Saturday, 26 December 2020 17:38

(COVID-19) … እርግዝና …. እና … ጨቅላዎች…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 ይህ ጽሁፍ በተዘጋጀበት እለት ማክሰኞ ታህሳስ 13/2013 ወይም እ.ኤ.አ Dec 22/2020 በወጣው መረጃ በ አለም ላ ይ 7 7,394,940 በ ኮሮና ቫ ይረስ የተያዙ ሲሆን 1,703,164 ሞተዋል፡፡ 43,663,983 ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡ በኢትዮጵያ ደግሞ 120,348 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 1,861 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል፡፡ 103,681 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፡፡ ይህ ቁጥር ጽሁፉ እስኪዘጋጅ ድረስ የነበረ ሲሆን በየእለቱ ግን የሚ ለዋወጥ ነው፡፡ COVID-19 ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ ሳይሆን አንዳንድ አገሮች ላይ እንዲያ ውም ችግሩ እንደገና እያገረሸበት በመሆኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች እንደገና እንዲወ ሰዱ በማስገደድ ላይ ነው፡፡ በዝርያው የተለየ የተባለ የኮሮና ቫይረስም በእንግሊዝ አገር እንደተገኘና ዜናውም አስደንጋጭ በመሆኑ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ለአለም ህዝቦች እየተነገረ ነው፡፡ COVID-19 ክትባቱን ለመጀመር ሀገራት እየተዘጋጁ … ህዝቦች ደግሞ በናፍቆት እየጠ በቁ መሆኑ የየእለቱ መረጃ የሚገልጸው እውነታ ነው፡፡ በሽታን የመከላከልና መቆጣጠር ማእከል CDC እንዳወጣው መረጃ ከኮሮና ቫይረስ(COVID-19) ጋር በተያያዘ በእርግዝና ጊዜ ምን መደረግ እንዳለበት እንዲሁም ጡት በማጥባት ወቅት እና ለተወለዱ ጨቅላዎች ወይንም ገና ለተወለዱ ልጆች ምን ማደረግ ይገባል የሚለውን እንደሚከተለው ምክሩን ይለግሳል፡፡ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ይበልጥ ለቫይረሱ ተጋላጭ ናቸው የሚል መረጃ ለጊዜው ባይኖርም በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ካላረገዙት ይልቅ በተለያየ የጤና መጉዋደል ወይንም የአቅም ማጣት ሊቸገሩ እንደሚችሉ ከእውነታው ተነስቶ መገመት ይቻላል። እርግዝና በሂደቱ አዲስ ተፈጥሮአዊ ክስተት ስለሆነ በሰውነት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና መቁዋቁዋም ላረገዘ ችው ሴት
ከባድ ሲሆን ሌላ ተጨማሪ ወረርሽኝ ሲገጥማት ደግሞ ምን ያህል እንደሚከብዳት መገ መት አያስቸግርም፡፡ በእርግዝና ላይ ያለች ሴት በኮሮና ቫይረስ ብትያዝ ችግሩ በራስዋ ላይ የሚያበቃ ሳይሆን ጽንሱም ሲወለድ ሊደርስ የሚችል ነው፡፡ አንዲት እርጉዝ ሴት ከሌላው ሰው በተለየ መንገድ የኮሮና ቫይረስ ሊይዛት አይችልም የሚል ምንም ማረጋገጫ ስለሌለ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ በእርግጥ ቫይረሱ እርጉዝ ስለሆነች በተለየ ሁኔታ ይይዛታል ማለት ባይሆንም በእርግዝናው ምክንያት በተፈጥሮአዊ መንገድ የሚደርሱባት የአካል እና የስነልቡና ድካሞች ለቫይረሱ ለመጋለጥ ተጨማሪ መንገድ እንዳይፈጥሩ መጠንቀቅ ተገቢ ነው ይላል የበሽታን የመከላከልና መቆጣጠር ማእከል CDC መረጃ፡፡ መረጃው አክሎም ከብዙ ሰዎች ጋር በቅርብ በተገናኙና ለረጅም ጊዜ ግንኙነታቸውን ካለጥንቃቄ በቀጠሉ ቁጥር በቫይረሱ ላለመያዝ እና ለሌሎች ላለማስተላለፋቸው ምንም ምክንያት የለም፡፡
አንዲት ሴት በእርግዝና ላይ ከሆነች ለራስዋ ለጥንቃቄ ከምትወስዳቸው እርምጃዎች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
• አንዲት እርጉዝ ሴት ከቤት ውጭም ሆነ በቤት ውስጥ ከምታገኛቸው ሰዎች ጋር ግንኙነትዋን በተቻለ መጠን መገደብ ይገባታል፡፡ በተለይም ከቤት የሚወጡና ከሰዎች ጋር ሰፋ ያለ ግንኙነት ያላቸው የቤተሰብ አባላት ከእርጉዝዋ ሴት በተቻለ መጠን እራቅ ማለት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አንዲት እርጉዝ ሴት ከቤት መውጣት ስትፈልግ ወይንም ሰዎች ከውጭ ወደቤትዋ ሲመጡ ልታገኛቸው ብትፈልግ ማድረግ የሚገባት ጥንቃቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
• የአፍንጫ እና አፍ መሸፈኛ mask ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በተለይም እርቀትን ለመጠበቅ ከማይ ቻልበት ሁኔታ ውስጥ ከሆነች በምንም ምክንያት mask ከፊትዋ ላይ ማንሳት የለባትም፡፡ የአ ፍና አፍንጫ መሸፈኛው በሌላ በምንም እይነት የጥንቃቄ መውሰጃ መንገድ የማይተካ ወይንም የማይለወጥ ነው። ለምሳሌ እጅን መታጠብ በመሳሰሉት ማለት ነው፡፡
• ሌሎች በአቅራቢያ የሚኙ ሰዎች የአፍንጫ እና አፍ መሸፈኛ ከሌላቸው በተቻለ መጠን እንዲያደርጉ መጠየቅ ወይንም ማስታወስ ይገባል፡፡ የማያደርጉ ከሆነ እራስን ማራቅ ተገቢ ነው፡፡
• አንዲት እርጉዝ ሴት ከቤትዋ ውጭ ከሌሎች ሰዎች ጋር ስትገናኝ ቢያንስ ቢያንስ 6 ጫማ ያህል መራራቅ ይገባታል፡፡
• እጅን በሳሙናና በውሀ ቢያንስ ቢያንስ ለ20 ሴኮንድ በደንብ አድርጎ መታጠብ ጠቃሚ ነው፡፡ ሳሙናና ውሀ በማይገኝበት ጊዜ ቢያንስ ቢያንስ 60% አልኮሆል ያለው ሳኒታይ ዘር ወይንም ማጽጃ እጅን ማጽዳት ይገባል፡፡
• መራራቅን ለመፍጠር አስቸጋሪ የሚሆን አንዳንድ እንቅስቃሴ ወይም ማህበራዊ ተሳትፎ ቢኖር ጉዳዩን አለመሳተፍ ወይም እራስን ማራቅ ይገባል፡፡
አንዲት እርጉዝ ሴት በራስዋ ከምትወስደው የጥንቃቄ እርምጃ በተጨማሪ ወደሕክምና ተቋም መሄድ እንዳለባት መርሳት የለባትም፡፡ የህክምና ክትትልን በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በሁዋላ ማድረግዋን መቀጠል ይገባታል፡፡ በሕክምና ባለሙያ የሚሰጡትን ቀጠሮዎች በሙሉ አክብሮ ወደ ጤና ባለሙያው መቅረብ ለአንዲት እርጉዝ ሴት እና ላረገዘችው ጽንስ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ በድንገት የህክምና አገልግሎት ማግኘት የሚያስፈልግበት ሁኔታ
ቢከሰት በቅርብ ወደሚገኝ የጤና ተቋም መሄድ ተገቢ ነው፡፡ ጤናማ ሆኖ እርግዝናውን እንዴት መቀጠል እና ለጽንሱም ምን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ
እና በጥሩ ሁኔታ ለመውለድ ቦታ ስለመምረጥም ይሁን ማንኛውንም ስለእራስዋ ደህንነት ያሉአትን ጥያቄዎች ምንም ሳትፈራ ክትትል የሚያደርግላትን
የህክምና ባለሙያዋን መጠየቅ ይገባታል፡፡ ምንጊዜም በጤና ተቋም በሰለጠነ ሰው እጅ ልጅን መውለድ አማራጭ የማይኝለት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል፡፡
• የጤና ተቋማቱ በ COVID-19 ምክንያት ለህክምና የሚቀርቡትን እና ሌሎች ወይም ቫይረሱ ያልያዛቸውን የሚመረምሩበት ወይንም ሕክምና የሚሰጡበት ደረጃ ሊለያይ ይችላል፡፡
• አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች የታካሚዎቻቸውን የቀጠሮ ቀን ለሌላ ጊዜ ሊያስተላልፉ ይችላሉ።
• ሌሎች ደግሞ በታካሚዎቻቸው ቀጠሮ መሰረት የሚከታተሉአቸውን እርጉዝ ሴቶች በስልክ በመሳሰሉት መንገዶች በማነጋገር ሕክምናውን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ይህ ውሳኔ እንደአገራቱ ወይንም እንደአካባው ሁኔታ ወይንም እንደታካሚው የጤና ሁኔታ የሚወሰን ወይም ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡
በእርግዝና ጊዜ ጉንፋን ወይም ፍሉ የሚባለው በመተንፈሻ አካል አካባቢ የሚከሰት ሕመም ሊያጋጥም ይ ችላል፡፡ ይ ህ ህ መም ከ ተለየያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን በተለይም ከሰው ወደሰው የሚተላለፍ ነው፡፡ ፍሉ ወይንም ጉንፋን ህመሙ የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃና በኮሮና ቫይረስ ከሚከሰተው ህመም ጋር በመጠኑ ተመሳሳይነት ቢኖረውም ነገር ግን አንድ አይነት አይደሉም፡፡ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ገና ለመጀመር በዝግጅት ላይ ያለ ሲሆን ፍሉ ለሚባለው ሕመም ግን ክትባቱ አለ፡፡ ስለዚህ ማንኛዋም እርጉዝ እናት ይህንን ክትባት ማግኘትዋ ጠቃሚ ይሆናል፡፡
• አንዲት እርጉዝ ሴት የ COVID-19 ቫይረስ ይዞኛል ብላ ካሰበች በአስቸኳይ ወደሕክምና መሄድ አለባት፡፡
• በእርግዝናው ወቅትም ይሁን ከእርግዝና በሁዋላ ድብርት ይዞኛል ብላ ካሰበች ሐኪምዋን ማማከር ይጠበቅባታል፡፡
• አንዲት እርጉዝ ሴት በምንም ምክንያት ሐኪም ማግኘት አለብኝ ብላ ካሰበች ችላ ማለት የለባትም፡፡ ለጨቅላዎች የሚደረገውን እንክብካቤ በቀጣዩ
እትም እናስነብባችሁዋለን፡፡


Read 11641 times