Print this page
Saturday, 14 November 2020 10:37

በጤና ወልዶ ጤናማ ልጅ ማሳደግ፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

እርግዝናን ከተለያዩ የጤና ጉዳዮች ጋር በማየት ለጥንቃቄ ይረዳል በሚል ለንባብ ያበቃው National Center for Chronic Disease Prevention and Health Promotion ሲሆን ለንባብ የበቃውም እ.ኤ.አ August 13, 2020 ነው፡፡ ይህ ማእከል እርግዝናን ከእርግዝና በፊት ከነበሩ የተለያዩ ሕመሞች እና በእርግዝና ወቅት ሊፈጠሩ ከሚችሉ ሕመሞች ጋር በማነጻጸር ሊደረጉ ይገባቸዋል የሚላቸውን የምርምር ውጤቶች ታነቡ ዘንድ  ወደ አማርኛ መልሰ ነዋል፡፡
ከእርግዝና ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች፤
በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ የጤና ችግሮች ወይንም ውስብስብ ነገሮች አሉ ሲባል የእርጉዝዋን ሴት ወይንም ያረገዘችውን ልጅ አለዚያም የሁለቱንም ጤንነት ሊጎዳ የሚችል ነገር ነው፡፡ አንዳንድ ሴቶች በእርግዝና ወቅት የሚነሳ ሕመም ሊኖራቸው የሚችል ሲሆን አንዳንዶች ደግሞ ከማርገዛቸው በፊት የጤና ችግር ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ስለዚህም ለማንኛዋም ሴት ከማ ርገዝዋ በፊት የህክምና ወይንም የምክር አገልግሎት ማግኘት እንዳለባት ጥናቶች ያስረዳል፡፡
ከእርግዝና በፊት፤
ማንኛዋም ሴት ከማርገዝዋ በፊት ቀደም ሲል ስለነበራት የጤና ችግር ለሐኪምዋ በማማከር ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባት መጠየቅ መረሳት የለበትም፡፡ ከእርግዝና በፊት ስለ ነበረው የጤና ችግር ሐኪሙ ማወቁ ጠቃሚ የሚሆነው የህክምና ባለሙያው ልታረግዝ ያቀ ደችው ሴት በእርግዝናዋ ወቅት በምን መንገድ በጤናማ ሁኔታ ሕመሙን እየተቆጣጠረች መቀጠል እንዳለባት ለመወሰን ስለሚረዳው ነው፡፡ ለምሳሌም፤
ከእርግዝና በፊት ይወሰዱ የነበሩ አንዳንድ መድሀኒቶች በእርግዝና ወቅት ቢወሰዱ ጎጂዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በሌላም በኩል ከእርግዝና በፊት ይወሰዱ የነበሩ መድሀኒቶች ከሐኪም ውሳኔ ውጭ በሆነ መንገድ በእርግዝና ወቅት ቢቋረጡ የጤና ችግር እንደማያስከትሉ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡
ስለዚህም ከእርግዝና በፊት ስለነበረው የጤና ሁኔታ በዝርዝር ከሕክምና ባለሙያው ጋር በመነ ጋገር እና ችግሩን በመቆጣጠር ጤናማ በሆነ መንገድ እርግዝናው ሊጠናቀቅና ጤናማ ልጅ ለመውለድ መንገዱን ማመቻቸት ተገቢ መሆኑን ማመን ይገባል፡፡
በእርግዝና ወቅት፤
እርግዝና ሲከሰት ያረገዘችው ሴት ባልተለመደ ሁኔታ አንዳንድ የማይመቹ ነገሮች ሊስተዋሉባት ይችላል፡፡ ንዴት፤ ምቾት ማጣት፤አንዳንድ የህመም ስሜት የመሳሰሉ ነገሮች ባረገዘችው ሴት ላይ ሊስተ ዋል ይችላል፡፡ አንዳንዴም ላረገዘችው ሴት ስሜቱ በምን ምክንያት እንደተከሰተ መገ መት ሊየስቸ ግራት እና ትክክል ነው ወይንስ አይደለም የሚለውን ጥያቄ ለራስዋ መመለስ ሊያስቸግራት ይችላል፡፡ በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ የጤና ችግሮች በአካል ወይም በስነልቡና ላይ የሚታዩ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ችግሮች በእርግዝናው ምክንያት ወይንም በሌላ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ሲሆን አብዛኞቹ በከፋ ደረጃ የማይስተዋሉ እና ጉዳታቸውም እድገት አድርጎ የበለጠ የታማሚነት ስሜትን አያሳዩም። ይሁን እንጂ ምንም እንኩዋን ሕመሙ በከፍተኛ ሁኔታ ደርሶ እርጉዝዋን ሴት ባይረብሻትም በውጤቱ ግን እናትየውን ወይንም የተረገዘውን ልጅ ሊጎዳ እንደሚችል አስቀድሞ መገመት ይጠቅማል። ሁሉም ሰው (ባል፤ እናት፤ አባት፤ እህት፤ ወንድም፤ ወይንም በአካባቢው የሚገኙ ጉዋደኛ ጎረቤት…ወዘተ) ሊያውቀው የሚገባው ነገር ማንኛዋም ሴት በእርግዝና ወቅት ከሕክምና ባለሙያ ጋር የቅርብ ግንኙነት ማድረግ፤ የክትትል ጊዜን ማክበር እንደሚገባት ነው፡፡
የደም ማነስ፤
በእርግዝና ወቅት ሊከሰቱ ይችላሉ ከሚባሉት የጤና ችግሮች አንዱ የደም ማነስ ነው፡፡ የደም ማነስ ሲባል አንድ ጤናማ ሰው ሊኖረው ከሚገባው ቀይ የደም ሴል ቁጥር በታች ሲኖረው ነው፡፡ አንዲት እርጉዝ ሴት የደም ማነሰ ሕመም ከገጠማት በሚደረግላት ሕክምና የቀይ የደም ሴሎች መጠን እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡ አንዲት እርጉዝ ሴት የደም ማነስ ካጋጠማት ድካም ሊኖራት እና ጠንካራ ላትሆን ትችላለች፡፡ ይህ የጤና ችግር  iron and folic acid suppl- ement) አይረን እና ፎሊክ አሲድ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በተጨማሪነት እንድትወስድ ግድ ይላል፡፡ የህክም ናው ባለሙያ እርጉዝዋ ሴት እስክትወልድ ድረስ ባላሰለሰ የአይረን መጠንን መከታተል ይጠበቅበታል፡፡
የሽንት ቧንቧና አካባቢው ሕመም፤
የሽንት ቧንቧ ወይንም በአካባቢው የሚፈጠር ህመም መነሻው በባክቴሪያ ምክንያት የሚከሰት ኢንፌክሽን ሊሆን ይችላል፡፡ አንዲት እርጉዝ ሴት ይህ ሕመም ሲከሰትባት የሚከተሉትን ስሜቶች ታያለች፡፡
ሽንትዋን በምትሸናበት ወቅት ማቃጠል ወይንም ሕመም፤
ወደመታጠቢያ ቤት ቶሎ ቶሎ መመላለስ፤
በታችኛው የሆድ አካባቢ ጫና መፍጠር ወይንም ክብደት መኖር፤
መጥፎ ሽታ ያለውና ደመናማ ወይንም ቀይ መልክ ያለው ሽንት መሽናት፤
የጀርባ ሕመም የመሳሰሉትን ስሜቶች ታያለች፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች የሚስተዋሉ ከሆነ በፍጥነት ወደሕክምና ባለሙያ በመሄድ የተፈ ጠረውን ኢንፌክሽን በሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ማስወገድ ይጠቅማል፡፡ በእርግጥ እርግ ዝና ያላት ሴት ከሽንት ጋር በተያያዘ ሕመም ቢሰማትም ባይሰማትም ቀድሞውኑም ክትትል ዋን ስትጀምር የሽንት ምርመራ ስለሚደረግ በጊዜው ሊታወቅ ይችላል፡፡ ነገር ግን የህክምና ክትትላቸውን ችላ የሚሉ ካሉ ሊጎዱ ስለሚችሉ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡  
የአእምሮ ሁኔታ፤
አንዳንድ ሴቶች በእርግዝና ጊዜም ይሁን ከእርግዝናው በሁዋላ የአእምሮ ጭንቀት ወይንም መደበር ይገጥማቸዋል፡፡ የእነዚህም ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ንቃት የሌለው ወይንም ዝቅተኛ እና የሐዘን ስሜት፤
ምንም አይነት የሚያስቁ ወይንም የሚያስደስቱ ነገሮች ቢከሰቱ አለመደሰት፤
ምግብን ለመመገብ ፤መኝታ ወይንም ለምንም ነገር ፍላጎትን ለማሳየት አለመቻል፤
ሁልጊዜ ችግሮች ይከሰታሉ ብሎ ማሰብ፤ለሁሉም ነገሮች ትኩረት ማድረግና ውሳኔ በግል መስጠት፤
እራስን ጠቃሚ እዳልሆኑ አድርጎ ማሰብ፤እፍረት መሰማት፤አጥፍቻለሁ ብሎ ማሰብ፤
ሕይወት ምንም አስፈላጊ ነገር አይደለም ብሎ ማሰብ…ወዘተ
አንዲት እርጉዝ ሴት እንደዚህ አይነት ስሜቶች ከአንድ ሳምንት በላይ ሲኖሩአት ድብርት ውስጥ እንደገባች መገመት ይቻላል፡፡ አንዲት እርጉዝ ሴት ድብርት ሲሰማት ለእራስዋም ሆነ ገና ላልወለደችው ልጅ ምንም አይነት ጥንቃቄ ላታደርግ ትችላለች። በእርግዝና ወቅት ድብርት የሚሰማት ከሆነ ከወለደች በሁዋላም ድብርቱ እንደሚኖራት መገመት ይቻላል፡፡ ስለዚህም ለእ ርጉዝዋ ሴትም ሆነ ላልወለደችው ልጅ አስፈላጊው ሕክምና ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ እርጉ ዝዋ ሴት የእርግዝና ክትትል በምታደርግበት የህክምና ቦታ ስትቀርብ ከሐኪምዋ ጋር በሚገባ መማ ከር ይጠበቅባታል፡፡ ምናልባትም እስዋ እንደችግር ባትቆጥረው እንኩዋን ባለቤትዋ ወይንም በቅ ርብ ያለ ሰው ለሐኪምዋ ሁኔታውን ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ እርምጃ በጤና ወልዶ ጤናማ ልጅ ለማሳደግ ይረዳል፡፡  


Read 12407 times