Saturday, 21 November 2020 10:01

እናትነትና ጤና፡-

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(2 votes)

 በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ የተለያዩ ጤና የማጣት ስሜቶች በእርግዝና ምክንያት የመጡ ስለሆኑ እንደህመም መቆጠር የለባቸውም የሚል አባባል ቢኖርም የሚመከረው ግን ማንኛ ውንም ስሜት ለሐኪም ከመግለጽ መቆጠብ አደገኛ መሆኑ ነው፡፡
በእርግዝና ወቅት በሚኖረው ተፈጥሮአዊ ጫና ምክንያት ያረገዘች ሴት አካልና ስነልቡናን የሚፈታተን ለውጥ መኖሩ ባይካድም ምናልባት ምክንያት ያለው ከሆነ ለእርጉዝዋ ሴት ወይንም ላረገዘችው ጽንስ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል አስቀድሞ መገመት ይገባል፡፡
ባለፈው እትም በእርግዝና ወቅት ስለሚከሰተው የተለያየ የጤና ሁኔታ እ.ኤ.አ August 13, 2020 በNational Center for Chronic Disease Prevention and Health Promotion ድረገጽ ለንባብ የበቃውን ምንጫችን አድርገን የተለያዩ ነጥቦችን አንስተናል፡፡ ጤናማ ልጅ ወልዶ በጤና ለማሳደግ ከእርግዝና በፊት፤ በእርግዝና ወቅት እና ከእርግዝና በሁዋላ ሊከሰት ስለሚችለው የደም ማነስ፤የሽንት ቧንቧ መመረዝ፤መደበር የሚሉትን የተመለከትን ሲሆን በዚህ እትም ደግሞ ሌሎቹን እናስነብባችሁዋለን፡፡
የደም ግፊት፡-
በእርግዝና ወቅት አንዱ አስቸጋሪው የጤና ሁኔታ የደም ግፊት ነው፡፡ በእርግዝና ላይ ያለችው ሴት ከማርገዝዋ በፊትም ይሁን በእርግዝና ላይ እያለች የደም ግፊት ሕመም ሊከሰትባት ይች ላል፡፡ ይህ ህመም በተገቢው መንገድ በሕክምና ካልተረዳ በእርጉዝዋ ሴትም ላይ ይሁን በተረገ ዘው ጽንስ ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህ ኢክላምፕሲያ ፕሪክላምፕስያ በመባል የሚታወቀው በእርግዝና ወቅት የሚከሰተው የደም ግፊት ህመም በተለይም ከህክምና ክትትል ውጭ በሆኑ ሴቶች ላይ በተያያዥነት ሌሎች ሕመሞችንና ጉዳቶች ሊያመጣ ይችላል፡፡
የእንግዴ ልጅ ከማህጸን ግድግዳ መላቀቅ፤
በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የስኩዋር ሕመም፤
ቀኑ ሳይደርስ ልጅን መውለድ፤
ለጨቅላዎች ሞት…ወዘተ ምክንያት ሊሆን ይችላል፤
ለእርጉዝዋ ሴትም ሞት ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡
በእርግዝና ወቅት የስኩዋር ህመም፤
አንዲት እርጉዝ ሴት በእርግዝናው ወቅት ወይንም ቀደም ሲል የስኩዋር ታማሚ ልትሆን ትችላለች፡፡ ስለዚህም እርግዝናን ስታስብ አስቀድሞ ከሕክምና ባለሙያ ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ በእርግዝናው ወቅት የሚከሰት የስኩዋር ሕመም ቢያጋጥምም በምን መንገድ መቆጣ ጠር እንደሚገባ ከባለሙያዎች ምክርና አገልግሎት ማግኘት ተገቢ ይሆናል፡፡ በእርግ ዝናው ወቅት የሚከሰተው የስኩዋር ሕመም ከወሊድ በሁዋላ ሊስተካከል የሚችል ሲሆን ነገር ግን በወደፊት ሕይወት ላይ የስኩዋር ሕመም ሊያጋጥም እንደሚችል እንደማስጠንቀቂያ ስለሚቆ ጠር ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ ፡፡  
የስኩዋር ሕመም በአይነቱ 1 እና 2 እንዲሁም በእርግዝና ወቅት የሚከሰት በመባል ይለያል። በአይነቱ 1 ተብሎ የሚታወቀው የስኩዋር ሕመም ሰውነት ኢንሱሊን የተባለውን ንጥረ ነገር ማምረት ሲያቆም የሚከሰት ነው፡፡ በአይነቱ 2 ተብሎ የሚታወቀው የስኩዋር ሕመም ደግሞ ሰውነት ኢንሱሊንን እያመረተ ነገር ግን በሚገባ አይጠቀምበትም፡፡ ሌላው በእርግዝና ወቅት የሚ ከሰተው የስኩዋር ሕመም ነው፡፡ አንዲት እርጉዝ ሴት የትኛውም አይነት የስኩዋር ሕመም ቢገጥማት ሕይወቱን ያጣ ወይንም ቀኑ ያልደረሰ ልጅ ለመውለድ ሁኔታው ያስገድ ዳታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጽንሱ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና ክብደት እንዲኖረው ሊያደርግ ስለሚ ችል እርጉዝዋ ሴት በምጥ ሳይሆን በቀዶ ሕክምና ልጅዋን እንድትወልድ ሊያስገድዳት ይችላል፡፡ ስለዚህም እርጉዝ ሴት የትኛውም አይነት የስኩዋር ሕመም ቢገጥማት ከሐኪም ክትትል ውጭ መሆን አይገባትም፡፡  
በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኩዋር ሕመም ልጅ ሲወለድ የሚጠፋ ቢሆን እንኩዋን በወደፊት ሕይወት ሊከሰት እንደሚችል አመላካች ነው ይባላል፡፡ ከእርግዝና በሁዋላ በቀሪው የህይወት ዘመን ሊያጋጥም የሚችለው በአብዛኛው 2ኛው አይነት የስኩዋር ሕመም ስለሚሆን ከዚህ የሚከተሉትን ለጥንቃቄ የሚረዱ ድርጊቶችን መፈጸም ይገባል ሲል ድረገጹ ያስነብባል፡፡
2ኛውን አይነት የስኩዋር ሕመም አደጋ ለመቀነስ የሚረዱ ነጥቦች፤-
አንዲት በእርግዝናዋ ወቅት የስኩዋር ሕመም ገጥሞአት የነበረች ሴት ከወለደች በሁዋላ ከ4-12 ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ሐኪምዋን ማማከር ይጠቅማታል፡፡ በዚህ ወቅት የስኩዋር ሕመም ካልታየ ለወደፊቱ ከ1-3 አመት በሚሆን ጊዜ ውስጥ በደም ውስጥ ያለውን የስኩዋር መጠን መታየት ይገባል፡፡
የተመጣጠነ የሰውነት ክብደት እንዲኖር ጥረት ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ ውፍረት ለስኩዋር ሕመም ሊያጋልጥ ስለሚችል ሁልጊዜ ክብደትን መከታተል ይጠቅማል፡፡
በየቀኑ ለ30 ደቂቃ ያህል ቢያንስ በሳምንት ውስጥ ለአምስት ቀናት አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠቅማል ፡፡ ችግር እንኩዋን ቢኖር ሰላሳውን ደቂቃ ለሶስት ጊዜ ከፋፍሎ ለ10-ደቂቃ ያህል በቀን ሶስት ጊዜ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠቅማል፡፡
ጤናማ ምግቦችን መመገብ ሌላው የሚመከር ጉዳይ ነው፡፡ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን መውሰድና ስብ ያለባቸውን ምግቦች በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተገቢ ነው።
ከፍተኛ ውፍረት በእርግዝና ወቅት፤-
አንዲት ሴት ከእርግዝና በፊትም ሆነ በእርግዝናዋ ወቅት ከፍተኛ የሆነ ውፍረት ሲኖራት ለራስዋ ጤንነትም ይሁን ላረገዘችው ህጻን አደገኛነቱ የጎላ ነው፡፡ ከደም ግፊት ጀምሮ በሚያጋ ጥሙ የጤና ችግሮች የተነሳ ሕይወት የሌለው ልጅ መውለድና ከቀዶ ሕክምና ውጭ በተፈጥሮ መንገድ በምጥ መውለድ የማይቻልበት ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ስለዚህ ክብደታ ቸው ከመ ጠን ያለፈ እርጉዝ ሴቶች ከፍተኛ የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ስለሆነ ከመውለዳቸው አስቀድሞ ሆስፒታል ውስጥ አልጋ ይዘው መቆየት ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ከእርግዝና በፊት ክብደትዋን ያስተካከለች ሴት ጤናማ በሆነ መንገድ እርግዝና ጊዜዋን ጨርሳ ጤናማ ልጅ የመ ውለድ እድልዋ ከፍተኛ መሆኑን ባለሙያዎች ይመሰክራሉ፡፡  
Infection (መመረዝ )
በእርግዝና ወቅት ጽንሱ በማህጸን ውስጥ ስለሚገኝ ከብዙ ሕመሞች ማለትም እንደጉንፋን ወይንም የሆድ ሕመም ካሉት ተጠብቆ የሚቆይ መሆኑ እውን ነው፡፡ ነገር ግን አልፎ አልፎ ሊያጋጥሙ የሚችሉ መመረዞች ሊኖሩ ስለሚችሉ ለእናትየውም ይሁን ለተረገዘው ጽንስ ጥንቃቄ ሲባል እጅን መታጠብ፤አንዳንድ ምግቦችን ማስወገድ የመሳሰሉት እርምጃዎች ይጠ ቅማሉ። አንዲት እርጉዝ ሴት ሕመም የሚሰማት ከሆነ በፍጥነት ሐኪምዋን ማማከር ይጠቅማታል፡፡
Morning sickness (እርጉዝ ሴት ጠዋት ጠዋት የሚሰማት ሕመም)
አንዲት እርጉዝ ሴት ጠዋት ጠዋት እንደ ሕመም ባይቆጠርም እንኩዋን ምቾትን የሚያሳጣ ስሜት ሊኖራት ይችላል፡፡ በተለይም በእርግዝናው የመጀመሪያ ሶስት ወር ጠዋት ጠዋት ትው ከት ሊኖራት ይችላል፡፡ ይህ ሕመም በከፋ ደረጃ ጠዋት ጠዋት ብቻ መሆኑ ቀርቶ በማንኛ ውም ሰአት በመከሰት እራስዋን ለመቆጣጠር ከማትችልበት ደረጃ ካደረሳት ሐኪምን መጎብኘት ይጠቅማል። ይህ ሕመም በሕክምና ካልተረዳ እርጉዝዋ ሴት በሰውነትዋ ድርቀትን እና የክብደ ትን መቀነስ ሊያስከትልባት ይችላል፡፡

Read 14190 times