Saturday, 05 December 2020 18:22

December 1/2020…አለም አቀፍ የኤችአይቪ ኤይድስ ቀን፡፡

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(3 votes)

 የኤችአይቪ ኤይድስን ስርጭት ለመግታት ኃላፊነትን በመጋራት አለምአቀፍ ጥምረት ያስፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ኤይድስ መከላከልና ቁጥጥር (Hapco)ያወጣው መረጃ በኢትዮጵያ ያለውን የስርጭት ሁኔታ ያሳያል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የኤችአይቪ ስርጭት በ2020/በመላው አገሪቷ 745‚719 ሲሆን አዲስ በቫ ይረሱ የሚያዙ ሰዎች በ2020/20‚988 ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ በ2020/ ቫይረሱ በደማ ቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች 704‚454 ይሆናሉ፡፡ በኢትዮጵያ እድሜአቸው ከ0-14 የሚ ሆናቸው ህጻናት ላይ ስርጭቱ 37‚103 ነው፡፡በ2020/በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት የተ መዘገበው ሞት መጠን 8‚426  እንደሆነ መረጃው መዝግቦአል፡፡  
እ.ኤ.አ ከ1988/ዓ/ም ጀምሮ በየአመቱ እ.ኤ.አ December 1 በአለም አቀፍ ደረጃ ኤችአይቪ ኤይድስን በሚመለከት የህዝቦች ንቃተ ህሊና እንዲጎለብት የተለያዩ ስራዎች የሚሰሩበት ፤ ባለፈው ታሪክ የኤችአይ ቪ ኤይድስ ስርጭት ምን ይመስል እንደነ በረና ለወደፊትስ ምን መደረግ ይገባዋል የሚለውን በአለም ያሉ ሀገራት ህዝቦች ፤መንግስታት፤ትኩረታቸውን በዘርፉ አድርገው የሚሰሩ ድርጅቶች ፤ የጤና ተቋማት ሁሉ የሚመክ ሩበት እና ሁሌም በየአመቱ የተሻለ አሰራርን እንዲነድፉ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች የሚነደፉበት ነው የአለም የኤይድስ ቀን፡፡
ኤይድስ ሁሉንም የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡ ቀደም ባሉት አመታት ማለትም ቫይረሱ እደተከሰተ አለም ብዙ ህጻናትን እና ወጣቶችን ባጠቃላይም በምርቱ ዘርፍ አስፈላጊ የሚባሉ ሰዎችን አለም ያጣ ችበት እንደነበር አይረሳም፡፡ ስለዚህም ይህ መድሀኒት ወይንም ክትባት ያልተገኘለት ቫይ ረስ የበሽታ መከላያን እያዳከመ በሁሉም የሰው ልጆች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስና ስርጭቱንም ለማስቆም የሚ ያስችሉ ስራዎችን ለመስራት እንዲቻል መነጋገሪያ፤መመካሪያ፤ ፕላን መንደፊያ፤ወደትግበራ መሄጃ…ወዘተ እንዲሆን ታስቦ በየአመቱ የተለየ ቀን ሆኖ እንዲ ታሰብ  የተወሰነ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሕክምናውን በሚመለከት በአለም ላይ ባሉ ሀገራት በሁሉም ደረጃ ለሚገኙ ሰዎች በእኩል ደረጃ እንዲሰጥ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሚነጋገሩበት እለት ይሆናል የአለም የኤችአይቪ ኤይድስ ቀን፡፡
የአለም ኤችአይቪ ኤይድስ ቀን መኖሩ የሚያሳየው የቫይረሱን ስርጭትን በመቀነስ ወይንም ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ የሚከሰት ሞት እንዳይኖር ህብረተሰቡን በማስተማሩ እና የህክምና አገል ግሎት እንዲያገኝ ንቃተ ህሊናውን በማዳበር ረገድ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው ፤ትብብር ወይንም አንድነት እንዲፈጠር፤ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝ ሰዎች ጥሩ ድጋፍ ማድረግ እና ቫይረሱን መቋቋም አቅቷቸው ለህልፈት የተዳረጉትን ለማስታወስ ቀኑ ፋይዳ አለው፡፡ ስለዚህም ኤችአይቪ ቫይረስን በሚመለከት አስፈላጊውን መልእክት እስከመሬት ለማውረድ ጥቅም ላይ ከሚውሉ ሌሎች ቀናት በተጨማሪ በየአመቱ በአገራችን አቆጣጠር ህዳር 22 (December1)  የሚውለው የአለም ኤይድስ ቀን በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ዋና አላማውም ቫይረሱን በሚመለከት የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና ማሳደግ ፤ በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የተዳረጉትን በክብር ማሰብ፤በወደፊት አሰራር የተሻለ የህክምና አገልግሎት ማዳረስ እንዲቻል ከመግባባት ላይ መድረስ፤ስርጭቱን ለመከላከል የሚያስችሉ መንገዶችን ሁሉ ለሰው ልጆች ለማመላከት የሚረዳ ነው፡፡
በ2020 የኤችአይቪ ስርጭት እንዲያበቃ ለማድረግ ኃላፊነትን በመጋራት አለም አቀፍ ጥምረት ያስፈልጋል የሚለው መሪ ቃል በየአመቱ በአለም ላይ የሚከበረው የኤችአይቪ ኤይድስ ቀን በ2020 ሊያደርገው የሚገባውን ኃላፊነት ያሳየ ነው፡፡ የአለም የኤይድስ ቀን በጋራ በመሆን የኤችአይቪን ቫይረስ እንዳይሰራጭ በማድረግ ለማስቆም፤ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸውን ሰዎች በመርዳት እና በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት የተዳረ  ጉትን በክብር ማሰብ የሚቻልበት አለም አቀፍ ቀን ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2020 እንደ መሪ ቃል የተወሰደው ኃላፊነትን በመጋራት አለም አቀፍ ጥምረት ያስፈልጋል ሲባል በአለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው ፤ ሰዎችን ማእከል ያደረገ ኤችአይቪን የመከላከል እና የተሟላ የህክምና አገልግሎትን መስጠትን የሚመለከት እና በዚህም ውጤትን ማስመዝገብ ነው፡፡
መሪቃሉ የሚያሳየው የህብረተሰቡን አቅም ማጎልበት እንዲቻል እና ከስጋቱ ጭርሱንም እንዲድን ማድረግ ሲሆን ሕመሙ ስርጭቱ ተወግዶ ጤናማነት እንዲሰፍን የጤና ተቋማቱም ኤችአይቪን በመከላከሉ ረገድ አሰራራቸውን አጠንክረው ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ የሚጠቁም ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ ኤችአይቪ ምን ይመስላል የሚለውን መረጃዎች አንዳንድ ጠቋሚ መልእክቶችን ጠቅሰዋል፡፡  
ኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭቱን ቢቀንስም ነገር ግን አሁንም ስርጭቱ ያላቆመና በህብረተሰቡ ላይ ጉዳት ማድረሱ አብቅቷል የማይባል መሆኑ ይታያል፡፡ በእርግጥ ኢትዮጵያም በ2020 ስርጭ ቱን በመቀነስ ከሚፈለገው አለም አቀፍ ደረጃ ለማድረስ ከስምምነት የደረሰች መሆንዋ ቢታወ ቅም ምን ያህል ለውጥ እንደተገኘ ለጊዜው ፍተሻ አልተደረገም ይላል WWW.avert.org/global -hiv- and-aids-statistics  ያስነበበው መረጃ፡፡ መረጃው በመቀጠልም፤-
በአለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ በ2018 ወደ 37.9 ቢሊዮን ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ህጻናት ናቸው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኝባቸው 0.8% ከሚሆኑ ሰዎች ውስጥ 21% የሚሆኑት ቫይረሱ በደማቸው መኖሩን የማያውቁ ናቸው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ህጻናት ቁጥር ቀንሶአል ፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 280,000 የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2018 ወደ 160,000 መቀነሱ ተመዝግቦአል፡፡ ከዚህ በመነሳት መረጃው ወደ 41 %ያህል እንደቀነሰና ነገር ግን አሁንም እንደታሰበው የሚያረካ ውጤት አይደለም ይላል፡፡ ስለዚህ ገና በስፋት ሊሰራ የሚገባው መሆኑን መረጃው ይጠቁማል፡፡  
ለአለም የኤችአይቪ ቀን በ2020 ሊሰሩ ይገባቸዋል ተብለው ከተጠቆሙት ነጥቦች ውስጥ የሚከተሉትን CDC’s National Prevention Information Network ጠቅሶአል፡፡
የኤችአይቪ ቫይረስ ስርጭትን መግታት፤ምናልባትም በቫይረሱ መያዝ ቢኖር እንኩዋን ከሕመሙ በፍጥነት ማገገምና የህክምናው ስርአት የሚመክረውን በመተግበር ቶሎ መዳን ይገባል የሚለውን ሁሉም ሊያስበው ይገባል፡፡   
ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ሰብአዊ መብታቸው ተከብሮ በክብርና በጥሩ ጤንነት ሕይወታቸው እንዲቀጥል ለማድረግ እንዲሁም ከሚገቡበት ጭንቀትና  ስጋት ተላቀው ቀሪውን ዘመናቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲመሩ የሚያስችላቸውን አቅም ማጎልበት ይገባል፡፡
ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ላለ ሰዎች አድሎና መገለልን አስወግዶ በችግሩ ዙሪያ ተመሳሳይ የጤና ሁኔታ ካለቸው ሰዎቸ ጋርም ይሁን ከሌላው የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመቀራረብ ግልጽ ውይይት በማ ድረግ መፍትሔ ፍለጋውንና ችግሩን የማስወ ገዱን ተግባር አብረው የሚወጡበትን መንገድ ማመቻቸት ይገባል፡፡
አዳዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች መኖር እስኪቆም ድረስ የምክር አገልግሎት እና ለስርጭቱ መቆም የሚረዳ ቅስቀሳ እንዲሁም የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመንደፍ ተግባራዊ ማድረግ ይጠቅማል፡፡
አድሎና መገለልን ለማስወገድ የተቻለውን ያህል ጥረት ማድረግና ህብረተሰቡም ተገቢውን እውቀት እንዲያዳብር እንዲሁም ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎችም በነጻነትና በግልጽ ማስተማር እንዲችሉ አቅምን ማጎልበት ጠቃሚ ነው፡፡  

Read 15037 times