Saturday, 21 November 2020 10:42

የአሌክስ አብርሃ “ከዕለታት ግማሽ ቀን” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(18 votes)

    እውቁ የወግ ፀሀፊ አሌክስ አብርሃም አምስተኛ ስራ የሆነው “ከእለታት ግማሽ ቀን” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ በሀገራዊ፣ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን የሕይወታችንን ሁለገብ እውነታዎች የፈተሸበት ነውም ተብሏል።
ይሄው መፅሀፍ በደራሲ፣ ሀያሲና መምህር ኃይለመለኮት መዋዕል አርትኦቱ እንደተሰራለትም ታውቋል። በ13 ክፍሎች ተከፋፍሎ በ287 ገፅ የተቀነበበው መጽሐፉ በ180 ብር እና በ40 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ደራሲው ከዚህ ቀደም “ዶክተር አሸብር”፣ “እናት ፍቅር ሀገር”፣ “ዙቤይዳ”፣ እና “አንፈርስም አንታደስም” የተሰኙ ተወዳጅ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡    

Read 16538 times