Saturday, 11 July 2020 00:00

ጥያቄና መልስ ስለ …COVID-19

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

   እርግዝና….ልጅ መውለድ እና COVID-19-ን በሚመለከት የአለም ጤና ድርጅት የዛሬ አራት ወር march/2020 በድረገጹ ጥያቄና መልስ አውጥቶ ነበር፡፡ COVID-19-ን በሚመለከት ምን ጊዜም የማይቀር…ባይሆን የሚሻሻል ነገር ካለ የሚሻሻል በመሆኑ ለትውስታ በዚህ እትም ወደ አማርኛ መልሰን ታነቡት ዘንድ እነሆ ብለናል፡፡  
በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ከሌሎች ይልቅ በከፍተኛ አደጋ ውስጥ ናቸውን?
በአሁኑ ወቅት ከቀረበው ጥያቄ ጋር በተያያዘ ጥናቶች እየተደረጉ ነው፡፡ በዚህ ጥናትም ትኩረት የሚደረገው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሚከሰተው ኢንፌክሽን በእርግዝና ላይ ባሉት ሴቶች ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል የሚል ነው:: በእርግጥ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶችንና ኮሮና ቫይረስን በሚመለከት ያሉት መረጃዎች ውስን ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን በአለንበት ወቅት ከሌላው ማህበረ ሰብ በተለየ እርጉዝ ሴቶችን የበለጠ ተጎጂ ይሆናሉ የሚል ምንም መረጃ የለም፡፡  
እርግዝና በራሱ በእርጉዝዋ ሴት ሰውነት እና ሕመምን የመቋቋም ስሜት ላይ ተፈጥሮአዊ ለውጥን እንደሚያስከትል የታወቀ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ቢያዙ ደግሞ ከመተንፈሻ አካሎቻቸው ጋር በተያያዘ በሚደርስባቸው ሕመም እንደሚረበሹ እሙን ነው፡፡ ለዚህም ነው አስቀድሞውኑ እራሳቸወን ከቫይረሱ መከላከልና አንዳንድ የተለዩ ስሜቶች ሲኖሩዋቸው በፍጥነት ለሕክምና ተቋም ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባቸው፡፡ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ትኩሳት፤የመተንፈስ ችግር፤ሳል፤የመሳሰሉት የጤና ችግሮች ሲገጥሙዋቸው አስቀድሞውኑ ለሚከታተላቸው ሐኪም ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
አንዲት እርጉዝ ሴት እንዴት አድርጋ እራስዋን ከ መከላከል ትችላለች?
በእርግዝና ላይ ያለች ሴት የCOVID-19 ቫይረስ ለመከላከል የታወቁ እና ማኛውም ሰው የሚጠቀምባቸውን  የመከላከያ ዘዴዎች መጠቀም በቂ ነው፡፡ ይህ ከተደረገ የኮሮና ቫይረስን መከላከል ይቻላል፡፡
እጅን በተደጋጋሚ በሳሙና መታጠብ:: እጅን በአልኮሆል ወይንም ከአልኮሆል ጋር ተደባልቆ ለእጅ ማጽጃነት በተዘጋጀ ሳኒታይዘር በደንብ ማጽዳት፡፡
በራስና በሌሎ ሰዎች መካከል በሚፈጠረው ግንኙነት ምንጊዜም እርቀትን መጠበቅ እና ሰዎች ከሚበዙበት ቦታ እራስን ማራቅ፡፡ ቢቻል ቢቻል ከቤት ሆኖ ስራን መስራት እና ወደውጭ የሚወጡበትን ጊዜ መቀነስ፡፡
አይንን አፍንጫንና አፍን ከመነካካት መቆጠብ፡፡
ትንፋሽን እንዴት መከላከል እንደሚገባ አስቀድሞ መለማመድ፡፡ ይህም ማለት በማሳል ወይንም በማስነጠስ ጊዜ አፍንጫንና አፍን በክርን በመሸፈን ወይንም በመሐረብ መሳይ ነገሮች በመሸፈን መጠቀም፡፡ የተጠቀሙበትን ነገር ወዲያው አርቀው ወይንም ሰው እንዳያገኘው በማድረግ መጣል ይገባል፡፡
አንዲት እርጉዝ ሴት ትኩሳት ሳል ወይንም የመተንፈስ ችግር ከገጠማት አስቀድሞ ለሕክምና ባለሙያ መንገር እንዳለባት እንዲሁም ከሕክምና ተቋሙ የሚነገራትን መመሪያ መከተልና መተግበርንም መርሳት የለባትም፡፡  
እርጉዝ ሴቶች እና ሌሎች በቅርብ የወለዱ ሴቶች እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የነበሩ ሁሉ የህክምና ክትትላቸውን በምንም ምክንያት ማቋረጥ የለባቸውም፡፡
በእርግዝና ላይ ያለች ሴት ሕመሙ ሳይሰማት አስቀድማ የኮሮና ቫይረስን ምርመራ ማድረግ አለባትን?
የህክምና ምርመራ ማድረግ እንደሚኖሩበት ቦታና ሁኔታ የሚለያይ ነው፡፡
ለማንኛውም WHO የሚሰጠው ምክር አለ:: በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች የኮሮና ቫይረስ ስሜት ሲኖራቸው ከምንም ነገር በማስቀደም ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ የኮሮና ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ካለ ልዩ እና የተለየ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡
COVID-19 ከእናትየው ወደ ጽንሱ ወይንም ወደ ጨቅላው ይተላለፋልን?
አንዲት እርጉዝ ሴት የኮሮና ቫይረስ ቢኖርባት ወደ ጽንሱ ወይንም በማህጸን ውስጥ ወደአለ ህጻን መተላለፉ እስከአሁን ድረስ ግልጽ አይደለም:: እስከአሁን ድስ ቫይረሱ በጽንሱ ላይ ወይንም በተወለደው ልጅ ላይ ለመተላለፍ የሚያበቃው በሽርትውሀም ይሁን በእናት ጡት ወተት አልተገኘም፡፡  
በእርግዝናና ልጅ በመውለድ ጊዜ ምቹ የሆነ የጤና አገልግሎት ይኖራልን?
ሁሉም በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች እና የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው የተገመተ ወይንም የተረ ጋገጠላቸው ሴቶች ጥራት እና ብቃት ያለው የጤና አገልግሎትን ከመውለዳቸው በፊትም ይሁን ከወለዱ በሁዋላ የማግኘት መብት አላቸው፡፡ ይህም ልጅ ከመወለድ በፊት፤ አዲስ የተወለዱትንና ከተወለዱ በሁዋላ ያሉትን የጤና ክትትል ይጨምራል፡፡  
ደህንነቱ የተጠበቀ እና ጥሩ የሚባል ልጅ አወላለድ የሚከተሉትን አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋል፡፡
ክብርና ጥሩ ቀረቤታ ባለው መንገድ የጤና አገልግትን ማግኘት፤
በመውለድ ጊዜ የሚተማመኑበት፤ ምርጫቸውን የሚያሟሉበት እድል መኖር፤
ከአዋላጅ የህክምና ባለሙያዎች ጋር ግልጽ የሆነ ግንኙነት፤  
ተገቢ የሆነ ህመምን የሚያስታግስ ዘዴ መኖር፤
ምጥን እንደአመጣጡ ማስተናገድ እና በምን መንገድ ሊወለድ እንደሚችል ማሳወቅ፤
የመሳሰሉት ተግባራት በማዋድ ስራ ላይ ከተሰማሩት ባለሙያዎች ይጠበቃል፡፡
የኮሮና ቫይረስ መኖሩ የተጠረጠረ ወይንም የተረጋገጠ ከሆነ የጤና ሰራተኞች እራሳቸውንና ሌሎችንም ከአደጋው ለመጠበቅ የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፤ ተገቢውን ቫይረሱን ለመከላከል የሚያ ስፈልገውን የህክምና ባለሙያ ልብስ መልበስ (የእጅ ግላብ ማጥለቅ፤ ጋዋን መልበስ፤ አፍንጫንና አፍን መሸፈን) የመሳሰሉትን መጠቀም ያስፈልጋል::
የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው የታወቁ እርጉዝ ሴቶች በቀዶ ሕክምና ልጃቸውን መውለድ ይጠበቅባቸዋል?
WHO እንደሚሰጠው ምክር ከሆነ ልጅን በቀዶ ሕክምና የመውለድ ውሳኔ በህክምና ባለሙያዎች የሚወሰን ይሆናል፡፡ ልጅን በተፈጥሮአዊው ም,መንገድ ለመውለድ የማይቻልበት ምክንያት ሲያጋጥም እና በእትየውም ስምምነት የሚደረግ ነው፡፡
እናትየው የኮሮና ቫይረስ ካለባት የተወለደውን ልጅ መንካት እና ማጥባት ይቻላልን?
የተወለደው ልጅ ከእናቱ ጋር የቅርብ ግንኙነት ካለውና ያላቋረጥ ጡት መጥባት ከተደረገለት ሊደርስት ከሚችለው ህመም እንዲያመልጥ የሚረዳው ነው፡፡ ስለዚህ፡-
ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ጡት ማጥባት
የልጁን ሰውነት ወደ እናትየው ሰውነት በማስጠጋት መያዝ
እና ከልጁ ጋር ክፍልን መጋራት እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
ነገር ግን ልጁን ከመንካት በፊትም ሆነ ከነኩ በሁዋላ እጅን በደንብ አድርጎ መታጠብ እንደሚገባ መረሳት የለበትም፡፡ ልጁ የሚተኛበትን ክፍል መሬቱን ሁሉ ካለማሰለስ ማጽዳት ይገባል፡፡
ምናልባትም ከዚህ በተጨማሪ መደረግ የሚገባው ነገር ቢኖር WHO ከስር ከስሩ አስፈላጊውን መረጃ ለመስጠትና ምክር ለመለገስ ዝግጁ መሆኑን በድረገጹ በተጨማሪ ገልጾአል፡፡


Read 2093 times