Sunday, 28 February 2021 00:00

የአድዋ ድል አክባሪዎች የአባቶች ስንቅ ተዘጋጅቶላቸዋል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የእቴጌ ጣይቱ ልጅ የነጋድራስ ግዛው ጣይቱ ብጡል መኖሪያ ቤት የነበረው ኤልቤት ሆቴል፣ ለአድዋ በዓል አክባሪዎች ልዩ ድግስ ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡
የኤልቤቴል ሆቴል ባለቤትና የፕሮግራሙ አዘጋጅ የሆኑት ጋዜጠኛ የእናት ፋንታ ውቤ፣ በሆቴላቸው የአድዋን በዓል ለማክበር ወደ አደባባይ ለሚወጡና
በሆቴሉ ለሚያልፉ አክባሪዎች፤ በአድዋ ጦርነት ወቅት በስንቅነት የተቋጠሩ ባህላዊ ምግቦችን ደግሰው ለእንግዶቻቸው እንደሚያቀርቡ ለአዲስ አድማስ
አስታውቀዋል፡፡ በእለቱ የአድዋ ዘማቾች ከ125 ዓመት በፊት በስንቅነት የተጠቀሟቸው ድፎ ዳቦ፣አነባበሮ፣ጠላ፣ጠጅ፣አምባሻ፣ቦርዴ፣ጠጅ፣ጨጨብሳ፣ቆሎና ጭብጦ ባህላዊ ይዘታቸውን በጠበቀ መልኩ ተዘጋጅተው እንደሚቀርቡ የእናት ፋንታ ውቤ አመልክተዋል፡፡ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ የሚገኘው ኤሌቤቴል
ሆቴል፣ እቴጌ ጣይቱ ካሳደጓቸውና በስማቸው ከሚጠሩት ልጆቻቸው አንዱ በሆኑት በነጋድራስ ግዛው ጣይቱ ብጡል መኖሪያ ቤት ውስጥ የተከፈተ ሲሆን በየዓመቱ አድዋን ለየት ባለ መልኩ በመዘከር ይታወቃል፡፡


Read 8134 times