Saturday, 26 December 2020 17:40

ክብርት ኮማንደር ደራርቱ በስፖርቱ አመራር እየተሳካላት ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(1 Vote)

 • ለሚቀጥሉት 4 ዓመታት አትሌቲክሱን እንድትመራ በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች
   • በኮቪድ ወቅት የአትሌቲክሱን ማህበረሰብ በሙሉ ሃላፊነት አስተባብራለች
   • ለቶኪዮ ኦሎምፒክ 6 እና 7 ወራት ዝግጅት ያስፈልጋል ብላ ተቀባይነት አግኝታለች
   • በረጅም ርቀት ሩጫ በትራክ ፣በአገር አቋራጭ ፣ በጎዳና ላይ ሩጫ እንዲሁም በማራቶን ፈርቀዳጅ እና ወርቃማ ታሪኮችን ያስመዝገበች ናት፡፡ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በኦሎምፒክ አስገኝታለች፡፡
   • በ10ሺ ሜ 2 የኦሎምፒክ የወርቅና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎች የተጎናፀፈች በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 1 የወርቅና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎች የወሰደች ናት፡፡ በአጠቃላይ በሩጫ ዘመኗ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን፤ አንድ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን፤ ሁለት ጊዜ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮን፤ ሁለት ጊዜ የአህጉራት ዋንጫ ሻምፒዮን፤ አንድ ጊዜ የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮን እና ሁለት ጊዜ
የአፍሪካ አትሌቲክሰ ሻምፒዮን ነበረች፡፡
  • በዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና 12 ሜዳልያዎች 6 የወርቅ፤ 5 የብርና 1 የነሐስ ሜዳልያ ስትጎናፀፍ በ3 ታላላቅ ማራቶኖች በለንደን ፣ በቶኪዮና በኒውዮርክ ከተሞች ድል ያደረገችም ናት፡፡
  • ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ ፤ ከጅማ ዩኒቨርሰቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዎች የተቀበለች ሲሆን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበር በ2019 ምርጥ የአትሌቲክስ ሴት ሆና ልዩ ሽልማቷን ወስዳለች፡፡


              ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ከ2 ሳምንታት በፊት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባካሄደው 24ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝደንት ሆና መመረጧ ይታወሳል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በፌደሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንትነት ያገለገለች ሲሆን በኮቪድ ወቅት በአትሌቶች ህልውና፤ ማህበራዊ ግንኙነት የተጋረጡ አደጋዎች የሚታደጉ እንቅስቃሴዎችን በማስተባበር፤ የአትሌቲክስ ማህበረሰቡ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ
እንዲኖረው በማነሳሳት አስደናቂ አስተዋፅኦ ነበራት፡፡ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በእጩነት ስትቀርብ “ያልተበረዘ፣ ያልተነካ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ማንነት ያላት ኢትዮጵያዊት” ተብሎ መገለጹን ያመለከተው ፌደሬሽኑ፤ የጉባኤው አባላት በሙሉ ድምፅ ያለምንም ተቃውሞ
ለፕሬዝዳንትነት እንደመጧት በመግለጫው አመልክቷል፡፡ ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በዋና ፕሬዝዳንትነት የምትመራ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌደሬሽን ምክር ቤት አባልነት እና በምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል
ፕሬዝዳንትነት እንደምትሰራ ይታወቃል። በኢአፌ የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ የሆነው ስለሺ ብሥራት ለስፖርት አድማስ እንዳብራራው ክብርት ኮማንደር ደራርቱ በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ፌዴሬሽኑን በመራችባቸው አስደናቂ የስፖርት አመራር ብቃቷን አስመስክራለች፡፡ ባለፉት ሁለት
ዓመታት በስፖርት ማዘወተርያ ስፍራዎች ላይ መሰራቱን የጠቀሰው ባለሙያው፤ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት፤ ከለገጣፎ ከንቲባና ከአትሌቶች ማህበር ጋር በትብብር በመስራት የለገጣፎ አትሌቲክስ ማዕከል ሰሞኑን መመረቁን አስቀድሞ ጠቅሷል፡፡ በሌላ በኩል አጠቃላይ የፕሮጀክት ሂደቱ ከ5 ዓመታት በፊት የተጀመረ ቢሆንም፤ ከአዲስ አበባ መስተዳድር የከንቲባው ፅህፈት ቤት ጋር በመነጋገር ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ዋና መስርያ ቤት በሚገኝ መሬት ላይ
ለተጨማሪ የስፖርት መሰረተ ልማት የመሰረት ድንጋይ እንዲጣል ማድረጓንም ገልጿል፡፡ በዋናነት ደግሞ ከኮሮና ጋር በተያያዘ የተሰሩ ስራዎች የኮማንደር ደራርቱ ቱሉን የአመራርነት ሚና እንደሚያሳይ የኮምኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያው ለስፖርት አድማስ ያስረዳል፡፡ በኮሮና ወቅት የኢትዮጵያ አትሌቶች ከፍተኛ
ጭንቀት የገቡበትን ሁኔታ በማስተዋል ከሶስት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ከዋልታ፤ ከኢቢሲ እና ከኢቤስ ጋር በመሆን በቀጥታ ለአትሌክሱ ባለድርሻ መድረስ ያለባቸውን መረጃዎች እና ግንዛቤዎች እንዲቀርቡ አመቻችታለች፤ ከብሄራዊ ቡድን አትሌቶች አንስቶ፤ በየክልሉ ያሉ ችግረኛ አትሌቶች በወረርሽኙ
የደረሰባቸውን ተፅእኖ በማጥናት ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንዲሰጥ አድርጋለች፡፡ ለችግረኛ አትሌቶች እነ መሰረት ደፋር አልማዝ አያና እና ሌሎችም ህንፃቸውንና ሌሎች ድጋፎችን እንዲሰጡም የኮማንደር ደራርቱ ሚና የላቀ ሲሆን የአትሌቲክስ ማህበረሰቡ በደም ልገሳ እንዲሳተፍም አስተባብራለች፡፡ በአጠቃላይ በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ዘመኗ የኮቪድ ወረርሽኝ መከሰቱ በስፖርቱ ላይ መከናወን የነበረባቸውን የልማት እና የእድገት ስራዎች ቢያጓትትም የፌደሬሽኑን ማህበራዊ ሃላፊነት ከመወጣት አንፃር የሚመሰገን ተግባር ማከናወኗን አውስቷል፡፡ በሌላ በኩል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለሁለት ዓመት በተከታታይ መላው የአትሌቲክስ ቤተሰብ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው መስራቷ ሲታወቅ በአገራዊ ጉዳዮች ማለትም በተለያዩ ክልሎች መፈናቀል ለደረሰባቸው ወገኖች ፌደሬሽኑ ድጋፉን እንዲሰጥ ሰርታለች ነው ያለው፡፡
ከቶኪዮ ኦሎምፒክ ጋር በተያያዘ እንደ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ኦሎምፒያኖች ጤንነታቸው አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከጅምሩ በሆቴል መገባት እንደሌለባቸው አቋሟን በማንፀባረቅ ከፍተኛ ውሳኔ ማሳለፏን የጠቀሰው የኮምኒኬሽን ባለሙያው የኮቪድ ወረርሽኝ አደገኛ ምዕራፎች ካለፉ በኋላ በአሁኑ ወቅት
ለሚደረገው ዝግጅት ወደ ሆቴል በቶሎ የሚገቡበትን እቅድ ማቅረቧንም ለስፖርት አድማስ አስታውቋል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የፌደሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ የስምንት ዓመት የስትራቴጂ እቅድ መተዋወቁን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በተለይ ከመንግስት ተቋማት ከትምህርት ሚኒስትር፤ በክልል ከሚገኙ
የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ጋር በሚደረጉ ስራዎች አትሌቲክሱን ወደ ከፍተኛ የእድገት አቅጣጫ በመውሰድ የመጀመርያውን አራት አመት የስራ ዘመን ለኮማንደር ደራርቱ አመራር የተሰጠ ሃላፊነት ሆኗል፡፡ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በሚኖራት ተሳትፎ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የአትሌቲክስ ፌደሬሽኑ ያቀደ ሲሆን ለዚህም አትሌቶች ቅድመ ዝግጅታቸውን 6 እና 7 ወራትን ቀደም ብለው ወደ ሆቴል በመግባት እንዲያከናውኑ በኮማንደር ደራርቱ ለጠቅላላ ጉቤ የቀረበው ምክረ ሃሳብ ሙሉ ድጋፍ ማግኘቱም ተናግሯል፡፡ ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ አሁን 48ኛ ዓመቷ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከሩጫ ውድድር ከ9
ዓመት በፊት ከወጣች በኋላ በኢትዮጵያ ስፖርት አጠቃላይ እንቅስቃሴ በባለድረሻ አካልነትና በአመራር ሰጭነት ስታገለግል ነው የቆየችው፡፡ ከስፖርቱ ባገኘችው ስኬት ወደ ኢንቨስትመንት በመሰማራት ስኬታማ የሆነችና በአገራዊ አጀንዳዎች ተሰሚነት ያላት ሆና ቆይታለች። ባለፉት ጊዜያት አትሌቲክስ ፌደሬሽኑን የተለያዩ አማተር አገልጋዮች ከሠራዊቱ ቤትና ከልዩ ልዩ ተቋማት ፌዴሬሽኑን በበጎ ፈቃደኝነት በመምራት አሁን ያለበት ደረጃ ማድረሳቸውን
በድረገፁ የሰፈረ መረጃ ያመለክታል፡፡ ወ/ሮ ብሥራት ጋሻውጠና ከ1994 ዓ. ም. በኋላ እስከ 2004 ዓ. ም. ማብቂያ ድረስ ያገለገሉ ብቸኛዋ ሴት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ነበሩ፤ እርሳቸውን ተክተው እስከ 2009 ዓ. ም. መጀመሪያ ድረስ አቶ አለባቸው ንጉሴ ፌዴሬሽኑን የመሩ ሲሆን ከመንግስት ተቋማት ከሚመጡት ወኪሎች ይዘውት የነበሩትን የፕሬዝዳንትነትን ኃላፊነት ወደ ስመ ጥርና ታዋቂ አትሌቶች ያዛወረ ክስተት በተፈጠረበት የ2009 ዓ.ም ምርጫ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ከ2009 ዓ. ም – ህዳር 2011 ፕሬዝዳንት ሆኖ ፌዴሬሽኑን መርቷል። ከህዳር 2011 ዓ. ም. ጀምሮ ክብርት ኮማንደር
አትሌት ደራርቱ ቱሉ kፍተኛ አመራርነቱን ይዛ ቆይታለች፡፡ ፌደሬሽኑ ከዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር፣ ከአዲዳስ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ፣ ከአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን፣ ከምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅንና ከአቻ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት ጋር መልካም የሚባልና በአርዓያነት ሊጠቀስ የሚችል ግንኙነት ያደርጋል፡፡ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) አባል በመሆን ሲመዘገብ፣ ከተወሰኑ ጊዜያት በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን (CAA) እና በምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን (EAAR) ውስጥ ከካውንስል አባልነት ባለፈ በአመራርነት እየተሳተፈ ነው፡፡ በትውልዷ በአርሲዋ ትንሽ ከተማ በቆጂ የሆነችው ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ለኢትዮጲያዊያን ብቻ ሳይሆነ ለአፍሪካዊያን እንስት አትሌቶች ፈርቀዳጅ የሆኑ ድሎችን በአለም አ ቀፍ ደ ረጃ በ ማስመዝገብ ታ ሪክ ሠርታለች፡፡ በተለይ ደግሞ የሚጠቀሰው በ1992 እ.ኤ.አ በስፔን ባርሴሎና በተከናወነው ኦሎምፒክ በ10ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ መጎናፀፏ ሲሆን፤ ይህ ድሏ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የኦሎምፒክ ታሪክ በረጅም ርቀት በሴቶች የወርቅ ወደ ኦሎምፒክ መድረክ የተመለሰችበትን ሁኔታ ከማድመቃቸውም በላይ ነጭና ጥቁር በሚል የነበረውን መከፋፈል ዋጋ ቢስ ባደረገ
ደስታቸው የማይዘነጋ ተእይንት አሳይተዋል። በሌላ በኩል በ2000 እኤአ በአውስትራያ በተካሄደው የሲድኒ ኦሎምፒክም ደራርቱ በ10ሺ ሜትር ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለመጎናፀፍ ስትበቃም በ10ሺ ሜትር ታሪክ አስደናቂ ድል የተባለ ነው፡፡ በዚያ ኦሎምፒክ ላይ ለድል የበቃችው የዓለማችንን ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች በማሸነፍ ሲሆን ከ1 እስከ 6ኛ ደረጃ ያገኙት ኦሎምፒያኖች በኦሎምፒክ ሪከርድ ፍጥነት ውድደሩን መጨረሳቸው
ተደጋግሞ ይወሳል፡፡ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአራት ኦሎምፒኮች ማለትም በ1992 ባርሴሎና፤ በ1996 አትላንታ፤ በ2000 ሲድኒ እንዲሁም በ 2004 እ ኤአ በ አቴንስ ኦ ሎምፒክ በ10ሺ ሜትር ከታዩ ምርጥ ኦሎምፒያኖች አንዷ ስትሆን ከሁለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያዎቿ ባሻገር በ1996 አትላንታ ላይ በ4ኛ ደረጃ ዲፕሎማ በ2004 እኤአ አቴንስ ላይ በ3ተኛነት የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች። ከኦሎምፒክ ባ ሻገር በ አለም አ ትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፏዋ 1 የወርቅና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎች የወሰደች ሲሆን በዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና 12 ሜዳልያዎች 6 የወርቅ፤
5 የብርና 1 የነሐስ በመሰብሰብ በከፍተኛ የውጤት ክብረወሰን ከታላላቆቹ ተርታ ትጠቀሳለች፡፡ በአጠቃላይ በሩጫ ዘመኗ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን፤ አንድ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን፤ ሁለት ጊዜ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮን፤ ሁለት ጊዜ የአህጉራት ዋንጫ ሻምፒዮን፤ አንድ ጊዜ የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮን እና ሁለት ጊዜ የአፍሪካ አትሌቲክሰ ሻምፒዮን ነበረች፡፡ በ10ሺ ሜትር ትራክ ላይ ከነበራት ስኬት በኋላ ወደጎዳና ላይ ሩጫ ከ ገባች በ ኋላ በ 3 ታ ላላቅ ማ ራቶኖች በለንደን፣ በቶኪዮና በኒውዮርክ ከተሞች ድል ያደረገችም ናት፡፡ ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከጅማ ዩኒቨርሰቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዎች የተቀበለች ሲሆን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበር በ2019 ምርጥ የአትሌቲክስ ሴት ልዩ ሽልማቷን ወስዳለች፡፡ ሜዳልያ የተገኘበት የመጀመርያው ድል ነበር። በዚህ ኦሎምፒክ ላይ በሁለተኛ ደረጃ የብር ሜዳልያ ከተጎናፀፈችው የደቡብ አፍሪካዊቷ ኤለና ማየር ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው የአፍሪካን ድል በልዩ ሁኔታ ማብሰራቸውን የዓለም የስፖርት ቤተሰብ በአድናቆት ያስታውሰዋል፡፡
ሁለቱ አፍሪካውያን ለዓለም ህዝብ ባሳዩት ፍቅር ከአፓርታይድ መታገድ በኋላ ደቡብ አፍሪካ ወደ ኦሎምፒክ መድረክ የተመለሰችበትንሁኔታ ከማድመቃቸውም በላይ ነጭና ጥቁርበሚል የነበረውን መከፋፈል ዋጋ ቢስ ባደረገደስታቸው የማይዘነጋ ተእይንት አሳይተዋል።በሌላ በኩል በ2000 እኤአ በአውስትራያበተካሄደው የሲድኒ ኦሎምፒክም ደራርቱበ10ሺ ሜትር ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያለመጎናፀፍ ስትበቃም በ10ሺ ሜትር ታሪክ አስደናቂ ድል የተባለ ነው፡፡ በዚያ ኦሎምፒክ ላይ ለድል የበቃችው የዓለማችንን ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጮች በማሸነፍ ሲሆን ከ1 እስከ 6ኛ ደረጃ ያገኙት ኦሎምፒያኖች በኦሎምፒክ ሪከርድ ፍጥነት ውድደሩን መጨረሳቸው ተደጋግሞ ይወሳል፡፡ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአራት ኦሎምፒኮች ማለትም በ1992 ባርሴሎና፤ በ1996 አትላንታ፤ በ2000 ሲድኒ እንዲሁም በ 2004 እ ኤአ በ አቴንስ ኦ ሎምፒክ በ10ሺ ሜትር ከታዩ ምርጥ ኦሎምፒያኖች
አንዷ ስትሆን ከሁለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያዎቿ ባሻገር በ1996 አትላንታ ላይ በ4ኛ ደረጃ ዲፕሎማ በ2004 እኤአ አቴንስ ላይ በ3ተኛነት የነሐስ ሜዳልያ አግኝታለች። ከኦሎምፒክ ባ ሻገር በ አለም አ ትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፏዋ 1 የወርቅና 1 የነሐስ ሜዳሊያዎች የወሰደች ሲሆን በዓለም አገር
አቋራጭ ሻምፒዮና 12 ሜዳልያዎች 6 የወርቅ፤ 5 የብርና 1 የነሐስ በመሰብሰብ በከፍተኛ የውጤት ክብረወሰን ከታላላቆቹ ተርታ ትጠቀሳለች፡፡ በአጠቃላይ በሩጫ ዘመኗ ሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮን፤ አንድ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን፤ ሁለት ጊዜ የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮን፤ ሁለት ጊዜ የአህጉራት ዋንጫ ሻምፒዮን፤ አንድ ጊዜ የዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮን እና ሁለት ጊዜ የአፍሪካ አትሌቲክሰ ሻምፒዮን ነበረች፡፡ በ10ሺ ሜትር ትራክ ላይ ከነበራት ስኬት በኋላ ወደጎዳና ላይ ሩጫ ከ ገባች በ ኋላ በ 3 ታ ላላቅ ማ ራቶኖች በለንደን፣ በቶኪዮና በኒውዮርክ ከተሞች ድል ያደረገችም ናት፡፡ ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከጅማ ዩኒቨርሰቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪዎች የተቀበለች ሲሆን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበር በ2019 ምርጥ የአትሌቲክስ ሴት ልዩ ሽልማቷን ወስዳለች፡፡ ባለፉት 30 ዓመታት በኦሎምፒክ እና በዓለም ሻምፒዮና የአትሌቲክስ የውድድር መድረኮች በወርቅ ሜዳሊያዎች ኢትዮጵያን ሲያኮሩ የቆዩት አትሌቶች በኢንቨስትመንት ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ ክብርት ኮማንደር ደራርቱ ለዚህም ፈርቀዳጅ ስትሆን አዲስ አበባ ውስጥ ባለ 15 ፎቅ ህንፃ ከመገንባቷም በላይ በአሰላና አዳማም በሆቴል እና የንግድ ህንፃ ግንባታ ላይ እየሰራች ነው፡፡


Read 957 times