Saturday, 28 November 2020 00:00

“የታፋኙ ማስታወሻ” ዛሬ በግዮን ሆቴል ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የአንጋፋው ፖለቲከኛ እና የቀድሞው “ግንቦት 7” መሪ አንዳርጋቸው ፅጌ “የታፋኙ ማስታወሻ” መፅሐፍ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ግዮን ሆቴል  በሚገኘው ግሮቭ ጋርደን ዎክ ይመረቃል።
በምረቃው ላይ በመፅሐፉ ዙሪያ ዳሰሳ የሚያቀርቡት የፍልስፍና ምሁሩ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) ሲሆኑ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋና አርቲስት ደበበ እሸቱ በክብር እንግድነት እንደሚገኙ የመርሃ ግብሩ አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይንመንት አስታውቋል።
መድረኩን አርቲስት አዜብ ወርቁ የምታጋፍረው ሲሆን በርካታ የስነ-ፅሁፍ ባለሙያዎችን፣ የስነ-ፅሑፍ አፍቃሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ታዋቂ ሰዎች ይታደማሉ ተብሏል።

Read 854 times