Saturday, 09 January 2021 12:21

“አራቱ ጓደኛሞችና ሌሎች” የተረት መፅሐፍ ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በታዳጊዋና ትንሿ ደራሲ ህሊና ወድነህ የተደረሰውና “አራቱ ጓደኛሞችና” ሌሎችም የተሰኘው  የተረት መፅሐፍ ነገ ጥር 2 ቀን 2012 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መፃሕፍት ኤጄንሲ አዳራሽ ይመረቃል።
በዕለቱ በርካታ ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች የሚቀርቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፣ በርካታ የልጆች መፅሐፍ በሳተመው ደራሲ ዳንኤል ነጋሽ አጭር የመፅሀፍ ዳሰሳ፣ ተሰጥኦ ባላቸው ህፃናት የሚቀርብ የንባብና ዘፈን ዝግጅት፣ በገጣሚና ደራሲ ታገል ሰይፉ የሚቀርብ አጭር ዲስኩርና ግጥም፣ የመፅሐፍ ግምገማ በዓለም ካሉ ትንንሽ ደራሲዎች አንፃር በደራሲ ውድነህ ክፍሌና የክላርኑት ጨዋታ በዳዊት ፍሬው ሀይሉ፣ በዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን መስራች ቢኒያም ከበደና ደራሲዋ ህሊና ውድነህ ለልጆች የሚሰጥ የመፅሐፍ ስጦታና በቢኒያም ከበደ የሚደረግ የመዝጊያ ንግግር በዕለቱ መርሃ ግብር ውስጥ ተካትተዋል።
የትንሿ ደራሲ ይሄው የተረት መፅሐፍ በ30 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል።

Read 11263 times