Print this page
Saturday, 06 February 2021 12:26

ፕሮስቴት ተፈጥሮአዊ አካል ነው፡፡

Written by  ፀሀይተፈረደኝከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

    በዚህ እትም ወንዶችን ስለሚገጥማቸው የፕሮ ስቴት ካንሰር ደረጃ እና አጠቃላይ የህመም ምል ክቱ ምን እንደሚመስል መከላከያውንና ዘር በማፍራት በኩል የሚኖረውን ተጽእኖ እናስነብባ ችሁዋለን፡፡ ወንዶች በብልታቸው አካባቢ ፕሮስቴት የሚባል ተፈጥሮአዊ እጢ አላቸው፡፡ ይህ እጢ በእድሜ ወይንም ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ እና በተ ለያዩ ምክንያቶች ሕመም ሲገጥመው በፍጥነት ወደሕክምና ካልተሄደ ህመሙ ተባብሶ ወደካንሰርነት የመለወጥ እድሉ ከፍተኛ እንደሚሆን የተለያዩ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡  አመጋገብ፤ ለአልኮሆል መጋለጥ፤ በተ ለያዩ ምክንያቶች ለኬሚካል መጋለጥ፤ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፤ በግብረስጋ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፍ መመረዝ (infections) የመሳሰሉት ሁሉ ወንዶችን ለፕሮስቴት ካንሰር ያጋልጣሉ፡፡ ሕመሙ በቤተሰብ ውስጥ ከነበረ በዘር የመተላለፍ እድል እንደሚኖረውና እዲሁም አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዘር ማለትም ጥቁር ወይንም ነጭ በመሆን ደረጃ ህመሙ የሚብ ስትና ቀለል የሚልበት ደረጃ አለ፡፡ በዚህም ጥቁሮች ላይ ሕመሙ እንደሚጨምር ያሳያል፡፡ በአጠቃላይም 50% የሚሆኑ ወንዶች እድሜአቸው 50 አመት ሲደርስ ሕመሙ ሊከሰት ይች ላል፡፡ ምንጫችን prostate cancer foundation የተባለው ሲሆን ስለ ፕሮስቴት ካንሰር በሰ ፊው የተለያዩ ነጥቦችን የሚያቀርብ ድረገጽ ነው፡፡
የፕሮስቴት ካንሰር ያለበትን ደረጃ አስቀድሞ ማወቅ ታካሚዎች መውሰድ የሚገባቸውን ጥን ቃቄ እና ማድረግ የሚገባቸውን ሕክምና ሊጠቁማቸው ይችላል፡፡ ህመሙ ያልገጠማቸውም አስቀድሞ ክትትል ለማድረግ ይረዳቸዋል የሚል እምነት አለ፡፡
ደረጃ (0) የሚባለው የካንሰር ሴል ከመራባቱ በፊት ያለው ጊዜ ሲሆን አለ ቢባልም እንኩዋን በጣም ትንሽ በሚባል ደረጃ ነው፡፡ ይህም በቀላሉ ታክሞ የሚድን ነው፡፡
ደረጃ (1) የሚባለው የካንሰር ደረጃ የካንሰር ሴሉ ፕሮስቴት በሚባለው እጢ ላይ ብቻ የሚገኝ ሲሆን ውጤታማ በሆነ የህክምና እርዳታ ሙሉ በሙሉ መዳን የሚቻልበት ደረጃ ነው፡፡
ደረጃ (2-3) የሚባለው የካንሰር ሴሉ በአቅራቢያው ወደ አሉ አካባቢዎች ተሰራጭቶ የሚገኝ ነው፡፡
ደረጃ(4) የሚባለው  የካንሰር ደረጃ ከፕሮስቴት እጢው አካባቢ ጀምሮ በሰውነት ውስት እንደ ሳንባ ወይንም አጥንት አካባቢ ጭምር ተሰራጭቶ ሲገኝ ነው፡፡
አብዛኛውን ጊዜ የፕሮስቴት ካንሰር ሴሉ ከመሰራጨቱ በፊት ሊደረስበት ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ባላሰለሰ መንድ ጊዜያቸውን ጠብቀው ህክምና ለሚያደርጉ ሰዎች ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን የካንሰር ሴሉ መራባት እንደጀመረ ብዙም ምልክቱን ላያሳይ ይችላል፡፡ ከመጀመሪያው ደረጃ ላይ ባለበት ጊዜ ምልክት ባያሳይም ውሎ አድሮ ግን ካንሰር መከሰቱን የሚያሳዩ የተለያዩ ምልክቶች አሉ፡፡ ከእነሱም ውስጥ፤-
ሽንት የመሽናት ችግር፤ ሊሸኑ ሲፈልጉ በጣም በዝግታ ቀስ እያሉ ለመሽናት መታገል፤ በተለ ይም በምሽት ቶሎ ቶሎ ሽንት የመምጣት ሁኔታ…
ሽንትን ለመሽናት በሚያስፈልግ ደረጃ መግፋት አለመቻል፤
ሽንትን ሸንቶ ሲጨረስ አብቅቷል ብሎ ለማቋረጥ መቸገር፤
በሽንት ውስጥ ወይንም በፈሳሽ ውስጥ የደም ምልክት መታየት፤
ለወሲባዊ ግንኙነት የብልት መነሳት ችግር፤
በጀርባ ወይንም በወገብ ላይ እንዲሁም በደረት አካባቢ ወይም በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ ሕመም የመሰማት፤
በእግር ወይንም በቅልጥም ላይ ድክመት መታየት የመሳሰሉት ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
በእርግጥ እነዚህ ምልክቶች ሙሉ በሙሉ የፕሮስቴት ካንሰር ምልክቶች ናቸው ብሎ መደም ደም አይቻልም፡፡ የፕሮስቴት እጢ ሕመም ከካንሰር ውጪ መሆኑ በሚታመንበት ደረጃም ሊሰሙ የሚችሉ ምልክቶች ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን ወደሕክምና በመሄድ መመርመር እና ደረጃውን ማወቅ እንዲሁም ካንሰር ከመከሰቱ በፊት በህክምና ባለሙያዎች ምክር መሰረት መድህን መፈለግ ተገቢ ነው፡፡
ዘር በማፍራት በኩል የፕሮስቴት ካንሰር የሚያስከትለው ድክመት መኖሩን መረጃችን ይጠቁ ማል፡፡ ፕሮስቴት የተባለው እጢ ለወንዶች ዘር ለማፍራት አስተዋጽኦ የሚያደርግ አካል ነው። ስለሆነም ይህ አካል በካንሰር ሲያዝ የካንሰር ሕመሙና ህመሙን ለማዳን ሲባል በሚወሰዱት የተለያዩ የህክምና እርዳታዎች ምክንያት ዘር የማፍራት ተግባሩ ሊጎዳ ይችላል፡፡
ሕመሙ በማጋጠሙ ምክንያት የፕሮስቴት እጢ በቀዶ ሕክምና በሚወገድበት ጊዜ የዘር ፈሳሽ semen እና ፍሬው የሚመረትበትን ሁኔታ ሊያውክ ይችላል፡፡
የጨረር ሕክምና የፕሮስቴት እጢን አካል ሊጎዳ …የዘር ፍሬ የሚገኝበትን sperm ሊያጠፋ አለዚያም የዘር ፍሬውን የሚያጉዋጉዘውን semen የተባለውን ፈሳሽ መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡
የሆርሞን ሕክምናው fertility ልጅ የማፍራት እድልን ሊያውክ ይችላል፡፡  
የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩ ከታወቀና ወደሕክምና የሚኬድ ከሆነ ሕክምናውን ከመጀመር በፊት ልጅ መውለድ የሚፈልጉ ከሆነ አስቀድሞ ሊያደርጉት የሚቻላቸው ምክር የሚከተለውን ይመ ስላል፡፡
ከቀዶ ሕክምናው በፊት የዘር ፍሬን በህክምና ተቋማት ባንክ ማስቀመጥ
የዘር ፍሬን sperm በማፍሰስ በላቦራቶሪ በአርተፊሻል መንገድ ልጅ ማግኘት የሚቻልበትን እድል መሞከር ይቻላል፡፡
ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ልጅ የማግኘት እድልን እውን ከማድረግ ውጪ የፕሮስቴት ካንሰር ሕክምናን እና ልጅ የማግኘት ፍላጎትን ማስታረቅ አስቸጋሪ መሆኑን ባለሙያዎቹ ይመ ሰክራሉ፡፡ ስለዚህ ሕክምናውን ከማድረግ አስቀድሞ ከቤተሰብ እና ከሕክምና ባለሙያው ጋር በጥብቅ መመካከር ይጠቅማል፡፡
የፕሮስቴት ካንሰርን ለመከላከል የሚያስችሉ መንገዶችን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ነገር ግን አደጋውን ሊቀንሱ ይችላሉ የተባሉ አንዳንድ ጠቃሚ ሀሳቦችን ምንጫችን እንደ ሚከተለው ዘርዝሮአል፡፡
በአትክልትና ፍራፍሬ የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፤
ስብ የበዛባቸውን ምግቦች ማስወገድ፤
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመደበኛው ሕይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ማለትም በኑሮ ወይንም በስራ ማካተት አለዚያም ሆን ብሎ ለእንቅስቃሴው ጊዜ መመደብ፤
የክብደትን መጠን መቆጣጠር፤
አልኮሆል መጠጣትንና ማጤስን ማስወገድ ይገባል፡፡
ከላይ የተመለከቱት ጥንቃቄዎች ካልተደረጉ ችግሮች መከተላቸው አይቀርም፡፡
የፕሮስቴት ካንሰር በሌሎች በአካባቢው ባሉ አካላት ማለትም በሽንት ፊኛ አካባቢ ሊሰራጭ ይችላል፡፡
ለሰውነት የማይጠቅሙና ፀረ ሰውነት የሆኑ ማለትም እንደፕሮስቴት ካንሰር ያሉ ህዋሳትን አጣርተው የሚያስወግዱ lymph nodes የተባሉ አካላት በካንሰሩ ሊጠቁ ይችላሉ፡፡
ሽንትን የመቆጣጠር ችግርን ሊያስከትል ይችላል…ወዘተ፡፡

Read 13487 times