Saturday, 09 January 2021 12:07

የክቡር አካለወርቅ ሀብተወልድን ግለታሪክ የያዘ ሲዲ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን የተዘጋጀውና የክቡር አካለወርቅ ሀብተወልድን የህይወትና የስራ ታሪክ የሚያስቃኘው የኦዲዮና ቪዲዮ ሲዲ ዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ረፋድ 3፡00 ላይ በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ ይመረቃል።
የ80 ደቂቃ ርዝመት ያለው ይሄው ግለ ታሪክ አገራቸውን በአርበኝነት፣ በትምህርት ሚኒስትርነት፣ በእርሻ ሚኒስትርነትና በፍርድ ሚኒስትርነት በትጋት ሲያገለግሉ የቆዩትን ነገር ግን ያልተዘመረላቸውን የአገር ባለውለታ የልጅነት፣ የትምህርትና የስራ ዘመን የሚያስቃኝ ሲሆን በግለታሪኩ ዝግጅት ላይ የተለያዩ ግለሰቦች፣ ጓደኞቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በምስክርነት መካተታቸውን የተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ገልጿል። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የባለ ታሪኩን ቤተሰቦች ጨምሮ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙም ታውቋል።
ተወዳጅ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለፉት አራት ዓመታት የበርካታ የአገር ባለውለታዎችን ግለታሪክ ወደ ድምጽ በመቀየር ያቀረበ ሲሆን እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ የ1000 የኢትዮጵያ ባለውለታ ተቋማትና ግለሰቦችን ታሪክ በድምፅ ዶክሜንተሪ የመስራት እቅድ እንዳለው አስታውቋል።

Read 796 times