Monday, 08 February 2021 00:00

“መግደል መሸነፍ ነው” ሐሙስ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አንጋፋ መምህር በሆኑት ዶ/ር መሃመድ ሀሰን የተጻፈውና በአገሪቱ ወቅታዊ እውነታዎች ላይ የሚያጠነጥነው “መግደል መሸነፍ ነው” የተሰኘ መፅሐፍ ከትላንት በስቲያ በብሔራዊ ቴአትር ተመርቋል፡፡
በመጽሀፉ ላይ ዳሰሳና ንግግር በማቅረብ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ በድሉ ዋቅጅራ( ዶ/ር)፣ ረ/ፕ ነብዩ ባዬ፣ መምህር ዮናስ ዘውዴና ደራሲና ጋዜጠኛ አጥናፍ ሰገድ ይልማ ተሳትፈዋል፡፡ በምርቃቱ ላይ በልዩ እንግድነትና ተናጋሪነት  ከታደሙት መካከል መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ኢ/ር ሐሰን በድሉ፣ አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይገኙበታል፡፡  
በተጨማሪም በተስፋሁን ከበደ (ፍራሽ አዳሽ)፣ በተወዛዋዥ ገጣሚ ኤፍሬም መኮንን (ኤፊ ማክ) ደግሞ ግጥም በውዝዋዜ የቀረበ ሲሆን ገጣሚ ናሁ አስተሰራዬ ፅጌም ግጥም ማንበቡን የምርቃት ሥነሥርዓቱ አዘጋጅ ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን አስታውቋል፡፡

Read 9378 times