Saturday, 19 December 2020 10:54

በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች

Written by  በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች
Rate this item
(2 votes)

 በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት የሚተላለፍ በሽታ ሲባል ልክ እንደጸጉር ወይንም ልብስ ላይ በጽዳት ጉድለት ወይንም ከሰው ወደሰው በመተላለፍ ሊፈጠሩ ወይንም ሊራቡ እንደሚ ችሉት (ቅማል) እንደሚባሉት ተባዮች በወንዶችም ይሁን በሴቶች ብልት አካባቢ ባለው ጸጉር ውስጥ ተጣብቀው የሰውን ደም በመምጠጥ የሚኖሩ ተባዮች ሊፈጠሩ ይችላሉ የሚለው ምንጫችን healthline.com ነው። የእነዚህ ተባዮች መኖር ምልክቱ፡-
በብልት ወይንም በመጸዳጃ አካል አካባቢ ማሳከክ ወይንም የመብላት ስሜት፤
በብልት ወይንም በመጸዳጃ አካል አካባቢ በማከክ ምክንያት የሚፈጠሩ ትናንሽ ቀያይ ጠቃጠቆዎች፤
መጠነኛ ትኩሳት ወይንም ኢንፌክሽን፤
አካባቢውን ለመንካት የማይቻልበት ህመም ሊፈጠር ይችላል፡፡
አንድ ወንድ ወይንም ሴት ይህ የሰውነት መቆጣት ወይንም ማሳከክ ሲገጥመው/ማት በብልት ላይ ባለው ጸጉር ውስጥ ቅማሎቹን ወይንም ቅጫሞቹን ለመመልከት ቢሞክር/ ብትሞክር ለማየት ይቻላል። ይህን በእርግጠኝነት ለማመን በአጉሊ መነጽር መጠቀምን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
በወንዶችም ይሁን በሴቶች ብልት አካባቢ የሚፈጠር ተባይ ምክንያቱ ከጽዳት ባሻገር ከሰው ወደሰው በቆዳ ንክኪ ወይንም ልብስን በመዋዋስ፤ አብሮ በመተኛት ወይንም የሰውነት ማድረቂያ ፎጣ በመጋራት ሊሆን እንደሚችል ምንጫችን ያስነብባል። በዚህ ምክንያት ከሰው ወደሰው የሚተላለፈው ተባይ ሰውነትን በሚያሳክክበት ጊዜ በገላ ላይ የሚፈጠረው መሰነጣጠቅ ወይንም መቁሰል ኢንፌክሽን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለዚህም በብልት አካባቢ ባሉ ጸጉሮች ውስጥ የሚፈጠ ረውን ተባይ በፍጥነት ማስወገድ ይመከ ራል፡፡
ባጠቃላይም ሰውነትን በሚገባ ማጽዳት፤ ልብሶችን መቀቀልና በሚገባ ማጽዳት፤ አልጋን እና ፎጣ የመሳሰሉትን ነገሮች ሁሉ ማጽዳት፤ ቤትን በሚገባ ማጽዳት፤ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት እንዳይተላለፍ ጉዋደኛን ወይንም የትዳር አጋርን ሁኔታ መገምገምና የጽዳት እርምጃውን መውሰድ፤ በህክምናው ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት በትክክል መጠቀም ይገባል፡፡
በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ ከሚባሉት በሽታዎች መካከል protozoan በሚባሉት ተፈጥሮዎች ከሰው ወደሰው በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፈው በሽታ የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል፡፡
ከሴት ወይንም ከወንድ ብልት ፈሳሽ መታየት፤
በወንድ ወይንም በሴት ብልት አካባቢ የማቃጠል ወይንም የማሳከክ ስሜት፤
ሽንት በመሽናት ወይንም የግብረስጋ ግንኙነት በሚደረግ ወቅት ጥሩ ስሜት ማጣት ወይንም ሕመም፤
ቶሎ ቶሎ ሽንትን መሽናት መፈለግ፤
በተለይም ሴቶች ፈሳሽ ከብልታቸው በመሚወጣበት ጊዜ አሳ አሳ የሚል መጥፎ ሽታ ይኖረዋል፡፡ በጊዜው ሕክምና ካላገኘ ሕመሙ ወይንም ኢንፌክሽኑ እስከማህጸን ይደር ሳል፡፡
በአማርኛው ቋንቋ ጨብጥ፤ ቂጥኝ፤ ከርክር…ወዘተ በሚል ይታወቁ የነበሩና ሌሎችም በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች የህመም መከላከያን በመውሰድ በቀላሉ ሊድኑ የሚችሉ በሽ ታዎች መሆናቸውን ምንጩ ይገልጻል፡፡ በእርግጥ ለመዳን የሚያስ ቸግሩ መኖራቸውን ጠቁሞ ከእነዚህም ውስጥ በሳይንሳዊ ስያሜያቸው HPV፤ HIV፤ herpes፤ የሚባሉ መሆነቸውን ይጠቁ ማል። በእርግጥ ለመዳን አስቸጋሪ ቢሆንም ህመሙ እንደተሰማ ወደሕክምና በመሄድ ወደባሰ ደረጃ እንዳይደርስ ማድረግና ሕመምን ለመቀነስ እንዲሁም ወደሌሎች ለማስተላለፍ እድል እንዳይኖር ለማድረግ ይቻላል፡፡
በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፍ በሽታ በእርግዝና ወቅት ወደ ጽንሱ ወይንም ልጁ ገና ሲወለድ ሊተላለፍ እንደሚችል ምንጭ ያደረግነው መረጃ ይገልጻል፡፡ ገና የተወለዱ ልጆች ሕመሙ የተለያዩ የጤና ችግሮችን ሊያስከትልባቸው የሚችል ሲሆን በሕይወት ዘመናቸው የህክምና እርዳታን የሚሹበት ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ እንደዋነኛ መፍትሔ የሚወሰደው እርጉ ዞች በህመሙ ምንም ምልክት እንኩዋን ባይኖራቸው ምርመራ በማድረግ ውጤቱን ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜም እርጉዝዋ እናት በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚከሰት ሕመም ቢታይባት አወላለድዋ በቀዶ ሕክምና እንዲሆን እና የሚወለደው ልጅ ላይ ሕመሙ እንዳይተላለፍ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል፡፡
በግብረ ስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ ሕመሞችን ለማስወገድ እንደ በሽታዎቹ አይነት ይለያያል፡፡ ዋናው መፍትሔ ግን ግንኙነቱን የሚያደርጉት ሰዎች ከመነካካ ታቸው በፊት ስለጤንታቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የጤና ምርመራ ማድረጋቸው ነው፡፡ ያ ካልሆነ ሕመሙን አንዳቸው ለአንዳቸው ይቀባበሉታል፡፡
አንድ ወንድ ወይንም ሴት ምርመራ በማድረግ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላ ለፍ በሽታ እንዳለባቸው ካወቁ በተቻለ ፍጥነት ሕክምና ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ አንዱ አይነት በሽታ መኖሩ ከተረጋገጠና በጊዜው ካልታከመ ሌላም አይነት ሕመም ሊያስከትል እንደሚችል ማወቅ ይገባል፡፡ በግብረስጋ ግንኙነት ከሚተላለፉት ሕመሞቹ አንዳንዶቹ በጊዜው ካልታከሙ አስከፊ ወደሆነ የጤና ችግር ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ በጊዜው ሕክምና ያላገኙት ሕመሞች ጊዜው ካለፈ በሁዋላ ቢታከሙም የማይድኑ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደንብ ሕክምና ከተደረገ ሕመሙ ከስር መሰረቱ ስለሚወገድ ፍጹም ጤነኛ መሆን ይቻላል፡፡
የህክምና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር እና የህክምና አገልግሎት በትክክል በመጠቀም በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ በሽታዎችን ጭርሱኑ ማስወገድ የሚቻል ሲሆን በባለሙያዎቹ ከሚሰጡት ምክሮች መካከል ግንኙነቱን የማድረግ ባህርይን የሚመ ለከት ይገኝበታል፡፡ ለምሳሌም ሕመሙ እስኪድን ድረስ የግብረስጋ ግንኙነትን ማስወገድ ወይንም እንደ ኮንዶም መጠቀም የመሳሰሉ የመከላከያ መንገዶችን የህክምና ባለሙያ ዎች ይመክራሉ፡፡
በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚከሰቱ ሕመሞች ጭርሱንም እንዳይከሰቱ ለማድረግ ዋናው መፍትሔ ጭርሱንም ግንኙነቱን አለማድረግ ነው። ነገር ግን ይህ በማይቻልበት መንገድ በሕክምና ባለሙያዎች ምክር መሰረት መከላከያዎችን መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ኮንዶም በፈሳሽ መልክ የሚተላለፈውን ኢንፌክሽን ከአንዱ ወደአንዱ እንዳይተላለፍ ይቆጣጠራል ቢባልም ቆዳ ለቆዳ በሚኖረው ንክኪ ግን የሚተላለፈውን ሊከላከል አይችልም፡፡
ጥንዶች አብረው የሚኖሩ ከሆኑ አንድ ላንድ በሚለው መርህ መሰረት መከባበር እና ከሌላ ጋር ግንኙነትን አለማድረግ እንዲሁም ጽዳትን በሚገባ መጠበቅ ፤ስለጤንነታቸውም ትኩረት ማድ ረግ የሚመከር ሲሆን አዲስ የተገናኙ ከሆኑ ደግሞ ሁለቱም ግንኙነት ከማድረጋቸው በፊት የህክምና ምርመራ በማድረግ የራሳቸውን ጤንት ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ምርመራ በሚያደር ጉበት ወቅት ስለግብረስጋ ግንኙነት ሕመም መኖር አለመኖር ማወቅ እንደሚ ፈልጉ ተናግረው ውጤቱን መቀበል እና ቀጣዩን እርምጃ መውሰድ አለባቸው፡፡ በዚህ መንገድ ሕመሙን ከራስ ወደሌላ ሰው ማስተላለፍ አይኖርም፡፡
በወንዶች ላይ በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ ሕመም ምልክት፤
ሕመሙ አንዳንድ ጊዜ ምልክት አይኖረውም። አንዳንድ የህመሙ አይነቶች ግን ምልክት የሚኖራቸው ሲሆን በወንዶች በኩል የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሽንት በመሽናት ወይም ግንኙነት በማድረግ ግዜ ምቾት ማጣት፤ ሕመም መሰማት፤
ያልተለመደ ፈሳሽ ወይንም ደም በብልት በኩል መታየት እና የመሳሰሉት፤ በሴቶች በኩል ምልክቶቹ፤
በወንዶቹ የተጠቀሱት እንዳሉ ሆነው በሴቶች በኩል በብልት አካባቢ ማሳከክን ፤መጥፎ ሽታ ያለው ፈሳሽ እና መቁሰልን ይጨምራል፡፡

Read 13607 times