Sunday, 29 November 2020 14:59

ጤናማ ሕይወት ለመኖር…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

ደካማ የሆነ የአመጋገብ ስርአት ያለው፤የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማያደርግ ሰው እየዋለ እያደረ በከፍተኛ ሁኔታ ሕመም እየተሰማው ሊመጣ ይችላል፡፡ ከዚያም ለሕ መሙ እርምት ማድ ረግ ካል ተቻለ ሕመሙ ወደ ካንሰርነት እንደሚለወጥ የሚያሳይ ስእል ነው የምትመለከ ቱት፡፡ ጥሩ ሕይወት መኖር ማለት ምን ማለት ነው የሚሉት Janet Farrar የፕሮስቴት ካንሰርን ሕመም ለመቀነስለ እንዲያስችል ምርምር ከሚያደርጉት Lorelei Mucci እና June Chan ጋር ምክክር አድርገው ነበር፡፡ በውይይታቸውም ምልከታ ያልተደረገባቸውን አመጋገብ፤እንቅስቃሴ ማድረግና ፕሮስቴት ካንሰር እንዴት ሊገናኙ ወይንም ሕመምተኛ ውን ለመርዳት ይችላሉ የሚለውን ለመመልከት ረድቶአቸዋል፡፡  
ጥሩ ሕይወት መኖር ሲባል የፕሮስቴት ካንሰርን የሚያካትት ላይመስልዎት ይችላል ይላሉ ጠቃሚ ምክሩን ለንባብ ያሉት ባለሙያ፡፡ የፕሮስቴት ካንሰርን ለመከላከል ድጋፍ የሚያደርገው አካል ይህንን ቁምነገር ታነቡ ዘንድ ስለጋበዘ እኛም ወደአማርኛ መልሰነዋል፡፡
አካልንና ስነልቡናን ጤናማ አድርጎ በጤንነት እንዲኖር ለማድረግ የተለያዩ እርምጃ ዎችን ሲወ ስዱ የሚያገኙዋቸው ጥቅሞች በአንድ ነገር የተወሰኑ አይደሉም፡፡ ለምሳሌም ፤-
የአካል ብቃት እን ቅስቃሴ ሲያደርጉ የሰውነት ክብደትን ከመቀነስ ባሻገር ድብርትን ለመከላከል ወይንም እንዳይከሰት ለማድረግ የሚረዳና የፕሮስቴት ካንሰር እንዳይከሰትም ሊያዘገይ ይችላል፡፡
ትክክለኛውንና ጠቃሚ የሆነውን ምግብ መመገብ ሲባል መጠን ያለፈ እና ኬሚካል የበዛባቸውን ምግቦች በማስወገድ የተመጣጠነ ምግብ በመውሰድ ስሜትን በጥሩ ሁኔታ ማደስ፤አቅምን ማጎልበት ጤነኛ የሆነ ስሜትንና እውነታን መፍጠር ይቻላል፡፡
ከፕሮስቴት ካንሰር ጋር በተያያዘ ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ስቃይን ለመቀነስ የሚያስችሉ ምግቦች የሚሰማውን ሕመም ለመቀነስና የፕሮስቴት ካንሰር እድገትን ለማዘግየት እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የሆኑ ሕመሞችን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡ በሌላ በኩል በአመጋገብ ላይ የሚ ደረጉ ጥንቃቄዎች ማለትም ለስኩዋር ሕመም ሲባል ዝቅተኛ የሆነ ስኩዋርን መጠቀም፤ለልብ ሕመም ሲባል የአካል ብቃት እንቅስ ቃሴ ማድረግ የመሳሰሉት ፕሮስቴት ካንሰርንም ጭምር ለመከላከል የሚረዱ መሆናቸውን ማወቅ ጥሩ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
በጤና መኖር በሚለው ሳይንሳዊ ትንታኔ የጤና ችግርን ለማስወገድ አቅም በፈቀደ መጠን ተገቢ የሆነ አመጋገብ ማድረግ ይጠቅማል የሚል ትንታኔ አለው፡፡ የሚከተሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ስብ የበዛባቸው ምግቦች አለመመገብ፤
ስኩዋር ያለባቸውን ምግቦች መቀነስ፤
ቀለማቸው ብሩህ ፤አረንጉዋዴ የሆኑ አትክልቶችን መመገብ፤
ስጋን በመጠኑ መመገብ…ወዘተ
ከላይ የተጠቀሱትን አመጋገቦች እንዳይሰለቹ በማለዋወጥ፣በቀጣይነት እና ሳያዛቡ መመገብ ጠቃሚ ነው፡፡ የምግብን ጥቅምና ካንሰርን ለመከላከል ስለማስቻላቸው ያለውን ምስጢር ያወቀ ሁሉ ምክሩን ለመቀበልና ለመተግበር ይቸገራል የሚል ግምት የለንም ይላሉ ጥናቱን ያቀረ ቡት፡፡
የካንሰርን ሕመም፤ከመጠን ያለፈ ውፍረትን፤የልብ በሽታን እና የስኩዋር ሕመምን ለመከላከል የሚያስችሉ ጠቃሚ ምክሮች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
ቀይ ስጋን በተቻለ መጠን መቀነስ፤ስኩዋር፤በእንዱስትሪ የተዘጋጁ ምግቦችን…ወዘተ ከመውሰድ መቆጠብ፤
የካሎሪ መጠኑ ያነሰ ምግብ መመገብና በተቻለ መጠን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድ ረግ ይጠቅማል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ለክብደት መቀነስ ብቻ ሳይሆን የልብ ሕመምን ለመከላል፤2ተኛውን የስኩዋር ሕመም ለመከላከል፤ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት፤የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በካንሰር እንዳይጠቁ ለማድረግ ይረዳል፡፡ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለካንሰር ሕመም ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሲደረግ በቀን ወይንም በሳምንት ይህን ያህል ደቂቃ የሚለውን በመመልከት ብቻ ከአካል ብቃት ወይንም ከአቅም ውጭ በሆነ መንገድ የሚሰራ አይደ ለም፡፡ የፕሮስቴት ካንሰር ሕመም ያለባቸው ወንዶች በፍጥነት በመራመድ የሚሰሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ወይንም ከህመሙ ጋር የማይመጣጠኑ እስፖርቶችን መስራት አይመከርም፡፡ ስለዚህ እንቅስቃሴውን ከመጀመር በፊት የህክምና ባለሙያን ማማከር ይጠቅማል፡፡
በአመጋገብ ደረጃ እንደ ብሮኮሊ እና የአበባ ጎመን የመሳሰሉትን ምግቦች መጨመር ጥሩ ነው፡፡እነዚህ የምግብ አይነቶች ካንሰር ለመከላከል ወይንም እድገቱን ዝቅተኛ ለማድረግ የሚያግዝ ንጥረ ነገር በውስጣቸው ይገኛል፡፡
በቀን አንድ ወይንም ሁለት ስኒ ቡና መጠጣት ክፉ አይደለም እንደጥናት አቅራቢዎቹ፡፡ በእርግጥ በቡና ውስጥ የሚገኘው ካፊን የተባለው ንጥረ ነገር ጠቃሚ ነው የሚል መደ ምደሚያ ባይኖረውም ቡና ለሞት ምክንያት ነው የሚል ማሳመኛም የለም፡፡ ስለዚህ ከመጠን ሳያልፍ መጠጣት ክፉ አይደለም እንደ መረጃው እማኝነት፡፡
ሲጋራ ማጤስን ማስወገድ ካንሰርን ለመከላከል ይረዳል፡፡ በአለም ላይ በተደረገው ጥናት ወደ 19% የሚሆነውን የካንሰር ሕመም የሚያስከትለው ሲጋራ ማጤስ ነው፡፡ ሲጋራ ማጤስ ሳንባን፤ጉሮሮን፤በአፍ አካባቢዎች ለሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች ምክንያት ስለሚ ሆን ሲጋራውን እራሳችሁ ባታጤሱ እንኩዋን እንደሚያጤሱ የምታውቁዋቸው ሰዎችን ለማስቆም ወደሁዋላ አትበሉ ይላል ጥናቱ ፡፡
አልኮሆልን መጠጣትን መቀነስ የካንሰር ሕመምን ጨምሮ የተለያዩ ሕመሞችን እንዳይከ ሰቱ ለማድረግ ይረዳል፡፡ መጠጣት እንኩዋን ቢያስፈልግዎ በቀን አንድ ብርጭቆ ወይን በቂ ነው ይላል ጥናቱ፡፡ ቀይ ወይን ምናልባትም ካንሰርን የመቋቋም ወይንም የመከላከል ኃይል እንዳለውም ይነገርለታል፡፡
ሕይወትዎን ካለመጨነቅ ዘና ባለ መንገድ መምራት ብልህነት ነው፡፡ ጭንቀትን መቀነስ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ይረዳል፡፡ በጭንቀት ምክንያት ድብርት፤ነገሮችን መርሳት፤ አለአግባብ መወፈር፤የምግብ አለመስማመት፤የልብ ሕመም የመሳሰሉት ሁሉ ሊከሰቱ ስለሚችሉ ጭንቀትን ማስወገድ አስፈላጊ ነው፡፡
አመጋገብን በተመለከተ ጥናቱ ተጨማሪ ያደረገው ምርቶችን በወቅታቸው መመገብ ጤናማ ለመሆን ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ለምሳሌም ፤-የበቆሎ እሸት፤የሽንብራና የባቄላ እሸት ሌሎችንም እንደድንች ቲማቲም ወይም ጎመን የመሳሰሉት ምግቦች ከምርት ላይ ተለቅመው በመደ ርደሪያ ላይ ተቀምጠው ከሚቆዩት ወይንም ለንግድ ከአገር ወደአገር ፀሐይና ብርድ እየተለዋወጠባቸው ከሚመላለሱት ይልቅ ከምርት እንደተለቀሙ መመገብ የተለያዩ ጥቅም እንዳላቸው ጥናት አቅራቢዎች አብራርተዋል፡፡
ከሚገኙት ጥቅሞች መካከል የምግቡ ጣእም የመጀመሪያው ነው፡፡ ምርቱ ተሰብስቦ ወደበላተኛው እስኪቀርብ ድረስ ያለው ጊዜ ረጅም ስለማይሆን አዲስ የሚባል ነው፡፡  
ምግብነቱ ተለቅሞ ረጅም ጊዜ ስለማይቆይ የሚያጣው ነገር ስለማይኖር የተሟላ ይሆናል፡፡ በመጉዋጉዋዝ ምክንያት ለፀሐይ፤ ለብርድ ለመሳሰሉት አደጋዎች አይጋ ለጥም፡፡ ከደረሰበት ቦታም በሚኖረው አጠባበቅና አቀማመጥ ምክንያት የሚያስገኘው ጥቅም አይጎልም፡፡
ጥሩ ጤንነት ለማግኘት፤የተመጣጠነ ምግብ ለማግኘት፤አቅምን ለማገናዘብ የሚረዳ ነው፡፡


Read 11546 times