Saturday, 30 January 2021 16:06

“ማነው?” ፊልም ማክሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የደራሲና ዳይሬክተር ስንሻው ሹምዬ “ማነው” ፊልም ማክሰኞ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል።
በቆንጆ ምስሎችና በቢንጎ ፒክቸርስ በጋራ የተሰራውና ልብ አንጠልጣይ ዘውግ ያለው ፊልሙ 90 ደቂቃ ርዝመት ያለው ሲሆን በአንድ ቤተሰብ የወንጀል ታሪክ ላይ ያጠነጥናል ተብሏል።
በ”ላምባ” ፊልም እውቅናን ያገኘችው ወጣቷ ተዋናይ ሊዲያ ሞገስና በ”አሉላ አባነጋ” ቴአትርም ሆነ በሌሎች በርካታ ፊልሞች ተቀባይነት ያገኘው ወጣቱ ተዋናይ ሔኖክ ዘርዓብሩክ በመሪ ተዋናይነት የተወኑበትና ሌሎችም አንጋፋ ወጣት ተዋንያንን የተሳተፉበት “ማነው”? ፊልም በታሪክ አወቃቀር፣ በምስልና ድምፅ ጥራት  ደረጃውን ጠብቆ የተሰራ ሲሆን ማክሰኞ አመሻሽ ላይ አንጋፋ አርቲስቶች፣ ፊልም አፍቃሪዎች፣ መንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት በድምቀት እንደሚመረቅ የፊልሙ ደራሲና ዳሬክተር አስታውቋል።


Read 10951 times