Saturday, 12 September 2020 13:30

ሔኒከን ቢራ ፋብሪካ በጐርፍ ለተፈናቀሉ የኮንደሚኒየም ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

   ሔኒከን ቢራ ፋብሪካ ቂሊንጦ በሚገኘው ፋብሪካው አካባቢ በጐርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው ለተፈናቀሉ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 9 ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ፡፡
በቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተባለ ሞዶ ዳርፋር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነሐሴ 10 ቀን 2012 በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የተከሰተው ጐርፍ በሦስት ህንፃ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው አስራ አንድ አባወራዎች ሄኒከን የበዓል መዋያና ሌሎች ድጋፎች አድርጐላቸዋል፡፡
በወቅቱ የጐርፍ አደጋው ተከስቶ ነዋሪዎቹ ከመኖሪያ ቤታቸው በተፈናቀሉ ጊዜ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍ ሊያደርግላቸው መቆየቱን የገለፁት ከተፊናቃዮቹ መካከል አቶ ባዩ ወንድሙ፤ አሁን ደግሞ ፋብሪካው በዚህ መንገድ ከወገኖቹ ጐን መቆሙን ማሳየቱ እጅግ የሚያስደስት ነው ብለዋል፡፡ አደጋው በድንገት የተከሰተና ከባድ ጉዳት ያደረሰብን በመሆኑ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገን ነበር የሉት አቶ ባዩ በዚህ ጊዜ ያገኘነው ድጋፍና እርዳታ ለእኛ ትልቅ ነገር ነው ብለዋል፡፡ ፋብሪካው በችግራችን ጊዜ ከጐናችን በመሆን ካሳየን አጋርነት ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው ሲሉም በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪዎች፤ ጊዜያዊ መኖሪያ እንደተሰጣቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Read 1343 times