Saturday, 20 February 2021 00:00

የቅዱስ ያሬድን ህይወትና ታሪክ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ነገ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በኢትትዮጵያ ብሎም በምድራችን የመጀመሪያው የዜማ ሊቅ እንደሆነ የሚነገርለት የቅዱስ ያድን ስራ ህይወትና ታሪክ የሚያሳይ ዘጋ ፊልም ነገ እሁድ ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በኢንተር ኮንቴኔንታል ሆቴል ይመረቃል።
የዘጋቢ ፊልሙ አዘጋጅ ኮሚቴዎች እንደገለጹት፤ ዘጋቢ ፊልሙ የተሰራው ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከአማራ ክልል መንግስትና ከሌሎች አካላት በተገኘው ሀሳብ ድጋፍ ነው።
የዜማ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በ6ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (ከ1 ሺህ 500 ዓመታት በፊት) የሰራቸውና የፈጠራቸው የዜማ ስልቶችና ኖታዎች ዛሬም ድረስ አገልግሎት ላይ ያሉ ቢሆኑም፣ ሊቁ በኣለም ላይ አቻ ያተገኘለት ፈር ቀዳጅ ሆኖ ቀጥሏል።
ነገር ግን ተገቢውን ትኩረት፣ እውቅናና ክብር አለማግኘቱ የሚቆጭ ነው ያሉት የዘጋቢ ፊልሙ አዘጋጅ ኮሚቴዎች፤ የዚህ ሊቅ ክብርና ሞገስ ከፍ እንዲል ዘንድ ዘጋቢ ፊልሙ መስራቱን ያስረዳሉ። ሰርቶ ለማጠናቀቅም አራት ዓመት መፍጀቱን ተናግረዋል።  

Read 12929 times