Saturday, 06 February 2021 12:22

“ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ትገደዳለች”

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(6 votes)

     ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል

        ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር ላይ በፈጸመችው ወረራ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱንና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ በፈጸመው ወረራ በርካታ ገበሬዎች መፈናቀላቸውን ፣ሃብት ንብረታቸው መዘረፉንና የሞት ጉዳት ማጋጠሙን የተናገሩት አምባሳደሩ ሃገሪቱ ጦሯን በአፋጣን በወረራ ከያዘችው ግዛት የማታስወጣ  ከሆነ ኢትዮጵያ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ትገደዳለች ብለዋል፡፡
ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ የፈፀመችው ወረራ ከህግም ሆነ  ሁለቱ ሃገራት ካላቸው የቆየ ጉርብትና አንጻር ታሪካዊ ስህተት መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፤ በሁለቱ ሃገራት መካከል በ1972 የተፈረመውን የድንበር መርህ ስምምነት የጣሰ ድርጊት ነው ብለዋል።
ሱዳን  ድርጊቱን የፈጸመችው  መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ህግ የማስከበር ተግባር ላይ መሆኑን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እንደሆነ ያስታወሱት አምባሳደሩ፤ ይህም ወዳጅን ከጀርባ የመውጋት ድርጊት ነው ሲሉ ነቅፈዋል፡፡
የሃገሪቱ ሰራዊት በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ለቆ እንዲወጣና ድርድር እንዲካሄድ የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ እየጠየቀ ሲሆን የሱዳን መንግስት በበኩሉ፤ የያዝኩትን አለቅም በሚል አቋሙ ፀንቷል፡
ሱዳን በወረራውበ አካባቢዎች የሚገኙ 16 ያህል ባለሃብት አርሶ አደሮች በወረራው ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት እንደወደመባቸው መዘገባችን አይዘነጋም፡፡  


Read 13403 times