Print this page
Monday, 22 February 2021 08:42

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(6 votes)

በወርኃ የካቲት የሚካኤል ለታ
ትልቅ ጠብ ተነስቶ መሬት ተቆጥታ
ቆስሎ ግራዚያኒ ሰበብ ሆናው ደሙ
ብዙ ሰው ታረደ ተናወጸ አለሙ፡፡
በየቤቱ ለቅሶ ጩኸት በየሜዳ
ይሰማል ይታያል በዚህ በዚያ ፍዳ፡፡
የሰው ልጅ እንደ ከብት ወድቆ እየታረደ
ሶስት ለሊት ሶስት መዓልት ከተማው ነደደ፡፡
ሽንትም እንደውኃ ተሸጠ በገንዘብ
ብልህ የሆነ ሰው ይህንን ይገንዘብ፡፡
ኢዮብ ነሽ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር
ወዳጅ
ወድቀሽ አልቀረሽም በጠላትሽ እጅ፡፡
(መስፍን ተፈሪ፤ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፤
የካቲት 12/1961)

በሞት ሥም ግጥም

ምንም ግን ሞት፣
የጨለማ ሽርግድ፣
የሥጋ ከነብስ ስንግ መለየት፤
የሹኩሹክታ ጉድጉድ አይደለም!
ሕይወት ...
ብርሀን መሳይ መስመር ላይ መጓዝ፤
ሞት....
ከመስመሩ ላይ መገፋት፣
ወዳላወቁት መግባት፤
ምናልባት...
ከንቡጥ ጨለማ ውስጥ፣
የማይታይ ብርሀን፣
ይኖር ይሆናል፤
ማን ያውቃል?
(በሳሙኤል በለጠ-ባማ)

Read 2880 times
Administrator

Latest from Administrator