Saturday, 10 October 2020 15:22

ከእውነትና ከውሸት ጀርባ÷ “ሌላ-ወግ”

Written by  ገዛኸኝ ፀ ጸጋው
Rate this item
(4 votes)

 “እውነት” እና “ውሸት” ምንድን ናቸው?
ከእውነት ጀርባ ውበት
ከውሸት ጀርባ ጉልበት
              ተማጥቆ እየታያቸው፣
የውሸት ጉልበቷ ጥፋቷ
የእውነት ጉልበቷ ጽናቷ
              እንዲል ፈጣሪያቸው፣
              ያ “ሰው” ከጀርባቸው…
የኑሮ ፍሙን እየሞቀ፣ አመዱን ነፍቶባቸው፣
እውነትም ይኸው ገረጣች፤ ውሸትም ወዟን ደፋችው፡፡
…..
ከ’ውነትና ከውሸት ጀርባ፣
ኑሮን አዝለው ባንቀልባ፣
ኑሮም ዙሩን ሲያከረው፣ ተያይዘው ከሚወድቁ!
ውሸትም ሟሽሻ እንዳትቀር፣ ለአደባባይ ሳይበቁ፣
ለእውነት አማላጅ ላከች፤ ሕያው መሆኗን እንዲያውቁ፡፡
…..
መቼ ይሆን? በኢትዮጵያ ሰማይ፣ ሁለቱም ሳያማጠቁ፣
ሕገ ሥጋን ከሕገ ነፍስ፣ እርስበርስ ሳይናጠቁ፣
ሕገ ዶሴያቸውንም ሳይፍቁ፣
የመንፈስ ልዕልናን ሳይደፍቁ፣
እኮ መቼ ይሆን!? ፍትሕን የሚያጠይቁ!
…..
ውሸት እንድትታወቅ፣ ችሎት ላይ ደምቃ እንድትወጣ፣
እውነት ትመስክርላት፤ ጥሯት! ከጀርባ ትምጣ …
ይኸው ነው ነገረ ዕውቀቱ፣ የሲኖዛ የሕይወት ፍላጻ፣
ያለ ውሸት እውነት አትቆምም፤ ውሸት በውሸት አትነጻ!?
የካቲት 2006 ዓ.ም. (ለምን ጊዜም የፍትሕ እና የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቹ ኢትዮጵያዊ÷  ለፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የተበረከተ)


Read 2978 times