Print this page
Tuesday, 23 February 2021 00:00

በአለማችን የመጀመሪያዋ በራሪ መኪና ፈቃድ ማግኘቷ ተነገረ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በሰዓት 100 ማይል የመብረር አቅም ያላትና “ቴራፉጂያ ትራንዚሽን” የሚል ስያሜ የተሰጣት የአለማችን የመጀመሪያዋ በራሪ መኪና፣ ከአሜሪካ ፌዴራል አቪየሽን ባለስልጣን ለበረራ ብቁ እንደሆነች የሚያረጋግጥ የብቃት እውቅና የምስክር ወረቀት ማግኘቷንና በቀጣዩ አመት መብረር ትጀምራለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡
ለአየር ላይ በረራ ብቻ የምትውለውና እስከ 10 ሺህ ጫማ ከፍታ መብረር የምትችለው “ቴራፉጂያ ትራንዚሽን” በአሁኑ ወቅት ለአብራሪዎችና የበረራ ትምህርት ቤቶች ብቻ መፈቀዷን የጠቆመው ዘገባው፣ በመጪው አመት ደግሞ በየብስም ላይ ለመንቀሳቀስ የሚያስችላትን የብቃት ማረጋገጫ በማግኘት፣ በብዛት ተመርታ በገበያ ላይ ትውላለች ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክቷል፡፡
27 ጫማ የሚረዝም ታጣፊ ክንፍ ያላትና ክብደቷ 1ሺህ 300 ፓውንድ ያህል ይደርሳል የተባለው “ቴራፉጂያ ትራንዚሽን”፤ ሁለት ወንበሮች ያሏት ሲሆን መኪናዋ ከ3 አመታት በፊት የመሸጫ ዋጋዋ 400 ሺህ ዶላር ይሆናል ተብሎ እንደነበርም አስታውሷል። ይህቺ ቻይና ሰራሽ መኪና የበረራ ፈቃድ ለማግኘት ለ80 ቀናት ያህል የሙከራ በረራ አድርጋለች ተብሏል፡፡
አሽከርካሪዎች፤መኪናዋን ከበራሪነት ወደ ተሽከርካሪነት ለመቀየር የሚፈጅባቸው ጊዜ ከአንድ ደቂቃ ያነሰ ነው መባሉን የጠቆመው ዘገባው፤ ከአነስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ወይም ሰፋፊ መንገዶች ላይ መነሳትና ማረፍ እንደምትችልም አክሎ ገልጧል፡፡


Read 1268 times
Administrator

Latest from Administrator