Saturday, 30 January 2021 16:05

“ራያ ኮንሰርት” ነገ በቆቦ ከተማ ይካሄዳል /ኮንሰርቱ እስከ 3 ሚ.ብር ይጠበቃል/

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በኢትዮ ሚዲያ ኤቨንትና በራያ ቆቦ አካባቢ ወጣቶች የተዘጋጀውና ገቢው ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች የሚውለው “ራያ ኮንሰርት” ነገ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም  በቆቦ ከተማ ይካሄዳል፡፡
እንደ አዘጋጆቹ ገለፃ ከኮንሰርቱ እስከ 3.ሚ ብር የሚጠበቅ ሲሆን፣ ገቢው በአንበጣ መንጋ ሰብላቸው ሙሉ ለሙሉ ለወደመባቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች፣በጅምር የቀረው የራያ የባህል ማዕከል ዳግም ወደ ግንባታ እንዲገባ የማነቃቂያ ድጋፍ እንዲሁም በጥረታቸው እስከ ብሔራዊ ሊግ ለደረሱት የቆቦ ከነማ እግር ኳስ ለመደገፍ እንደሚውል ከኮንሰርቱ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ እንየው ቢሆነኝ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
በኮንሰርቱ ላይ ድምጻዊያኑ መሰረት በለጠ (ጉምጉም)፣ በውቀቱ ሰው መሆን ኑርአዲስ ሰይድ፣ ዱባለ መላከ(ጉዱገና) ዮኒ ጎንደርኛና ሌሎችም እንደሚያቀነቅኑ ጋዜጠኛው ጨምሮ ገልጿል፡፡ የመግቢያ ትኬቶቹ ዋጋ መደበኛው 50 ብር ሲሆን ቪአይፒ 100 ብር እንደሆነና ይህን በጎ አላማ የሚደግፍ ሁሉ ትኬቶቹን እየገዛ ለዘመድ ወዳጅ በመጋበዝ አላማው ግቡን እንዲመታ ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Read 848 times