Saturday, 23 January 2021 14:39

ጥቂት አንቀፆች ለቅምሻ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  “የግንቦት ንፋስ ጉልበተኛ ነው… አውሎ ንፋስ ነው… በዚህ አውሎ ንፋስ ውስጥ በዝግታ የሚራመዱ እግሮች ይመጣሉ… አቧራ በጋረደው አየር ውስጥ ደብዘዝ ያለ ገፅታቸውን ልብ ብለህ ለማየት አይንህን መግለጥ አለብህ… አቧራውን ፈርቼ አይኔን እጨፍናለሁ… ካልክ ግን ድንገት አጠገብህ ደርሰው ያስደነግጡሃል… የድንጋጤህ ከፍተኛነት ደሞ ምንም ማድረግ እንድትችል እድል አይሰጥህም… እናም ረጋ ብሎ አንተን ድምጥማጥህን የማጥፋቱ ተራ የእነሱ ይሆናል…
ከርቀት ታጥበው የተሰጡ ልብሶች ታያለህ… ደርቀው ከመግባታቸው በፊት ወድቀው ይጨቀያሉ… በራሳቸው እርጥበትና በመሬቱ አቧራ…
… ወደ ትላልቅ መስኮቶች ቀና ያልክ እንደሆነም አዛውንቶችን ታያለህ… መስኮቱ አጠገብ ቆመው ሀይለኛው አውሎ ንፋስ የሚያናውጠውን አለም በስጋት ያያሉ… ይፈራሉ… ደመና በሌለው ሰማይ ላይ የሚጋልብ አውሎንፋስ በጣም ይፈራሉ… እየፈሩም… ይሄ መንግስት ይቺን ክረምት ያልፍ ይሆን?... እያሉ ራሳቸውን ይጠይቃሉ…”

Read 727 times