ልጅ- አባዬ፣ አንድ ጥያቄ ብጠይቅህ ትመልስልኛለህ?
አባት- በደንብ እንጂ ልጄ። ምንድን ነው ጥያቄህ?
ልጅ- /ፖለቲካ/ ምንድን ነው?
አባት- ደህና። እንዲገባህ በምሳሌ ላስረዳህ።
ለምሳሌ፡- የእኛን ቤተሰብ እንደ አንድ ሀገር ብንወስድ። እኔ ለሀገሩ ገንዘብ የማገኝ ሰው ነኝ። እኔን የአሰሪዎችን መደብ እንደምወክል አድርገህ አስብ። እናትክን ደሞ ገንዘቡን ቦታ ቦታ እያስያዘች የምትመራ ናት እንበል። እሷን መንግስት ብለህ ጥራት። ሁለታችን የአንተን ጥቅምና ፍላጎት የምናሟላልህ ስለሆነ፣ አንተ ደግሞ ህዝብ ትባላለህ ማለት ነው። የቤት ሰራተኛችንን፣ የሰራተኛው መደብ ብለን እንጠራታለን።
ትንሹን ወንድምህን ደሞ የነገው ትውልድ እንለዋለን። አሁን ገባህ/ፖለቲካ/ ማለት?
ልጅ- የለም አባዬ፤ በደንብ የገባኝ አልመሰለኝም። ትንሽ ላስብበት እስቲ።
* * *
የዚያኑ ዕለት ማታ ቤተሰቡ ሁሉ ተኝቶ ሳለ ልጁን የትንሽ ወንድሙ ለቅሶ ከእንቅልፉ ይቀሰቅሰዋል። ምን ሆኖ እንደሚያለቅስ ለማረጋገጥ ወደ ህፃኑ ሄዶ ቢያይ፤ የሽንት ጨርቁ እንዳለ ርሷል። ይሄንኑ ሊያስረዳ ወደ እናትና አባቱ መኝታ ቤት ሄደ። እናቱ ለጥ ብላ እንቅልፏን ትለጥጣለች። ከዛ ወደ ቤት ሰራተኛቸው መኝታ ክፍል ሄደና አንኳኩቶ አልከፍት ስላለችው፣ በበሩ ቀዳዳ አሾልቆ ሲያይ፣ አባቱ ሰራተኛዋን አቅፎ ይታገላል። ቢያንኳኳም ጨርሶ የሚሰሙት አልሆነም። ስለዚህ ልጁ ተስፋ ቆርጦ ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ ተኛ።
በማግስቱ።
ልጅ- አባዬ አባዬ፤ /ፖለቲካ/ ማለት አሁን ገባኝ፤ መሰለኝ- አለው።
አባት- በጣም ጥሩ የኔ ልጅ። በል እስቲ አስረዳኝ።
ልጅ- አየህ አባዬ፤ የአሰሪዎች መደብ የሰራተኛውን መደብ ያንገላታዋል! መንግስት ለጥ ብሎ ተኝቷል፡፡ ህዝብ ግራ ገብቶታል። የነገው ትውልድ ከእነ መፈጠሩም ተረስቷል። ይሄው ነው /ፖለቲካ/ ማለት::
Published in
ጥበብ
Latest from Administrator
- የእስራኤል እና የኢራን ፍጥጫ
- Insights on Israel's Response: Interview with Mr. Tomer Bar-Lavi, Chargé d’Affaires at the Embassy of Israel to Ethiopia
- Barr, a vocal Trump critic, says he will ‘support the Republican ticket’ in November
- Iran president warns of ‘massive’ response if Israel launches ‘tiniest invasion’
- "አልሞቷል" ፊልም ዛሬ በዓለም ሲኒማ ይመረቃል