Sunday, 06 September 2020 00:00

የተመጣጠነ ምግብ ችግር በ COVID-19 ወቅት…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

ልጆችዎ ጤናማ ምግብ እንዲመገቡ ማድረጊያ መላዎች - BBC News አማርኛ    በተመጣጠነ ምግብ እጦት ይበልጥ ተጎጂ የሚሆኑት በተለይም በእርግዝና ላይ ያሉ፤ የሚያጠቡ እናቶች እና ህጻናት ናቸው፡፡
በዘመናችን የተመጣጠነ ምግብ በልማት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች መካከል ነው የሚለው International Food policy Research Institute ነው፡፡ የጥናት ተቋሙ እ.ኤ.አ በ April 23, 2020 ለንባብ እንዳበቃው ከሆነ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት በተለይም ከከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ ብዙ እንቅፋቶች ሊገጥሙት እንደሚችል ማሳያዎችን በድረገጹ አስቀምጦአል፡፡ በተለ ይም በእርግዝና ላይ ላሉ ሴቶችና ለህጻናት ምን ያህል አስቸጋሪ መሆኑን እንደሚከተለው ዘርዝ ሮአል፡፡
Derek Headey and Marie Ruel እንደሚሉት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአለም አቀፍ ደረጃ ለሚኖረው የተመጣጠነ ምግብ እጦት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ወረ ርሽኙ ባስከተለው ተጽእኖ ምክንያት በማደግ ላይና በመካለኛ ደረጃ ባሉ ሀገራት በተለይም ለጉዳት የተጋለጡ ሰዎች በተለ ያየ መንገድ ኑሮአቸውን ለማሳካት ወይንም ለመጠገን ስለሚቸገሩ በዚህ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት በዋነኛነት እንደሚጎዱ እሙን ነው፡፡
የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በምን ምክንያት ይከሰታል ብለን ስናስብ ይላሉ ባሙያዎቹ…..
ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፊት ይሰሩት ከነበረው ስራ መገለል ወይንም ይሰሩት የነበረው ስራ በወረርሽኙ ምክንያት ገቢ የማያስገኝ በመሆኑ እንዲቋረጥ በመሆኑ የገቢ መቀነስ ወይንም መቋረጥ ሲከሰት፤
በኮሮና ቫይረስ ላለመያዝ በተቻለ መጠን በቤት ቆዩ በሚለው መመሪያ መሰረት በተለይም ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑት ሰዎች በቤታቸው ቢቆዩ ለራሳቸው የሚሆን ነገር የማያገኙ መሆኑ እና አቅም ያላቸው ሰዎች ደግሞ በቤታቸው በመቆየታቸው ምክንያት ገበያዎች ስለሚቀዘቅዙ እና የእለት ፍላጎቶችን ሸጠው የሚጠቀሙ ሰዎች በመቸገራቸው፤
በመንገድ ላይ የሚሸጡ ምግቦች ደፍሮ የሚገዛቸው ተጠቃሚ በመቀነሱ፤
በትምህርት ቤቶች የትምህርት ስርአቱ ለጊዜው ስለተቋረጠ የምግብ አቅርቦትም አብሮ በመቋረጡ፤ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች በተለይም በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖሩ ሰዎች የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ሊያቅታቸው ይችላል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ የጤና ተቋማት ከተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ጋር የተያያዘ አገል ግሎት ይሰጡ የነበሩ ከሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረቱ ላይከሰት እንደሚችል ጥናት አቅራቢ ዎቹ ይገልጻሉ፡፡ ለምሳሌም የእርግዝና ክትትል፤የተመ ጣጠነ ምግብ አቅርቦት፤ የህጻናትን ተቅማጥ መከላከልና ድጋፍ ማድረግ በተመለከተ በሚዘረጉ ፕሮግራሞች፤ኢንፌክሽን፤እና የተ መጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል ጋር ተያይዞ ድጋፉ የሚቀጥል ከሆነ ችግሩ ብዙም አይስተዋልም፡፡
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሰዎችን የተለያዩ ጠቃሚ ምግቦችን እንዳያገኙ ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚባልበት ምክንያትም አትክልቶችን፤ፍራፍሬዎችን ፤የእንስሳት ተዋጽኦ…ስጋ …ወተት…ዶሮ…አሳ…ወዘተ የመሳሰሉትን ምግቦች እንደልብ ማግኘት ከአቅርቦትም ሆነ ከገንዘብ ጋር በተያያዘ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወይም ተያያዥ በሆነ ምክንያት የተከሰተ የገቢ መቋረጥ ካለ በግልጽ ቤተሰብን ለማስተዳደር የማያስ ችል ድህነት ሰለሚኖር ይህ አይነት ኑሮ የገጠማቸው ሰዎች በዝቅተኛ ዋጋ ሊያገኙ የሚችሉ ትን ውስን ነገር በማቅረብ በተደጋጋሚ እንዲመገቡት ይገደ ዳሉ፡፡ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የተመጣጠነ ምግብ ለማግኘት የሚረዱ እንደ እንቁላል… ፍራፍሬ….አትክልት…የመሳሰሉት ምግቦች እንደ በቆሎ…ሩዝ…ስንዴ …ከመሳሰሉት ምግቦች ጋር ሲነጻጸር ዋጋቸው አስር ጊዜ ያህል ስለሚ በልጥ ዝቅተኛ ዋጋ ባላቸው ምግቦች መወሰን ግድ ይሆናል፡፡ በእንደዚህ አይነቱ የቤተሰብ አስተዳደር ውስጥ ይበልጥ ተጎጂ የሚሆኑት ደግሞ በተለይም በእርግዝና ላይ ያሉ ወይንም የሚያጠቡ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን ጥናቱ ይገልጻል፡፡
ስለዚህ በ COVID-19 ምክንያት የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ለሚያቅታቸው ሰዎች ምን ቢደረግ ችግሩን ይቀንሰዋል በሚል ድረገጹ የሚከተሉትን ጠቃሚ ሀሳቦች በዝርዝር ያስነብባል፡፡
ፖሊሲ አውጪዎችና ተመራማሪዎች ይህንን ችግር በመቅረፉ ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት ያለባ ቸው ሲሆን መንግስታትና የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ ትኩረት ሰጥተው አቅጣጫ መቀ የስ አለባቸው፡፡ ይህንን ካደረጉ የኮሮና ቫይረስን መከላከልንና ሌሎች የጤና ችግሮችም እንዳይከ ሰቱ ለማስቻል የሚረዳውን የሰዎችን የተመጣጠነ ምግብ ፍላጎት ለማሟላት ጥረት በማድረግ ችግሩን ሊወጡት ይችላሉ፡፡ በተያያዘም ሰዎች በተቻለ መጠን ገቢያቸው እንዳይቀንስ የሚያደ ርገውን ስልት በመቀየስ ድህነት እንዳይኖር ማድረግም ያስችላቸዋል፡፡
ከግብርና ጋር የተያያዙ ምግቦችን ለማቅረብ የሚያስችለውን አሰራር መዘርጋት፤ በዚህ ፕሮግራም ገበሬዎች እናዲያመርቱ ፤ይህንን በሙያቸው መደገፍ የሚችሉ ስራቸውን በአግባቡ እንዲወጡ፤ነጋዴዎች ምርቱን ወደ ተጠቃሚው እንዲያደርሱ(እንዲሸጡ)፤ የሚያስችለውን አሰራር እውን ማድረግ፤
በቤት ውስጥ…በጉዋሮ…በበረንዳ ላይ….በእቃ ላይ …ሊመረቱ የሚችሉትን አትክልትና ቅጠላቅጠሎች…ፍራፍሬዎች እና ዶሮ…እንቁላል የመሳሰሉትን ሴቶች… ልጆች…ሁሉ እርቀታቸውን ጠብቀው ሊሰሩት እንደሚችሉ መምራት ይጠቅማል፡፡ ይህ ከተደረገ ቤተሰቡ ከገበያ በሚመጣው ላይ ብቻ ሳይወሰን በቤቱ ውስጥ የተመጣጠነ ምግብን ማምረትና መመገብ ይችላል፡፡
ለምግብ የሚሆኑ ምርቶችን ለማሰራጨት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዱ ምክሮ ችን ተግባራዊ በማድረግ መንቀሳቀስ፤ ለዚህም መንግስት፤የልማት ሰራተኞች፤አነስተኛና ጥቃቅን እንዲስትሪዎች አስፈላጊውን ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል፡፡
መሰረታዊ የሆነውን የእናትና ልጅ ጤንነት አገልግሎትን መጠቀም እንዳይደበዝዝ አስፈ ላጊውን ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያዎች ህብረተሰቡን በጤና ተቋም መገልገል እንዳለባቸው ግንዛቤ ለማስጨበጥ ብዙ አስቸጋሪ ጊዜያትን እንዳለፉ እሙን ነው፡፡  እናቶችም የእራሳቸውንም ሆነ የልጆቻቸውን ጤና ከሚጠብቁበት የተሻለ እው ቀት ደረጃ ላይ ያሉ ሲሆን ነገር ግን የኮሮና ወረርሽኝ ባስከተለው ችግር ዛሬ ብዙዎች ከጤና ተቋሙ ለመሄድ ሲያቅማሙ ይስተዋላሉ፡፡ በቅድሚያ የጤና ተቋማቱ ታካሚችን ለማስተናገድ ምቹ በሆነ ሁኔታ እራሳቸውን እንዲያደራጁ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ተገልጋዮችም ከፍርሀት ይልቅ ጥንቃቄን በማስቀደም እራሳቸውን ከጤና ተቋም እንዳ ያርቁ ይመከራሉ፡፡በተጨማሪም እናቶችና ህጻናት መሰረታዊ የሆነ ውን የተመጣጠነ ምግብ ለማግኘት እንዲችሉ በሞባይል ስልክ ወይንም በመገናኛ ብዙ ሀን አማካኝነት እንዲሁም ኮሮና ቫይረስን ለመከታተል በሚዘረጋው የቤት ለቤት አገልግ ሎት ጭምር ተገቢውን መረጃ መስጠት ይገባል፡፡     
በኮሮና ቫይረስም ይሁን በሌሎች ለኢንፌክሽን በሚያጋልጡ ምክንያቶች እናቶችም ሆኑ ልጆቻቸው እንዳይጎዱ ስለእጅ መታጠብና ስለንጽህን በደንብ ማስተማር ከጤና ባለሙያ ዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ይጠበቃል፡፡
የጤና አገልግሎትም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መንግስትንም ጨምሮ ለህብረተሰቡ የተመጣጠነ ምግብ እጦት ማለት ምን ማለት እንደሆነና በምን መንገድ ችግሩን እንደሚወጣው ማሳየትን በከፍተኛ ሁኔታ ሊሰሩት የሚገባው ነው፡፡ ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጎድተው የሚያሳዩትን ምስሎች ማሳየት እና ትክክለኛው መንገድ ምን እንደሆነ መጠቆም በአጠቃላይም እናቶች የራሳቸውንና የልጆቻቸውን ሕይወት እንዴት በተመጣጠነ ምግብ በበቂ ሁኔታ መምራት እንዳለባቸው ማስተማር ያስፈልጋል፡፡  
የኢኮኖሚው ጫና፤ ማህበ ራዊ መራራቁ፤የቤትውስጥ ጥቃትንና የስነልቡና ጫናን እንደሚያ ስከትል እሙን ነው፡፡ ስለዚ ህም ማህበ ራዊ ደህንነትን በሚሰጡ ፕሮግራሞች እናቶችንና ህጻናትን ማስቀድም ይመከ ራል፡፡ በተያያዘም ህብረተሰቡ ግለሰቦችን በመርዳት በኩል አዳዲስ ነገር እንዲያውቁ እና ያወቁ ትን ነገርም እንዲከውኑ ማስቻል ትልቅ ስራ ነው፡፡ የእናቶችንና የህጻናትን ደህንነት መጠበቅ የተቀዳሚነትን ድርሻ ይይዛል፡፡

Read 11254 times