Saturday, 06 March 2021 13:37

COVID-19…ለመከላከል…እውቀትና ፍርሀት

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

    ኮሮና ቫይረስን በሚመለከት ለመከላከል እውቀት አለመኖርና የቫይረሱን ስርጭት በመፍራት ችላ ማለት የሚያስከትለው ውጤት በተለይም በሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ ጎንደር ካሉ እርጉዝ ሴቶች መካከል በተወሰኑት ላይ ጥናት ተደርጎ እ.ኤ.አ14 January 2021 ለንባብ እንዲ በቃ ቀርቦአል። ይህን ጥናት ካቀረቡት ባለሙያዎች መካከል Tesfamichael G/Mariam መረጃውን የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር 29ኛ አመታዊ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅትም አቅ ርበውት ነበር። ጥናቱ የተደረገውም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ክፍሎች ካሉ ባለሙያዎች ጋር ሲሆን ለጥናቱ መልስ እንዲሰጡ የተጋበዙት እርጉዝ ሴቶችም በህክምና ተቋማቱ ቀርበው የጤና ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ ናቸው፡
በአለም ላይ የኮሮና ቫይረስን ስርጭትና  ያደረሰውን ጉዳት ቫይረሱ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በየእለቱ መረጃ የሚወጣ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ብቻ በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ብዛት እንደሚከተለው ተመዝግቦአል፡፡
Africa: 3 754 326 cases; ህመሙ መኖሩን ሪፖርት ያደረጉ አምስት ሀገራት የሚከተሉት ናቸው፡፡ South Africa (1 491 807), Morocco (478 474), Tunisia (223 549), Egypt (173 813) and Ethiopia (147 092).
ከላይ የተገለጸው ቁጥር መረጃው እስከወጣ ድረስ ያለው ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን ለመጨመሩ በኢትዮጵያ ብቻ ከ150.000 በላይ በመድረሱ ማሳያ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ፌብሩዋሪ/25/2021 የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው ቫይረሱ የተገኘባቸው 155.234….በቫይረሱ የሞቱ 2316…. ያገገሙ 133.438 ናቸው። የኮሮና ቫይረስ እስከአሁን በአለም ላይ አስፈሪ የህብረተሰብ የጤና ችግር በመሆኑ ስለመከላከልና መቆጣጠር ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ  ለህዝብ ማዳረስ ተገቢ ነው፡፡ በተለያዩ ሀገራት የሚደረጉ ተያያዥ የሆኑ ጥናቶች አላማቸው ያደረጉትም በተለይም በእርግዝና ላይ ባሉ ሴቶች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጉዳቶችን አስቀድሞ መከላከል እንዲያስችል የታለሙ ናቸው፡፡
በሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ ከJuly - August 2020 መካከል ለተደረገው ጥናት 422 ተሳታፊች የነበሩ ሲሆን ለህክምና ክትትል የሚቀርቡ ሴቶችን ፊት ለፊት በማነጋገርም የተገኙ መልሶችን ያመዛዘነ ነው፡፡ ስለዚህም ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ የኮሮና ቫይረስን በሚመለከት በመከላከል ረረገድ ያለው በጎ ጎን (47.4%) ሲሆን ቫይረሱን በመፍራት ረገድ የተገኙ ውጤቶች (50.9%) ነው፡፡ አብዛኛውን ቁጥር የያዘው በቫይረሱ ላይ ያለው እውቀት ሲሆን እሱም (55.0%) ነው፡፡ በእርግዝና ክትትል ላይ ከነበሩት ሴቶች ግማሽ ያህሉ ከቫይረሱ እራሳቸውን እንዴት እንደሚከላከሉ የሚያውቁ መሆኑ ጥሩ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አሁንም ብዙ እናቶች እውቀ ቱን አለመጨበጣቸው ነገሩን አሳሳቢ ያደርገዋል። አንዳንዶች ደግሞ ከፍርሀት የተነሳ ስለ ቫይ ረሱ ለመስማትም እንኩዋን ዝግጁ አለመሆናቸው የታየ ስለሆነ ይህንን የኮሮና ቫይረስ ሊያስከ ትል የሚችለውን ችግር ለማስወገድ የህክምና ባለሙያዎች ድርሻ ከፍተኛ ይሆናል፡፡
በአስቸኳይ መመለስ የሚገባው ጥያቄ አለ ይላልለ ጥናቱ፡፡ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በተነደፈው ፖሊሲ እና እቅድ ውስጥ መካተታቸውን እና በህመሙ ቢያዙ ሊደርስባቸው የሚችለውን ጉዳት በማሰብ የሚኖራቸውን ፍርሀት አስቀድሞ መገንዘብ ተገቢ መሆኑ ነው፡፡ የመከላከል እርምጃው ማለትም (መራራቅ፤ በቤት ውስጥ መቆየት፤ ሰዎች በተሰ በሰ ቡበት ቦታ እራስን አጋልጦ አለመገኘት፤ የመሳሰሉትን ብዙዎች እንደሚያውቁት ከመልሳ ቸው ቢረጋገጥም ወደተግባር መለወጡ ላይ ግን እጅግ የሳሳ መሆኑ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች በእርግዝናው ምክንያት ሊከሰት የሚችለው አንዳንድ የጤና መዛባት በራሱ በሴትየዋ ላይ ጭንቀትን እና መረበሽን የመሳሰሉ ስሜቶችን የሚፈጥር ሲሆን በዚህ ላይ የኮሮና ቫይረስን ተጨማሪ አድርጎ ማሰብ በእርግጥ ይከብዳል፡፡ ለምሳሌም፤- ከእርግዝና ጋር በተያያዘ ለሞት በግንባር ቀደምትነት እንደሚጠቀሰው የደም ግፊት መጨመር የመሳሰሉትን ሕመሞች እንዳይባባሱ ከማድረግ በተጉዋደኝ የኮሮና ቫይረስ እንዳይከሰት ለማድረግ ፍርሀት ሳይኖር እውቀቱን መጨበጥና መተግበር አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ከተደረገ ለእናትየውም ይሁን ለጨቅላው ደህንነት ዋስትና ይሆናል፡፡
በእርግዝና ጊዜ የሚደረገው የህክምና ክትትል የታወቀ የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጠው ነው። ለምሳሌ አንዲት ሴት በእርግዝናዋ ጊዜ ማለትም እስክትወልድ ድረስ ቢያንስ ቢያንስ ስምንት ጊዜ ከሕክምና ባለሙያ ጋር መገናኘት ይገባታል፡፡ ይህም ከወሊድ በፊት የሚኖረውን ሞት በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን የክትትል ልምዱንም የሚያዳብር ይሆናል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን የኮሮና ቫይረስ በመከሰቱ ምክንያት ለጥንቃቄ ሲባል በሚወሰዱ እርምጃዎች ምክንያት ብዙዎች ይህንን ፕሮግ ራም ለመጠበቅ እንደሚቸገሩ አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ለምሳሌም የህክምና ክትትልን በስልክ ወይንም (online) ማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በገጠሩ ክፍል ለሚኖሩ እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነ ይህ ጥናት ያብራራል፡፡ በከተሞች ነዋሪ ለሆኑትም ቢሆን ከአቅምና እውቀት ባሻገር ሌሎች አስቸጋሪ የሚሆኑ ነገሮች መኖራቸው አይካድም፡፡ በዚህ ምክንያትም ምናልባትም እርጉዝዋ ሴት አስቸኳይ ለሆነ እርዳታ ካልሆነ በስተቀር በፕሮግ ራምዋ መሰረት ወደሕክምና መቅረብዋን ልታቋርጥ ትችላለች፡፡ በእነዚህ በተጠቀሱት ምክን ያቶች COVID-19 ከምርመራ ጀምሮ እስከ ምክር አገልግሎት ያለውን የመከላከል እርምጃ ጥራቱን የሚያዛባ እና በህክምናው አሰራር ሊገታ የሚችለውን የቫይረስ ስርጭት መቋቋም ከማይቻልበት ሊደርስ ይችላል፡፡
አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አንዳንድ ከእርግዝና ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ የጤና ችግሮች በእርግዝና ክትትል ጊዜ የምክር አገልግሎትን በትክክል የሚወስዱ ከሆነ መፍትሔ እንደሚያገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስን በሚመለከት እውቀት መጨበጥና መፍራት ሳይሆን በትክክል መከላከል እንደሚገባ በምክር አገልግሎት አስቀድሞ እንዲያውቁ የሚስችል የምክር አገልግሎት በክትትል ፕሮራማቸው ስለሚሰጣቸው ብዙዎች ካለምንም ችግር በሰላም ልጆቻቸውን ሊወልዱ ችለዋል፡፡ ጥናቱ በተደረገበት አካባቢ በተገኘው መረጃ መሰረት       
(41.3%) የሚሆኑት ቫይረሱን እንዴት መከላከል እደሚቻል ከፍተኛ እውቀት አላቸው፡፡
(77.3%) የሚሆኑት እጃቸውን በደንብ በመታጠብ ቫይረሱን መከላከል እንደሚችሉ ያውቃሉ፡፡
(53.8%) የሚሆኑት ከሰዎች ጋር መጨባበጥ መሳሳም እንደሌለባቸው ያውቃሉ። ባጠቃላይም እርቀታቸውን በመጠበቅ ቫይረሱን መከላከል እንደሚችሉ ተረድተዋል፡፡  
በእርግዝና ላይ ያሉት ሴቶች የእርግዝና ክትትል በትክክል በፕሮግራሙ መሰረት አለመካ ሄዱ ብዙ ችግሮችን እንደሚያስከትል እና የእርግዝና ጊዜው የእናትየውንም ሆነ የልጁዋን ጤን ነት በተሟላ ሁኔታ ካለምንም ሳንካ ከዳር ለማድረስ የሚቻልበትን አሰራር የሚፈትኑ ሁኔታ ዎች መኖራቸው አይካድም፡፡ በአሁኑ ወቅት ሁኔታውን የበለጠ አስቸጋሪ ሊያደርገው የሚች ለው በእርግዝና ላይ ላሉ ሴቶች የኮሮና ቫይረስን በሚመለከት የሚከሰተው አላስፈላጊ የሆነ መጨ ነቅና ፍርሀት ሲሆን በሌላም በኩል ባለው አሰራር ትኩረት የሚሰጠው ይበልጡኑ በአገር ደረጃ ስለመከላከልና አደጋውን ስለመቀነስ ስለሚሆን የእናቶችና የጨቅላዎች እንዲሁም የህጻ ናት ሞትን እንዳይጨምር እንዲሁም የሚከሰተው ፍርሀት ወደአእምሮ መዛባት ወይንም ወደ ስነ ልቦና ቀውስ እንዳያድግ ያሰጋል፡፡ በሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ በተደረገው ጥናትም በእርግ ዝና ላይ ያሉ እና ለህክምና ክትትል ወደጤና ተቋም የቀረቡ ሴቶች የኮሮና ቫይረስን በሚመለ ከት ያላቸው ፍርሀትና እውቀት የሚጠቁሙ መረጃዎችን ከላይ ያስነበብናችሁ ሲሆን ድጋሚ ታነቡት ዘንድ እነሆ፡፡
በሰሜ ምእራብ ኢትዮጵያ በጎንደር በጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ የተደረጉት ለክትትል ወደጤና ተቋም የቀረቡት እናቶች ቁጥር 422 ሲሆን ጥያቄዎችን ሙሉ በሙሉ መልሰዋል፡፡
በጥያቄው ከተጋበዙት ውስጥ ግማሽ ያህሉ (50.9%) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ፍርሀት እንዳለባቸው ታውቆአል፡፡
(55%) የሚሆኑት የእርግዝና ክትትል የሚያደርጉ ሴቶች የኮሮና ቫይረስን ስለመከላከል በቂ እውቀት አላቸው፡፡
(47.4%) የሚሆኑት የእርግዝና ክትትል የሚያደርጉ ሴቶች የኮሮና ቫይረስን መከላከልን በጥሩ ሁኔታ የሚተገብሩ ሆነው ተገኝተዋል፡፡
ይህ ውጤት እንደሚጠቁመው የኮሮና ቫይረስን በመከላል ረገድ ለጥያቄ ከቀረቡት ውስጥ በጥሩ የሚተገብሩት ግማሽ ያህሉ ስለሆኑ የሚመለከተው አካል በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ የሆነ የተሻለ አሰራርን መንደፍ ይጠበቅበታል፡፡Read 11355 times