55

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ የ(Face Mask) ድጋፍ ተደረገ፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

  ብዙ ሰዎችን የሚያሳስባቸው መሞት ነው፡፡ ግን ሞት የሚሞተው በምን ሁኔታ ነው የሚለው የበለጠ አሳሳቢው ነገር ይመስለኛል፡፡
በሕክምናው ትምህርት የሚነገረን ሰው እንዳይሞት ማድረግ እንዳለብን ነው፡፡ በተጨ ማሪ ግን ከማዘር ተሬዛ ቤት እኔ የተማርኩት …ለካስ የሰውን የመጨረሻ ሰአት ማሳመ ርም በራሱ ከሕክምና የማይተናነስ በጎ ተግባር ነው፡፡  
ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ
የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማበበር ለተለያዩ ድርጅቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (Face Mask) ድጋፍ አደረገ፡፡ ማህበሩ (ESOG) ግንቦት 29/2012 በአዲስ አበባ ለሚገኙት ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ (ማሪያ ቴሬዛ) ፤ጎጆ (የህሙማን ማረፊያ) ፤የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማህበር፤ ለተሰኙት ድርጅቶች በግንባር በመቅረብ ለእያንዳንዱ ድርጅት ከሁለት ሺህ እስከ አራትሺህ የሚደርስ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በስነስርአቱም ላይ የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤የማህበሩ አባል ዶ/ር መንግስቱ ኃይለማርያም እና የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሰላማዊት ክፍሌን ጨምሮ ሌሎች እንግዶችና የማህበሩ ሰራተኞች ተገኝተው ነበር፡፡ ማህበሩ ድጋፍ ያደረገውን (Face Mask) ያገኘው በውጭ ከሚገኙ የሙያ አጋሮች በተደረገ ትብብር መሆኑ ታውቆአል፡፡
የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ደጋፍ ካደረገባቸው ቦታዎች በአንዱ ማለትም ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ በተሰኘው የህክምና ተቋም ዶ/ር መቅደስ ዳባ የሚከተለውን ተናግረው ነበር፡፡
‹‹ ዛሬ እዚህ በመገኘታችን እጅግ ደስተኞች ነን፡፡ እናንተም በዚህ ተገኝታችሁ የደሀ ደሀ የተባለ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን እየረዳችሁ በመሆኑ ከማሪያ ተሬዛ አላማ እንዲሁም በዚህ ቦታ የሙያ ድጋፍ ከሚያደርጉት የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች እና ከአጠቃላይ በሙ ያው ላይ ከተሰ ማራችሁት ከእናንተ ብዙ እየተማርን መሆኑን መግለጽ እወዳለሁ፡፡ ሁልጊዜም የምንናገረው ነገር እናቶች ከምንም ነገር በቅድሚያ ትኩረትን ድጋፍን ይሻሉ የሚል ነው፡፡ የእናቶች እጆች ምንጊ ዜም ማንኛቸውንም ህጻናት እንኩዋን ደህና መጣችሁ ብለው የሚቀበሉ ኛቸው፡፡ የአለም ልጆች በዘር በሀይማኖት በጾታ ሳይለዩ ሁሉም ለእናቶች በተመሳሳይ ልጆቻቸው ናቸው፡፡  ስለዚ ህም እንደ ኢትዮጵያ ማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር እዚህ በመገኘታችን ተባባሪነታችንን የሚያ ጠናክርልን ከመሆ ኑም ባሻገር በግንባር እዚህ ተገኝታችሁ እነዚህን ወገኖቻችንን የምትረዱትን ባለሙያ ዎች እራሳችሁንም ሆነ ታካሚዎቻችሁን ከኮቪድ -19 ልትከላከሉ የምትችሉበትን (Face Mask) ስናቀርብላችሁ ለምትሰሩት ስራ ከልባችን እያመሰገንን ነው ›› ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ በሚሽን ኦፍ ቻሪቲስ የበጎ ፈቃድ ሐኪም ስለሆኑ በሳምንት አንድ ቀን እየሄዱ ለታካሚዎች የሕክምና አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ይህ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ ከያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ትይዩ ባለ መንገድ ገባ ብሎ የሚገኘው በማሪያ ተሬዛ ስም የሚታወቀው ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ የደሃ ደሃ የሆኑና በራሳቸው ምንም አይነት ሕክምና ለማያገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በተመላላሽና በማስተኛት የህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በተለይም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚኖሩትን ማህበረሰብ ክፍሎች የሚያጠቃውን ተቪ እንዲሁም ኤችአይቪን በማከም ይህ የህክምና ተቋም ጉልህ ሚና አለው፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ሲያጋጥም ስምምነት ወደተደረገባቸው የመንግስት ሆስፒታሎች በመላክ ከፍ ያለ ሕክምና እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሰለሞን አንድ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ‹‹…በየመንገዱ ላይ ብዙ የመኖሪያ ቤት የሌላቸው ሰዎች ይኖራሉ፡፡ በዚያው እያሉ ልጅ ይወልዳሉ፡፡ በዚያው እያሉ ይታመማሉ፡፡ ለመሆኑ በየመንገዱ ሰዎች ለምን ሞተው አይታዩም የሚል ጥያቄ አቅርቦ የሚያውቅ አለ? የሚል ነበር፡፡ በእርግ ጥም ይህንን ብዙ ሰው አስቦት የማያውቅ በመሆኑ በስፍራው የነበሩ ሰዎችም ግራ የመጋባት ምልክት ነበር የታየባቸው፡፡ የዶ/ር ሰለሞን መልስም ሰዎች በየመንገዱ ሞተው ላለመታየታቸው ምክንያት ከሚባሉት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የያዘው የማሪያ ተሬዛ ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ ነው፡፡ የሚል ነበር፡፡
ምንም አይነት ታዛቢ የሌላቸው የደሀ ደሀ የሆኑ ሰዎች፤ጧሪ ቀባሪ የሌላቸው ወገኖች፤ ባጠቃ ላይም ኑሮአቸውን በችግር ገፍተው በስተመጨረሻም በሕመም ከጎዳና ላይ ወይንም ባሉበት አካባቢ ሲሰቃዩ በአካባቢያቸው ያሉ እነሱን መሰል ሰዎች ከወደቁበት አንስተው የሚያመጧቸው ወይንም አምቡላንስ ከወደቁበት አንስቶ ለሕክምና እርዳታ የሚያመጣቸው ወደ ሚሽነሪስ ኦፍ ቻረቲ ነው፡፡ ይሄ ቤት ባይኖር ኖሮ ከተማ ውስጥ በየጎዳናው ሰው ሞቶ ማየት ብርቅ አይሆንም ነበር ብለዋል ዶ/ር ሰሎሞን፡፡ በቀን እስከ ሀያ እና ሰላሳ ሰው ለሕክምናው የሚቀርብ ሲሆን ድጋፍ በተደረገላቸው ወቅት እስከ 400/የሚደርሱ ታካሚዎች አልጋ ይዘው ተኝተው እንደነበር መረጃው ያሳያል፡፡ ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ ከአዲስ አበባ ውጪም የሚገኝ ሲሆን በብዙ የአለማችን ክፍሎችም እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎአል፡፡
የማዘር ተሬዛ ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ በእናቶች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ሌሎች ታካሚዎች ከሚገለገሉበት ክሊኒክ ፊት ለፊት በኑሮአቸው ዝቅተኛ የሆኑ እናቶች በእርግዝና ላይ እያሉ ከሚደረግላቸው ክትትል በተጨማሪ ለመውለድ አንድ እና ሁለት ወር ሲቀራቸው ገብተው እንዲተኙ የሚደረጉበት ከወለዱም በሁዋላ ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ታርሰው እንዲወጡ የሚደረግበት ሌላ የተመቻቸ ስፍራ አለ፡፡
ዶ/ር ሰለሞን እንደሚሉት ብዙ ሰዎችን የሚያሳስባቸው መሞት ነው፡፡ ግን ሞት የሚሞተው በምን ሁኔታ ነው የሚለው የበለጠ አሳሳቢው ነገር ይመስላል፡፡ ሰዎች ሲሞቱ በባህሉም ይሁን እንደየእምነቱ አስፈላጊው ተደርጎለት ወደቀብር ሲሸኝ ማየት ትክክለኛው ሲሆን እንኩዋንስ የቀብር ስነስርአታቸው በወግ ሊፈጸም መፈጠራቸውም ሳይታወቅ የሚያልፉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህንን ችግር ለመቀነስ ግን በአለም በተለያዩ አገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዋና ዋና ከተሞች የሚገኙት የማዘር ተሬዛ ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲዎች ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ ስለሆነም ማዘር ተሬዛ የደሀ ደሀ የሆኑ ምንም እራሳቸውን መርዳት የማይችሉ ሰዎችን ሕክምና አድርጎ ጤነኛ ማድረግ ተቀዳሚው ተግባር ሲሆን ይህ ካልተቻለም የሰውን የመጨረሻ አሟሟት ማሳመር ሌላውና በጉልህነት የሚፈጽመው ተግባር
ማዘር ተሬዛ የእርዳታ ስራዋን የጀመረችው በህንድ በካልካታ ሲሆን ለስራዋ መነሻ የሆናትም በካልካታ መንገዶች ላይ ስማቸው ማን እንደሆነ እንኩዋን ሳይታወቅ ወድቀው የሚኖሩ እና የሚሞቱ ሰዎች የነበሩ መሆኑ ነው፡፡
‹‹…አንድ ሰው በጠና ታሞ ለሕክምና መጣ፡፡ ከእኔ እጅ እንደደረሰ በቅድሚያ ስሙን ጠየቅ ሁት፡፡ እገሌ ነኝ አለ፡፡ ነገር ግን አፍታም ሳይቆይ ወዲያው እጄ ላይ አለፈ፡፡ እኔም ቢያንስ ቢያንስ እገሌ የሚባል ሰው በዚህች ምድር ላይ ተፈጥሮ እንደነበረ አስመዝግቦ ሞተ አልኩ….››
ማዘር ተሬዛ  
ማዘር ተሬዛ የገጠማት አይነት ታካሚዎች በኢትዮጵያ ሲገኙ ወደ ሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ ይመጣሉ፡፡ ስማቸው ሳይታወቅ የሚሞቱ ሰዎች ሚስተር X ወይንም ሚስ/ሚስስ X ተብለው እንደሚቀበሩም የታወቀ ነው፡፡ ሰዎቹን ከወደቁበት አንስተው ለሕክምና ሲያመጡዋቸው በነበሩበት ሁኔታ ምናልባትም 6ወር ወይንም አንድ አመት ያህል ልብሳ ቸው ሳይቀየር ፤ቀምለው፤ሸተው፤እራሳቸውን ጭራሽ ጥለው ፤ወደ መንግስት ጤና ተቋም እንኩዋን መሄድ ሳይችሉ ቀርተው ለሞት ሲያጣጥሩ ይህ ተቋም ሲቀርቡለት ትልቅ ስራ ይሰራል፡፡ ገላቸውን አጥቦ….ጸጉራቸውን ላጭቶ፤ልብሳቸውን ቀይሮ ፤አልጋ ተሰጥቶ አቸው ሲታዩ ጭራሽ ሌላ ገጽታን ይላበሳሉ፡፡ ከህመማቸውም መዳን ይጀምራሉ፡፡ የሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ ተግባር ለሕክም ናው ሲመጡ መሞት ቀርቶ በሕይወት ተለውጦ ጤናማ እንዲሆኑ ማስቻል በመሆኑ ይህንን በመስራት ስመጥር በጎ አድራጊ ነው…እንደ ዶ/ር ሰለሞን ወርቁ በሚሽነሪስ ኦፍ ቻሪቲ በጎ አድራጊ ሐኪም ምስክርነት….
በስተመጨረሻው ዶ/ር ሰለሞን የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር የኮሮና ቫይረስን መከላከያ ከሆኑት ግብአቶች አንዱን ማለትም (Face Mask) በድጎማ ስላበረከተላቸው ምስጋና ቸውን አቅር በዋል፡፡ በዚሁ ለአንባቢዎች ማስታወስ የምንወደው ማዘር ተሬዛ ከአለፉ በሁዋላ በአለም ላይ ላደረጉት በጎ አስተዋጽኦ በእምነታ ቸው የ(ጻድቅ)ነት ማእረግን አግኝተዋል፡፡  

Read 12519 times