Friday, 23 October 2020 14:53

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(18 votes)

 አይተሻል አንዳንዴ


  የወደቀ ዛፍ ነው ምሳር የሚበዛው
እቃ ብቻ አይደለም ገንዘብ የሚገዛው
እንኳን እኔና አንቺ
ከፍጡራን በላይ ልቆ የሚበልጠው፣
40 በማይሞላ 30 ብር ነው አምላክ
የተሸጠው፡፡
አይተሻል አንዳንዴ
ሰይጣን ስላለ ነው እግዜር የሚነግሰው፣
ህመም ሲጠፋ ነው መድሀኒት
ሚረክሰው፣
ያው አምላኩ ብሎት
የሙሴ በትር ነው ባህር የገመሰ፣
በዳዊት ፊት አደል ጎልያድ ያነሰ፣
ቢሆንም በ ትሩ ባ ህር ምን ቢገምስም
አይበልጥም ከሙሴ፣
ጎልያዶች ሁሉ በምነታችን እንጂ
በድንጋይ አይወድቁም፣
ትልሻለች ነፍሴ፡፡
ካስተዋልሽ አንዳንዴ
እውር ያለ በትሩ ወዴትም አይሄድም
የሟች ስጋ ሁሉ መቃብር አይወርድም
የገደለም ሁሉም ወንጀለኛ አይደለም
ነፍስን ስለማዳን ነፍስ ይጠፋ የለም፡፡
አይተሻል አንዳንዴ
እውቀት ያለው ሁሉ ገድል አያበዛም፣
የተማረ ሁሉ ሃገርን አይገዛም፣
ታዲያ እንዲህ ከሆነ ተማሩ ባልናቸው፣
እውቀት በቀሰሙት ሃገር መች ይናዳል፡፡
ተመልከች አንዳንዴ
ያፈቀረ ሁሉ ፍቅሩን አያገኝም፣
ሽበት ያለው ሁሉ ሽምግልና አይዳኝም፣
የሚሮጠው ሁሉ አይሆንም አንደኛ፣
አይተሻል አንዳንዴ እንደዚህ ነን እኛ፡፡
አስታውሰኝ ረጋሳ
“ተስፋ” ከተሰኘ መድብል የረወሰደ


Read 2885 times