Saturday, 06 February 2021 13:35

“የድንቁርና ጌቶች" ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲና ሃያሲ ብርሃኑ ደቦጭ የተፃፈው “የድንቁርና ጌቶች” የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ትያትር ይመረቃል። በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ፕ/ር ዓለማየሁ ገዳ፣ ዶ/ር ዳዊት ወንድምአገኝን ጨምሮ ሌሎች ምሁራንና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚታደሙ ይጠበቃል። በ389 ገፆች የተቀነበበው “የድንቁርና ጌቶች”፤ በ200 ብር ነው ለገበያ የቀረበው፡፡
ደራሲው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የሚታተሙ የተለያዩ መፃህፍትን አርትዖት በማድረግ እንዲሁም በታሪካዊና ፖለቲካዊ መፃሕፍት ላይ በሚያቀርባቸው ሂሳዊ መጣጥፎች  ይታወቃል።    

Read 1690 times