Print this page
Saturday, 12 September 2020 15:10

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(9 votes)

    “ልብ ያለው ልብ ይበል”

መልካ ምሳለ
ክፋት መርጠን፣
ደምብ ጥሰን
ህግ አፍርሰን፣
ብርሃን ትተን
ሰንዳክር በጨለማ፣
ከሰውነት ተራ ወረድን
ማንነታችን ተቀማ።
ፈጣሪን እረስተን
ግፍ አንፈራ ብለን፣
ቀኙን መንገድ ትተን
ግራውን አጥብቀን፣
ገንዘብ ስልጣን ወደን
ሰይጣንን አንግሰን፣
በፈፀምነው ክደት
በሰራነው ሥራ፣
ያመፃችን ልኬት
በፅዋተ ሰፍራ፣
ደምወዝ ተከፈለን
አጨድን መከራ።
ባውቃለሁ ባይነት
ትዕቢት ተወጥረን፣
ቅዱሱን አርክሰን
እርኩሱን ቀድሰን፣
አውሬ ያልሞከረውን
ስንት ነገር ሰርተን፣
ያጠራቀምነው ግፍ
ሰይጣን አስቀንተን፣
ዛሬ ፅዋው ሞልቶ
በትንፋሽ ጨረሰን።
አያድርስ አይጣል ነው
የፈጣሪ ቁጣ፣
ጣራችን ከበደ
ሞታችን ቅጥ አጣ፣
ጥሪያችን ፈጠነ
መኖር ትርጉም አጣ፣
ትናንት የነበረው
ሲነጋ እየታጣ።
ሀዘን ግራ ገባው
ቀብራችን ሰው አጣ፣
ወንበር ፈር ቶሸሸ
ድንኳንም አልወጣ፣
የበደል ክምችት
ይህን ቀን አመጣ፣
ልብ ያለው ልብ ይበል
የባሰ እንዳይመጣ።
ነሐሴ 15, 2012

       ብላሽ!
እኛ ...
እብዱ ኹሉ፣ ከንቱው ኹሉ፣
ባልጠረቃ ጅል አመሉ፣
በመንገዱ ያሰረውን - ዝባዝንኬ፣ ስለ
ትትብታብ፣
ያገም ጠቀም ውራ ወሬ - ተረት ሙሉ ባዶ
ክታብ፣
ቋጠሮውን ያላወቅን - ካሰረው እብድ
የማንሻል፣
ተነጋግረን ከምንፈታ - ስናጠብቀው ቀን
ይመሻል።
እብዱስ ይኹን ቀድሞም አብዷል -
አሳሳቢው የኛ ነገር፣
ድልድይ መስበር የለመድን - ገደል ማዶ
ሳንሻገር።
(ከአበረ አያሌው ፌስቡክ)


Read 2928 times
Administrator

Latest from Administrator