Saturday, 21 November 2020 10:44

አስር የንባብ ሳምንታት ለህጻናት ሊዘጋጁ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   ኢትዮጵያ ሪድስ ዋና ተሳታፊ ይሆናል

           ብሄራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት ኤጀንሲ ከኢጋ ኮሙኒኬሽን ጋር በትብብር ያዘጋጁትና በዋናነት የሕጻናትን ንባብ ለማሳደግ፡ ትኩረቱን ያደረገው“ አስር የንባብ ሳምንት ገበታ ቤተ መጻህፍት” ተጀምሯል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ አምስት የጋራ መኖሪያ መንደሮች በሚካሄደው በነዚህ 10 የንባብ ሳምንት የኢትዮጵያ ሬድስ “ገበታ” የተሰኘው የህዝብ ቤተ መመፃህፍት ዋና ተሳታፊ ሲሆን የንባብ ሳምንቱ ዋና ዓላማ በጋራ መኖሪያ መንደሮች የሚኖሩ ህፃናትን የንባብ ባህል በማዳበር በአዕምሮ በእውቀት የታነፁ ተተኪ ዜጎችን ማፍራት እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡
በዚህ የ10 ሳምንት ዝግጅት ላይ በዋናነት እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሪድስ “ገበታ” ቤተ መፅሃፍት በነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጊዜያዊ ቤተ መፅሀፍት በማኖርና መፅሀፍትን በማቅረብ ልጆች በቦታው ተገኝተው እንዲያነቡ፣ በቤተ-መፃህፍት ባለሙያዎች እንዲነበብላቸውና ወላጆችም ከልጆቻቸው ጋር መጥተው እንዲያነቡ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ  ሪድስ ባለፈው ሳምንት ሶስተኛውን የልጆች የንባብ ፌስቲቫል በቀጨኔ መድሃንያለም ህጻናት ማሳደጊያ  “መፅሐፍት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት ማካሄዱ የሚወስ ነው

Read 13384 times